Tuesday, August 25, 2020

፨ ስለ ዑለማዎች መታዘዝና የመሐይም ኸዋሪጆች ግንዛቤ 

=========================

፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩህና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ፡፡

፨ በአህሉ ሡናዎች ዐቂዳ መሠረት የሚያከፍር መታዘዝ (الطاعة المكفرة) የሚባለው ነገር በልቁ የሚያዝ እንዳልሆነ ሙሐቂቅ ዑለሞቻችን ያስቀምጣሉ፡፡ ኸዋሪጆች ግን ከድሮም ጀምሮ ሱፈሃኡ-አህላም ናቸውና ሸሪዐን እንዴት መገንዘብ እንዳለባቸው የሚረዱ አይደሉም፡፡ የሚያከፍር መታዘዝ የሚባለው በኢስቲህላል ላይ የቆመ ነገር ነው፡፡


- ይህ ማለት በወንጀል ላይ ስንታዘዝ ሐላል በማድረግ ላይ ተመሥርተን የታዘዘን ከሆነ ብቻ እና ብቻ ነው ኩፍር አክበር የሚሆነው...

በተህሊል (ሐላል በማድረግ) እና በተሕሪም (ሐራም በማድረግ) ላይ መታዘዝ የሚባለው ነገር ኩፍር የሚሆነው በኢስቲህላል መልክ ከተፈፀመ ብቻ ነው፡፡ 


የአህሉ-ሡናህ ዑለሞች ይህን አንቀፅ በዚህ መልኩ ነው የተረዱና ያስቀመጡት! 


42:21 * ከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አልሏቸውን? * እንደዚሁ የአሏህ ንግግር ...

9:31 * ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡* እናም 


6:121 *ብትታዘዙዋቸውም እናንተ በእርግጥ አጋሪዎች ናችሁ፡፡*


: {أم لهم شركاء شرعوا لهم من الدين ما لم يأذن به الله} وقوله تعالى : {وإن أطعتموهم إنكم لمشركون} وقوله تعالى : {اتخذوا أحبارهم ورهبانهم أربابا من دون الله} 


፨ እነዚህ አንቀፆች ሐላል በማድረግና ሐራም በማድረግ ላይ መታዘዝን በተመለከተ የሚያሥረዱ ናቸው፡፡ ይህ ነጥብ በሁለት መልኩ ተከፋፍሎ የሚታይ ነው፡፡ 


1ኛ).  በወንጀል ላይ መታዘዝ ይሆናል ይህ *ወንጀል* (معصية)ነው፡፡ 

2ተኛ). ወይ ደግሞ ኢስቲህላል በሚያደርግ ሁኔታ በወንጀል መታዘዝ የሚለው ነው፡፡ ይህ ከሽርክ ይመደባል፡፡ 


፨ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሂመሁሏህ እንዲህ ያብራራዋል

يقول ابن تيمية رحمه الله :

*ሌላን አካል በመሥማትና በመታዘዝ ከከፊል የአሏህ አምልኮቶች የተኩራራ ሠው እዚህ ቦታ ላይ *ላ ኢላሃ ኢለሏህ* የሚለውን ቃል አላረጋገጠም፡፡ እነዛ ቀሳውስቶቻቸውና መነኩሴዎቻቸው ጌታ አድርግ በመያዝ አሏህ ሐራም ያደረገውን ሃላል ሲሉ ፥ አሏህ ሐላል ያደረገውን እነሱ ሐራም ሲሉ የታዘዟቸው ሠዎች በሁለት በኩል ተከፋፍሎ የሚታይ ነው!


(من استكبر عن بعض عبادة الله سامعًا مطيعًا في ذلك لغيره، لم يحقق قول: لا إله إلا اللّه، في هذا المقام. وهؤلاء الذين اتخذوا أحبارهم ورهبانهم أربابا حيث أطاعوهم في تحليل ما حرم اللّه وتحريم ما أحل اللّه 👈🏼 يكونون على وجهين:


#أحدهما: أن يعلموا أنهم بدلوا دين اللّه فيتبعوهم على التبديل، #فيعتقدون تحليل ما حرم اللّه، وتحريم ما أحل اللّه، اتباعًا لرؤسائهم، مع علمهم أنهم خالفوا دين الرسل، فهذا كفر، وقد جعله اللّه ورسوله شركًا وإن لم يكونوا يصلون لهم ويسجدون لهم، #فكان_من_اتبع_غيره_في_خلاف_الدين مع علمه أنه خلاف الدين، #واعتقد ما قاله ذلك، دون ما قاله اللّه ورسوله مشركًا مثل هؤلاء.


፨ አንደኛው. እነሱ የአሏህ ዲን እንደቀየሩ ማወቃቸውና በዚያ በቀየሩት ነገር ሲከተሏቸው ነው፡፡ አለቆቻቸው በመከተል አሏህ ሐራም ያደረገውን ሐላል ነው ብለው #ሲያምኑ ፥ አሏህ ሐላል ያደረገውን ሐራም ነው ብለው #ሲያምኑ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው የአሏህ ዲን የኻለፉ መሆናቸው ከማወቃቸው ጋር ነው፡፡ ይህ ክህደት ነው፡፡ አሏህና መልዕክተኛው ሽርክ አድርገውታል፡፡ ሠዎቹ (ለአለቆቻቸው) ባይሠግዱላቸውም እንኳን ፥ ከዲን በተቃራኒ ያለን ነገር  የተከተለ ሠው ፥ ከዲን የሚፃረር ነገር መሆኑ እያወቀ ከሆነ ፥ አሏህና መልዕክተኛው ከተናገሩት ውጪ በዚያ ነገር ላይ የተናገረውንም #ካመነ እንደነዚያ ሙሽሪክ ይሆናል፡፡ 


#والثاني: #أن_يكون_اعتقادهم وإيمانهم بتحريم الحلال وتحليل الحرام #ثابتًا، لكنهم أطاعوهم في معصية اللّه، كما يفعل المسلم ما يفعله من المعاصي التي يعتقد أنها معاص، فهؤلاء لهم حكم أمثالهم من أهل الذنوب)


፨ ሁለተኛው ፦ " ሐላሉን ሐራም በማድርግና ሐራሙን ሐላል በማድረግ ላይ ያላቸው እምነት የተረጋገጠ ነው፡፡ ነገር ግን አሏህን በማመፅ ነው የታዘዟቸው፡  ልክ አንድ ሙሥሊም ማንኛውም ወንጀል እንደሚሠራው ፥ ያ ወንጀል መሆኑን እያመነ የሚሠራው ነው ፥ እነዚህ ሠዎች እኔደ አምሳዮቻቸው የወንጀል ባለቤቶች አይነት ሁክም ነው ያላቸው፡፡ * 


📚


፨ ይህንን ነጥብ ይበልጥ በማብራራት እንመልከተው፡፡ ከሠለፎች የፀደቁ አሰሮችና የሙፈሲሮች ንግግር እየመጣን ፥ የስንኩል ግንዛቤ ባለቤቶች (ኸዋሪጆችን) እንምከር


፨ ኢማም አቡ ጃዕፈር አጥ-ጦበሪይ ረሂመሁሏህ እንዲህ ብሏል ፦ የአሏህን ንግግር [ ከአሏህ ውጪ ጌቶች አድርገው.. ] የሚለው (أربابا من دون الله) የሚለው ሲያብራራው እንዲህ ብሏል ፦ "ይህ ማለቱ ከአሏህ ውጪ ለነሡ አለቃ አደረጓቸው፡፡ #አሏህን_በማመጽ_ላይም_ይታዘዟቸዋል፡፡" አለ፡፡


يقول الإمام الطبري رحمه الله في تفسير قوله تعالى (أربابا من دون الله) : [ يعني: سادةً لهم من دون الله، #يطيعونهم_في_معاصي_الله]

፨ ይህ ንግግር ከቀልባችን አስተንትነን እንረዳው ፥ በርግጥ ኢማም አጥ-ጦበሪይ ማብራርያ አልጨረሰም፡፡ እንደ አንዳንድ ሱፈሃኡ-አህላም የሩጫ ግንዛቤ እቺን ቦታ ብቻ ቆረጠው ያመጧትና ባጢላቸውን ለመገንባት ይጣጣራሉ፡፡ ነገርግን ቀጥለን በደንብ የሚያብራራውን የኢማም አጥ-ጦበሪ ንግግር እናምጣው...


" (አለቆቻቸው) ሐላል ያደረጉትን ነገር ሐላል ነው ይላሉ ፥ በርግጥ አሏህ ሐራም አድርጎት እያለ፡፡ (አለቆቻቸው) ሐራም ያደረጉትን ሐራም ነው ይላሉ ፥ በርግጥ አሏህ ሐላል ካደረገው ነገር ሆኖ እያለ፡፡ " አለ ኢማም አጥ-ጦበሪይ ረሂመሁሏህ


[فيحلون ما أحلُّوه لهم مما قد حرَّمه الله عليهم، ويحرِّمون ما يحرِّمونه عليهم مما قد أحلَّه الله لهم]


፨ እዚህ ጋር ቆም ብለን የምናየው ነገር ቢኖር እነዚህ ሠዎች  ዑለሞቻቸው አሏህ ሃላል ያደረገውን ነገር  ሐራም ነው ሲሏቸው "አዎ ሃራም ነው" ሳይሉ ቢታዘዟቸውና ቢፈፅሙ ተግባራቸው ኩፍር አይሆንም፡፡ ባይሆን የማያከፍር ወንጀል ይሆንባቸዋል፡፡ ነገር ግን አሏህ ሐላል ያደረገውን ፥ አለቆቻቸው ሐራም ነው ሲሉ  *አዎ! ሐራም ነው* ብለው ከታዘዟቸው ይህ ጊዜ ኩፍር ይሆንባቸዋል፡፡ 


የኢማም አጥ-ጦበሪይ ሙሉው ንግግር ይኽ ነው፡፡👇

(يعني: سادةً لهم من دون الله، #يطيعونهم_في_معاصي_الله فيحلون ما أحلُّوه لهم مم


ا قد حرَّمه الله عليهم، ويحرِّمون ما يحرِّمونه عليهم مما قد أحلَّه الله لهم)


፨ ይቺ ነች የምታከፍር መታዘዝ በመባል የምትታወቀው፡፡ በወንጀል ስንታዘዝ ሐላል አድርገን ከታዘዝን ማለት ነው፡፡ 


ከዚህ በመቀጠል ኢማም አቡጃዕፈር ረሂመሁሏህ በተፍሢሩ ላይ የተለያዩ አሳሮች አምጥቶ ይህ የአህሉ ሡናህ ዐቂዳ ያጠናክረዋል፡፡ 


[16633- حدثني سعيد بن عمرو السكوني قال: حدثنا بقية، عن قيس بن الربيع, عن عبد السلام بن حرب النهدي, عن غضيف, عن مصعب بن سعد, عن عدي بن حاتم قال:


* ዐዲይ ቢን ሃቲም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ "የአሏህ መልዕክተኛ ሠለሏሁ ዐለይሒ ወሠለም ሡረቱል በራኣ እየቀሩ ሠማኋቸው፡፡ "ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡" (اتخذوا أحبارهم ورهبانهم أربابًا من دون الله) የሚለው ሲቀሩ "የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! እነሱ እኮ (ለሊቃውንቶቻቸውና ለመነኮሳቶቻቸው) አይሠግዱላቸውም ነበር፡፡ " አልኩኝ አለ፡፡ 


- እሳቸውም "እውነት ብለሃል ፣ ነገርግን አሏህ ሐራም ያደረገውን ነገር እነሱ (ሊቃውንቶችና መነኩሴዎቹ) ሐላል ያደርጉላቹህ ነበር፡፡ #እነዚያም_ሐላል_(ያደርጉታል)_ነው_ይላሉ፡፡ አሏህ ሐላል ያደረገውን እነሱ ሐራም ያደርጉታል፡፡ እነዚያም ሐራም (ያደርጉታል) ነው ይላሉ፡፡ " 


سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقرأ " سورة براءة "، فلما قرأ: (اتخذوا أحبارهم ورهبانهم أربابًا من دون الله)، قلت: يا رسول الله, إما إنهم لم يكونوا يصلون لهم! قال: صدقت, ولكن كانوا يُحلُّون لهم ما حرَّم الله #فيستحلُّونه, ويحرّمون ما أحلّ الله لهم فيحرِّمونه. (44)


፨ በዚህ የዐዲይ ቢን ሃቲም ረዲየሏሁ ዐንሁ ሐዲስ ላይ የተብራራው..

1ኛው). እነዚያ ጌታ አድርገው ያዙ የተባሉ ሠዎች ለሊቃውንቶቻቸውና ለመነኩሴዎቹ አይሠግዱላቸው ነበር፡፡ ያመልኳቸዋል የተባለው በሌላ አይነት እንደሆነ ረሡል ሠለሏሁ ዐለይሒ ወሠለም አብራሩለት፡፡ 


2ተኛ. እነዚያ ሠዎች አለቆቻቸው ጌታ አድርገው ያዙ የተባለው ፥ ሊቃውንቶቹና መነኩሴዎቹ ሃራምና ሃላል ብለው ሲነግሯቸው ፥ በወንጀል ስለታዘዟቸው ብቻ አይደለም፡፡ እንግዲያውስ አለቆቹ ሐላል ነው ፥ ሲሉ ተከታዮችም አዎ ሐላል ነው ብለው ይተገብሩ ስለነበር ነው፡፡ ይህ ለማረጋገጥ فيستحلُّونه በማለት በመዕሲያ ብቻ ስለታዘዟቸው እንዳልሆነ ገለፁ፡፡ 


፨ ሌላው የሠለፎች አሳር ፦ ከኹዘይፋህ የተዘገበ ነው፡፡ እሱም "ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡" ስለሚለው የአሏህ ቃል ተጠየቀ.. " ያመልኳቸው ነበርን?" ተብሎ ተጠየቀ፡፡


-እንዲህ መለሠ "አይ (አለቆቻቸው) ለእነሱ የሆነ ነገር ሐላል ያደረጉላቸው ጊዜ #እነሱም_ሐላል_ያደርጉታል፡፡ በእነሱ ላይ የሆነን ነገር ሐራም ያደረጉባቸው ጊዜ #ሐራም_ያደርጉት ነበር፡፡ " 


16634- حدثنا محمد بن بشار قال، حدثنا عبد الرحمن بن مهدي قال، حدثنا سفيان, عن حبيب بن أبي ثابت, عن أبي البختري, عن حذيفة: أنه سئل عن قوله: (اتخذوا أحبارهم ورهبانهم أربابًا من دون الله)، أكانوا يعبدونهم؟ قال: لا كانوا إذا أحلُّوا لهم شيئًا #استحلوه, وإذا حرَّموا عليهم شيئًا حرَّموه.


በዚህ 👇 ዘገባ ደግሞ ለኹዘይፋህ እንዲህ ተባለ " ሊቃውንቶቻቸው ያዙ  ..."( اتخذوا أحبارهم) ስለሚለው የአሏህ ቃል ምን ትላለህ?" ተባለ፡፡ እንዲህ አለ "እነሱማ ለነሱ ብለው አይፆሙላቸውም ፥ አይሠግዱላቸውም ነበር፡፡ ነገርግን ለነሱ አንድ ነገር ሐላል ሲያደርጉላቸው (እነሱም) #ሐላል ይሉ ነበር፡፡ አሏህ ሃላል ያደረገላቸው ነገር ሆኖ (አለቆቻቸው) ሐራም ነው ሲሉ እነሱም #ሐራም ነው ይላሉ፡፡ በዚህ መልኩ ነበር ጌታ ተደርገው የመያዛቸው ነገር፡ " 


16636- حدثنا ابن وكيع قال، حدثنا يزيد بن هارون, عن العوام بن حوشب, عن حبيب عن أبي البختري قال: قيل لحذيفة: أرأيت قول الله: (اتخذوا أحبارهم) ؟ قال: أمَا إنهم لم يكونوا يصومون لهم ولا يصلون لهم, ولكنهم كانوا إذا أحلوا لهم شيئًا #استحلُّوه, وإذا حرّموا عليهم شيئًا أحله الله لهم حرَّموه, فتلك كانت رُبوبيَّتهم.]


፨ እዚህ በተጨማሪ የሚባለው ወደ-ጧጉት መፋረድ ኩፍር የሚሆነው በኢስቲህላል መልክ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም ወደጧጉቱ ተሃኩም አደርግን ማለት በሚፈርድበት ነገር #ታዘዝነው ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ተሃኩም (التحاكم) መሠረቱ መታዘዝ ነው፡፡ 


ለዚህም ነው አሏህ ሱብሃነሁ ወተዐላ ለነዚያ ሙናፊቆች ሲወቀሳቸው *መታዘዝን በተመለከተ ርዕስ ላይ ነው፡፡* ምክንያቱም መታዘዝ ነው የተሃኩም መሠረቱ፡፡ ይህ ማለት በአንድ መሥዐላ ላይ አ


ሏህን በቀልብና በሠውነታችን በምንሠራው ተግባር ለመታዘዝ  የአሏህን ሑክም መፈለግ ማለት ነው ተሃኩም ሲባል፡፡ 


አሏህ እነዚያ ሙናፊቆችን ሲወቅሳቸው የተናገረውን እንይ

: {وَمَا أَرْسَلْنَا مِن رَّسُولٍ #إِلَّا_لِيُطَاعَ_بِإِذْنِ_اللَّهِ ۚ وَلَوْ أَنَّهُمْ إِذ ظَّلَمُوا أَنفُسَهُمْ جَاءُوكَ فَاسْتَغْفَرُوا اللَّهَ وَاسْتَغْفَرَ لَهُمُ الرَّسُولُ لَوَجَدُوا اللَّهَ تَوَّابًا رَّحِيمًا}


[ ማንንም መልክተኛ በአላህ ፈቃድ ሊታዘዙት እንጅ አልላክንም፡፡ እነሱም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ ወደ አንተ ቢመጡና አላህንም ምሕረትን በለመኑ መልክተኛውም ለነርሱ ምሕረትን በለመነላቸው ኖሮ አላህን ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ኾኖ ባገኙት ነበር፡፡ ] 4:64

يقول الإمام الطبري رحمه الله :

፨ ኢማም አጥ-ጦበሪይ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላል ፦ " ይህ ከአሏህ ዘንድ የሆነ ማሥፈራርያ ነው፡፡ ለነዚያ ተሃኩምን ፈልገው የሄዱትን፡፡ እነሱ በነብዩ ሠለሏሁ ዐለይሒ ወሠለም ላይ በተወረደው አምነናል ብለው ይሞግቱ ነበር፡፡ ወደጧጉትም በመካከላቸው ባለው ጉዳይ ሊፋረዱ ሄዱ ፥ ከረሡል ሠለሏሁ ዐለይሒ ወሰለም እየሸሹ፡፡" ለነሱ አሏህ እንዲህ ይላቸው: አንድም መልዕክተኛ አልላኩም ፥ ወደሱ በላኩት ነገር ላይ እንዲታዘዙት ግዴታ ባደርግ እንጂ፡፡ ሙሐመድ ሠለሏሁ ዐለይሂ ወሠለም ከነዚያ ሩሡሎች መካከል ነው፡፡ እሳቸውን መታዘዝና ሑክማቸውን መውደድ የተወ ሠው ፥ ከዚያ ወደጧጉት ሄዶ የተፋረደ የኔን ትዕዛዝ ጥሷል፡፡ ግዴታ ያደረግኩት ነገርም አጠፋ፡፡ " 




(وإنما هذا من الله #توبيخ للمحتكمين من المنافقين = الذين كانوا يزعمون أنهم يؤمنون بما أنـزل إلى النبي صلى الله عليه وسلم = فيما اختصموا فيه إلى الطاغوت، صدودًا عن رسول الله صلى ال


له عليه وسلم. يقول لهم تعالى ذكره: ما أرسلتُ رسولا إلا #فرضت_طاعته على من أرسلته إليه، فمحمد صلى الله عليه وسلم من أولئك الرسل، #فمن_ترك_طاعته_والرِّضى_بحكمه_واحتكم_إلى_الطاغوت، فقد خالف أمري، وضيَّع فرضي.)

📚 አጥ-ጦበሪ


፨ ስለተሃኩም ሲወራ አስሉ መሠረቱ ከጧዐ (መታዘዝ) የሚመደብ ነገር ነው፡፡ 


፨ስለዚህ በሌላ ክፍል እንመጣበታለን፡፡ ዋናው የተፈለገው መልዕክት ዑለማዎች ፥ ሊቃውንቶች ፥ መነኩሴዎች የመሳሰሉት ያለ ኢስቲህላል ሐራምና ሐላል ብለው ከአሏህ ኪታብ ውጪ በሚሉት ነገር መታዘዝ  ትልቁ-ኩፍር አይደለም፡፡


🔖 ወልሐምዱሊላሂ ረቢል ዐለሚን

Monday, August 24, 2020

ስለ-ተሃኩም በተመለከተ የሡረቱ ኒሳእ ፡61 አንቀፅ ማብራርያ

🔖 በአሏህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩህና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ፡፡  

በዚህ ሁፍ በአሏህ እርዳታ በመታገዝ ወደ ጧጉት መፋረድ ምን እንደሆነ እና ወደ ጧጉትም መፋረድ ያለው ሁክም እንመለከታለን፡፡ በምን አይነት ሁኔታ ወደ ተሃኩም መፋረድ ኩፍር አክበር የሚሆነው? እናያለን፡፡ 


🔖 ይህ አንቀፅ የወረደባቸው ሠዎች ክህደት ያገኛቸው ወደ ጧጉት በመፋረዳቸው ብቻ ነውን ወይስ የጧጉትን ሁክም ከአሏህ ሁክም የበለጠ ፥ ወይም እኩል የሆነ ፥ ወይም ኢስቲህላል ያደርጉም ስለነበር ነው ፥ ወይስ  በአሏህ ሁክም አይወዱም ነበር?


  እዚህ ቦታ ንግግራችን ሁሉ ሊሽከረከርበት የሚችልበትን ሁለት መግቢያ አስቀድመን የምንመለከት ይሆናል፡፡ 


#የመጀመርያው).  በዚህ አንቀፅ ላይ ተሃኩም ያደረጉት ሠዎች ትክክለኛው ተግባራቸው ምን እንደነበረ ማረጋገጥ፡፡ 


#ሁለተኛው) .እነዚያ ሠዎች በትክክል ይተገብሩ የነበረው #ተግባራቸው ከዑለሞች በማረጋጥ እንመለከታለን፡፡ 


ይህ አሁን በዝርዝር የምንመለከተው መስዐላ *አሏህ ባላወረደው ነገር መፍረድ* የሚለው ውስጥ ሊካተት የሚችል ነገር ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ሠለፎች ዘንድ እንኳን በተቅኒን ደረጃ ተከስቷል፡፡ በታብዕዮች ዘመን ሙኩስ የተባለን በሸሪዐ የሌለ ህግ አውጥተው ያስተዳድሩ ነበር፡፡ በኒ ኡመዮችን በዚህ ያከፈራቸው አንድም የለም፡፡ ( አንዳንዶች ይህ ሲባል በዘመናችን ያሉ የአሏህን ሁክም የመለሱ ፥ ኢስላማዊ መንግስት ኋላቀርነት ነው የሚሉ ፥ ኢስቲህላልና ሌሎችም ኩፍርያት የሆኑ ነገሮች የሞሉበት *ዲሞክራሲያዊ* ሥርዐት አራማጆችን እንዲሁም በሙሥሊሞች ካፊርን እያገዙ ያሉ ሙርተዶችን በዚህ ርዕስ የሚመደቡ ይመሥላቸዋል፡፡ ነገሮቹ ልዩነታቸው ለማወቅ የዑለሞች ትክክለኛ መንሐጅ ይዘን ራሳችን ከጥመት ተጣሪዎች መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ 


፨ በቀጥታ ወደ አንቀፁ ማብራርያ ስንገባ ልብ ብለን መረዳት ያለብን ነገር ይኖራል፡፡ 

1ኛ). ተሃኩም ማድረጋቸው የኒፋቃቸው ምልክት እንደነበር

2ኛ). ተሃኩም አድርገው የነበረው የአሏህ ሁክም ከመፈፀም ኩራት ይዟቸው (በኢስቲክባር) እንደነበር እና የአሏህ ሑክምን ወደው የሚቀበሉ ስላልነበሩ ነው ክህደት ላይ የወደቁት.. 


በመጀመርያ አንቀፁን እናቅርበው፡፡ ትክክለኛ የኩፍራቸው ሁኔታ እንዴት እንደነበረና አሏህም ምን አይነት ሁክም እንደወሠነባቸው እንይ፡፡


፨ አሏህ የሙናፊቆችን ሁኔታ እንዲህ በማለት ይነግረናል፡፡ አስተንትነት እናንብበው፡፡


4:61* ወደ እነዚያ እነርሱ በአንተ ላይ በተወረደውና ከአንተ በፊትም በተወረደው አምነናል ወደሚሉት፤ አላየህምን በእርሱ እንዲክዱ በእርግጥ የታዘዙ ሲኾኑ ወደ ጣዖት መፋረድን ይፈልጋሉ፡፡ ሰይጣንም (ከእውነት) የራቀን መሳሳት ሊያሳስታቸው ይፈልጋል፡፡ * 


قال الله تعالى : {ألم ترَ إلى الذين يزعمون أنهم آمنوا بما أنزل إليك وما أنزل من قبلك يريدون أن يتحاكموا إلى الطاغوت وقد أمروا أن يكفروا به ويريد الشيطان أن يضلهم ضلالا بعيدا 


4:65 * ለእነርሱም፡- «አላህ ወደ አወረደው (ቁርኣን)ና ወደ መልክተኛው ኑ» በተባሉ ጊዜ መናፍቃን ከአንተ መሸሽን ሲሸሹ ታያቸዋለህ፡፡*


وإذا قيل لهم تعالوا إلى ما أنزل الله وإلى الرسول رأيت المنافقين #يصدون_عنك_صدودا


4:66 * እጆቻቸውም ባስቀደሙት (ጥፋት) መከራ በደረሰችባቸውና ከዚያም «ደግን ሐሳብና ማስማማትን እንጅ ሌላ አልሻንም» በማለት በአላህ የሚምሉ ኾነው በመጡህ ጊዜ እንዴት ይኾናሉ? *


فكيف إذا أصابتهم مصيبة بما قدمت أيديهم ثم جاؤك #يحلفون_بالله_إن أردنا إلا #إحسانا_وتوفيقا ,  

* እነዚህ እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፡፡ እነርሱንም ተዋቸው ገሥጻቸውም፡፡ ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው፡፡ *

أولئك الذين يعلم الله #ما_في_قلوبهم  #فأعرض_عنهم وعظهم وقل لهم في أنفسهم قولا بليغا}


.................. ሙሉ አንቀፁ ይህ ይመሥላል፡፡ በዚህ አንቀፅ መነሳት የሚኖርባቸው ወሳኝ ነጥቦች እያየን እንቀጥላለን፡፡


1ኛው). አሏህ እንደሚጠቅስልን እነዚህ ሠዎች ፥ አሏህ ካወረደው ኪታብ (ሑክም) ይሸሻሉ፡፡ ይህ ማለት ከአሏህ ሁክም ይሸሻሉ (ኢዕራድ ያደርጋሉ) ማለት ነው፡፡ 


፨ ኢብኑል ሙንዚር ተፍሢሩ ላይ እንደመጣው ፦

جاء في تفسير إبن المنذر :

1949 - حَدَّثَنَا زكريا، قَالَ: حَدَّثَنَا أَبُو جعفر مُحَمَّد بْن أحمد بْن نصر، قَالَ: حَدَّثَنَا يوسف بْن عدي، قَالَ: حَدَّثَنَا رشدين، عَنْ يونس بْن يزيد، عَنْ عطاء، فِي قول الله جل ثناؤه "{يَصُدُّونَ عَنْكَ صُدُودًا} ، قَالَ: الصدود: الإعراض "


በዚህ ሠነድ ላይ ታብዒዩ ዐጧእ ( ረሂመሁሏህ) * ከአንተ መሸሽን ሲሸሹ ታያቸዋለህ፡፡* (يَصُدُّونَ عَنْكَ صُدُودًا) የሚለው ሲተረጉም *አስ-ሱዱድ* (الصدود)  የተባለው መሸሽ ኢዕራድ (الإعراض) ነው ብሏል፡፡ 📚 ተፍሢር ኢብኑል ሙንዚር


፨ ኢብኑ ከሢር ረሂመሁሏህ ተፍሢሩ ላይ እንዲህ አስቀምጧል፡፡

- وفي تفسير ابن كثير

"( يصدون عنك صدودا ) أي : يعرضون عنك #إعراضا_كالمستكبرين عن ذلك."

* " ከአንተ መሸሽን ሲሸሹ ታያቸዋለህ" ( يصدون عنك صدودا ) የሚለው ማለት የተፈለገው * እንደኩራተኞች (كالمستكبرين) በመሆን ካንተ መሸሽን ይሸሻሉ፡፡* ብሎ አስቀምጧል፡፡ እንግዲህ ሙናፊቆቹ ኢስቲክባር (መኩራት) እንደነበረባቸው ግልፅ ሆነ ማለት ነው፡፡ 


፨ እንደሚታወቀው አል-ኢስቲክባር (والاستكبار) የኢብሊስ ክህደት አይነቶች ሥር የሚገባ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የኢብሊስ ኩፍር ኢስቲክባር (መኩራት) የነበረበት ነው፡፡ እነዚህ ሙናፊቆችም ይህን *ኢስቲክባር* የተጠናወታቸው ነበሩ፡፡ "መፋረድን መተው" ብቻ የሚመለከት ነገር አልነበረም፡፡ 


-አንድ ሠው በአሏህ ሁክም የዝሙትን ሐራምነት ላይ ኩራት ይዞት ፥ ዝሙት ቢፈፅም ካፊር ይሆናል፡፡ ነገርግን ያለኩራት ዝሙት የፈፀመ እንደሆነ ካፊር አይሆንም፡፡ የነዚህ ሙናፊቆችም " መፋረድን መተዋቸው" ብቻ አልነበረም ለዚህ የዳረጋቸው *ኢስቲክባር* ስለነበረባቸው ነው፡፡ 


፨ ሙቃቲል ቢን ሡለይማን 📚 ተፍሢር ላይ እንዲህ ይገልፀዋል፡፡ 

* ከአንተ መሸሽን ሲሸሹ ታያቸዋለህ * (يصدون عنك صدودا) የሚለውን ፥ ማለት የተፈለገበት "አንተ ሙሃመድ ሆይ! ካንተ ውጪ ወደሆነ አካል መሸሽን ይሸሻሉ፡፡ ይህ ያደረጉት በፍርድ ላይ እንዳትበድላቸው በመፍራት ነው፡፡ * 📚 ተፍሢር ሙቃቲል

- وفي تفسير مقاتل بن سليمان

"(يصدون عنك صدودا)  يعني يعرضون عنك يا محمد إعراضا إلى غيرك، #مخافة_أن_تحيف_عليهم" 


፨ እነዚህ ሙናፊቆች ከረሡል ﷺ በኩል በደል ይደርስብናል ፥ ይበድለናል ብለው በራሳቸው ላይ ይፈሩ ነበር፡፡ ምንም ጥርጥር የሌለው ነገር የኢሥላም ሸሪዐህ ፍትሐዊ እንደሆነና በደል እንደሌለበት የማያምን ሠው ካፊር ነው፡፡


-2ተኛው). አሏህ ስለነዚህ ሙናፊቆች ሲገልፅ ፥ እነሱ በአሏህ ይምሉ ነበር፡፡ እነሱ (በዚህ ተሃኩም ፈልጋ ወደሌላ መሄዳቸው) «ደግን ሐሳብና ማስማማትን እንጅ ሌላ አልሻንም» በማለት ነበር፡፡ አሏህ ሡብሃነሁ ወተዐላ ግን በቀልቦቻቸው የያዙት የደበቁትን ያውቅ ነበር፡፡ ይህ በዋናነት ከሚሠጠን ማሥረጃ መካከል ፥ እነዚህ ሙናፊቆች በውስጣቸው ካለ የተለየ ነገር በውጭ ገፅታቸው ያሳዩ ነበር፡፡ በውስጣቸው ኒፋቅ ነበር፡፡ 


፨ ኢብኑ ዘመነይን እንዲህ ብሏል ፦


قال ابن زمنين :

(فكيف إذا أصابتهم مصيبة) قال الحسن : وهذا كلام منقطع عما قبله وعما بعده ؛ يقول : (إذا أصابتهم) يعني : #أن_يظهروا_ما_في_قلوبهم_فيقتلهم رسول الله - صلى الله عليه وسلم - 


*መከራ በደረሰችባቸውና ከዚያም «ደግን ሐሳብና ማስማማትን እንጅ ሌላ አልሻንም» በማለት በአላህ የሚምሉ ኾነው በመጡህ ጊዜ እንዴት ይኾናሉ* የሚለው ላይ (فكيف إذا أصابتهم مصيبة) "መከራ ባጋጠማቸው ጊዜ እንዴት ይኾናሉ" የሚለው የአሏህ ንግግር ከፊትና ከኋላ ካለው ንግግር የተቋረጠ ነው፡፡ *ባገኛቸው ጊዜ * ሲል በቀልቦቻቸው የደበቁትን ግልፅ ባደረጉ ጊዜ ረሡል ይገድሏቸዋል፡፡ ማለት ነው፡፡ 


(ثم جاءوك يحلفون بالله إن أردنا إلا إحسانا وتوفيقا) أي :

#إن_أردنا_إلا_الخير .(أولئك الذين يعلم الله ما في قلوبهم) : #من_الشرك_والنفاق}

* ከዚያም «ደግን ሐሳብና ማስማማትን እንጅ ሌላ አልሻንም» በማለት በአላህ የሚምሉ ኾነው በመጡህ ጊዜ እንዴት ይኾናሉ* ማለቱ  መልካምን እንጂ ሌላ ፈልግን አይደለም አሉ፡፡ * እነዚህ እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፡፡ እነርሱንም ተዋቸው ገሥጻቸውም፡፡ ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው፡፡ *


📚 ተፍሢር ኢብኑ ዘመነይን


፨ እንደዚሁም ሙናፊቆቹ በውጣቸው ያለው ሌላ ፥ በውጭ ገፅታቸው የሚያሳዩት ሌላ እንደሆነ ከሚጠቁሙት መካከል 

وفي تفسير البغوي : 

"( أولئك الذين يعلم الله ما في قلوبهم ) من النفاق ، أي : #علم_ان_ما_في_قلوبهم #خلاف_ما_في_ألسنتهم"


[ አል-በገዊ ፦ እንዲህ ብሏል *እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፡፡* ከነፍቅና የተነሳ ይህ በሚለው የተፈለገበት በቀልባቸው የቋጠሩት ፥ በምላሳቸው ከሚሉት ተቃራኒ ነው፡፡ 

وفي تفسير الحافظ عز الدين الرسعني الحنبلي : 

፨ ዒዘዲን አርረሥዐኒ አልሃንበሊ በተፍሲሩ እንዲህ ብሏል ፦


* እጆቻቸው ባስቀደመው (ጥፋት)*  ሲል አሏህ #ኒፋቃቸው እና #ወደ_ጧጉት_መፋረዳቸውን_ነው፡፡ *ደግን ሐሳብና ማስማማትን እንጅ ሌላ አልሻንም* ሲሉ ደግሞ ማለት የፈለጉት መልካም ነገር ፥ ሐቅን የሚገጥም ነገር በመፈለግ ነው፡፡ ማለታቸው ነው፡፡ በሌላም እንደተባለው * ከአንተ ውጪ ወደ አለ ሄደን መፋረድ አልፈለግንም በሁለቱ ተከራካሪዎች ዘንድ መልካም ነገርና ማስማማት እንጂ፡፡* ይላሉ፡፡ የአንተን ሑክም ለመቃረን ብለን ወይም ባንተ ፍርድ ወደን የማንቀበል ሆነን አይደለም፡፡ #ይህ_ከነሱ_የሆነ_ውሸት_ነው፡፡ አታይምን አሏህ የሚለውን *እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፡፡* በልቦቻቸው ያለው ሲል ኒፋቅና ኩፍር ፥ እንዲሁም ከደበቁት ተቃራኒ ነገር ግልፅ ማድረጋቸውን ነው፡፡ ]


[( بما قدمت ايديهم ) #من_النفاق_والتحاكم_إلى_الطاغوت .

( إلا إحسانا وتوفيقا ) اي : #خيرا_وطلبا #لما_يوافق_الحق .

وقيل : #ما_اردنا_بالتحاكم إلى غيرك #إلا_إحسانا_وتوفيقا #بين_الخصمين #لا_مخالفة_حكمك #وعدم_الرضى_بقضائك #وذلك_كذب_منهم ، ألا تراه يقول ( أولئك الذين يعلم الله ما في قلوبهم ) يعني #من_الكفر_والنفاق #وإضمارهم_خلاف_ما_يبطنون .} 

📚ተፍሢር ዒዘዲን


፨ ሙፈሢሩ ኢብኑ ከሢር ረሂመሁሏህ እንዲህ ብሏል ፦* እነዚህ እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፡፡ እነርሱንም ተዋቸው ገሥጻቸውም፡፡ ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው፡፡ * ሲል አሏህ ማለት የተፈለገው " ወደ አንተ ዑዝራቸውን ያቀርባሉ፡፡ ይምላሉም፡፡ " እኛ ካንተ ውጪ በመሄዳችን ፥ ካንተ ውጪ ወደሆነ አካል መፋረዳችን ደግን ሐሳብንና ማስማማትን እንጂ ሌላ ፈልገን አይደለም ይላሉ፡፡ እንዲሁ በውጪ ገጽታ ለማሥመሠል ብለን እንጂ ከውስጣችን እዛ ያለው ፍርድ አምነንበት አይደለም፡፡ " ይላሉ፡፡ 


وفي تفسير ابن كثير [ (ثمّ جاءوك يحلفون باللّه إن أردنا إلا إحسانًا وتوفيقًا) أي: يعتذرون إليك ويحلفون : ما أردنا بذهابنا إلى غيرك، #وتحاكمنا_إلى_عداك إلّا إلإحسان والتوفيق ، أي: #المدارة_والمصانعة، #لا_إعتقادا_منا #صحة_تلك_الحكومة،]


፨ እነሡ ውሸታቸውን እኛ የአሏህን ሑክም እንወዳለን ብለው ይሞግታሉ፡፡ በአሏህ ሁክም ወደው የሚቀበሉ አይደሉም፡፡ እንደውም የአሏህ ሁክም ትክክለኝነት አይቀበሉም፡፡


3ተኛው). አሁን ወደ ዋናው ነጥብ መጥተናል፡፡ በመጨረሻም አሏህ ስለነዚህ ሠዎች ሲናገር እንዲህ ነበር ያለው ፦

{فأعرض عنهم وعِظْهم وقل لهم في أنفسهم قولاً بليغاً} 

*እነርሱንም ተዋቸው ገሥጻቸውም፡፡ ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው፡፡* አለ አሏህ፡፡


፨ይህ የጌታችን ትዕዛዝ ብቻውን ወደ ጧጉት መፋረድ ብቻውን ኩፍር አክበር ነው ፥ ከኢስላም ያስወጣል የሚሉ ሠዎችን  መሠረት ለማውደም በቂ ይሆን ነበር፡፡ 


፨ ልብ በል ‼️እነዚህ ሙናፊቆች በገሃድ የሠሩት ሥራ [ ከሸሪዐ ውጪ ወደ ሆነ ነገር መፋረድ ብቻ ] ሆኖ ፥ ያለምንም ኢስቲክባር ፥ ኢስቲህላል ኩፍር አክበር ነው ቢባል ኖሮ ፥ አሏህ መልዕክተኛውን (ሠለሏሁ ዐለይሂ ወሠለም) *ኢስቲታባ* እንዲያርጓቸው ያዝ ነበር ወይም ከኩፍር ተውበት እንዲያደርጉ አለበለዚያ እንደገደሉ ያደርግ ነበር፡፡


- የኩፍር አህካሞችን በነዚህ ሠዎች እንዲፈፀም ባደረጉ ነበር ፥ ነገር ግን አሏህ ረሡልን *ተዋቸው ነው ያላቸው ፥ ከነሱ እንዲሸሹ ነው የነገራቸው፡፡ * ምክንያቱ ምንድነው ከተባለ አሏህ ለረሡል ሠለሏሁ ዐለይሒ ወሠለም የነዚህ ሠዎች ውስጣዊ ምንነታቸው አሳወቃቸው፡፡ እነዚህ ሠዎች ወደጧጉት ሲፋረዱ ፥ በጧጉቱ ሁክም ወደው እንደሆነ ፥ የጧጉቱ ሑክም ከአሏህና መልዕክተኛ ሑክም የተሻለ ነው ብሎ እንደሄዱ ወይም ከአሏህ ሁክም እኩኩል ነው ብለው በማሠብ ሄደው እንደተፋረዱ አሳወቃቸው፡፡ ከላይ በውጪ ገፅታቸው የሚያሳዩት በውስጣቸው ካለው የተቃረነ ነበር፡፡ በውኮጣቸው አምቀው የያዙት ነገር ግልፅ ቢያደርጉ ኖሮ የአሏህ መልዕክተኛ በተጋደሏቸው ነበር፡፡ ምክንያቱም *ሙርተድ* ሆነው ነበር እና፡፡ 


፨ ኢብኑ ዘመነይን እንዲህ ብሏል ፦

قال بن زمنين :

" (أولئك الذين يعلم الله ما في قلوبهم) : #من_الشرك_والنفاق

(فأعرض عنهم) : #فلا_تقتلهم #لما_جعلوا #يظهر


ون_الإيمان 

(وعظهم وقل لهم في أنفسهم قولا بليغا) يقول لهم : #إن_أظهرتم_ما #في_قلوبكم_قتلتكم ."

* እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው* የሚለው አንቀፅ ሽርክና ኒፋቅ ማለቱ ነው፡፡ *ከነሱ መሸሽን ሽሽ* (فأعرض عنهم) የሚለው ደግሞ #ኢማንን_ግልፅ_እያደረጉ_ሥለሆነ_አትግደላቸው_ማለቱ ነው፡፡ *እነርሱንም ተዋቸው ገሥጻቸውም፡፡ ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው፡፡ * የሚለው ቃል ደግሞ  #በቀልቦቻቹህ_ውስጥ_ያለውን_ግልፅ_ካደረጋቹህ_ትገደላላቹህ፡፡ " እያላቸው ነው፡፡ 


✅ ይህ ወደጧጉት ተሃኩም ማድረግ ብቻውን ኩፍር አክበር እንዳልሆነና ሙናፊቆቹም ኩፍር የሚወድቅባቸው በቀልባቸው በቋጠሩት እንደሆነ አንቀፁ በደንብ ይገልፃል፡፡ 


፨ ሙፈሲሩ አል-በገዊ እንዲህ ብሏል ፦

ويقول البغوي : 

"( فأعرض عنهم ) أي : عن عقوبتهم وقيل : فأعرض عن قبول عذرهم وعظهم باللسان ، وقل لهم قولا بليغا ، وقيل : هو التخويف بالله ، وقيل : أن توعدهم بالقتل إن لم يتوبوا ، قال الحسن : القول البليغ أن يقول لهم : #إن_أظهرتم #ما_في_قلوبكم #من_النفاق_قتلتم لأنه يبلغ من نفوسهم كل مبلغ"

*ከነሱ ሽሽ(ራቅ)* የሚለው የተፈለገበት እነሱ ከመቅጣት ራቅ ማለት ነው፡፡ በሌላም እንደተባለው *ዑዝራቸውን ከመቀበል ራቅ፡፡ በአንደበትህ ገስፃቸው፡፡ *ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው* የሚለው ደግሞ ይህ በአሏህ እንዲያሥፈራራቸው ነው፡፡ በሌላ እንደተባለው ደግሞ ተውበት ካላደረጉ ፥ ትገድላቸዋለህ እንደማለት ነው፡፡ አል-ሐሰን እንዲህ ብሏል ፦* ስሜት ያለው ቃል* ሲል እንዲህ እንዲላቸው ነው [ በቀልባቹህ ውስጥ ያለ ኒፋቅ ግልፅ ካደረጋቹህ ትገደላላቹህ፡፡ 

ويقول الرسعني الحنبلي : 

፨ ዒዘዲን አርረሥዐኒ አልሃንበሊ  እንዲህ ብሏል ፦

" ከነሱ ሽሽ(ራቅ) * የሚለው አያ ቅጣታቸውን ተውላቸው ማለት ነው፡፡ *ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው፡፡* የሚለው ደግሞ ለነሱ ተናገራቸው ፥ በሐይልም ገስፃቸው፡፡ በነፍሶቻቸው ተፅዕኖ ሊያሳድር የሚችል ግሳፄ አድርግላቸው፡፡* ማለት ነው፡፡ አልሐሰን አልበስሪ እንዲህ ብሏል ፦ "ለነሱ ተናገራቸው ማለቱ  *በቀልቦቻቹህ ያለውን ኒፋቅ ግልፅ ብታደርጉ ትገደላላቹህ* እየተባሉ ነው፡፡

" (فأعرض عنهم ) دع عقوبتهم .

( وقل لهم في أنفسهم قولا بليغا ) : قل لهم وبالغ في وعظهم مبالغة تؤثر في نفوسهم وتبلغ كنه قلوبهم ، قال الحسن البصري - رحمه الله -  المعنى : قل لهم :   #إن_أظهرتم #ما_في_قلوبكم #من_النفاق_قتلتم"


📚ተፍሢር አርረሥዐኒ


፨ ኢብኑ ከሢር እንዲህ ብሏል ፦

ويقول الحافظ بن كثير 

* ከእነሱ ራቅ(ሽሽ) * የሚለው ይህ ማለት በቀልባቸው ውስጥ ባለ ነገር አትጨክንባቸው (ሺዳህ አታሳያቸው)፡፡ ገስፃቸው የሚለው ደግሞ በቀልቦቻቸው ውስጥ ካለ ኒፋቅና የውስጥ ሸር ከልክላቸው፡፡ * እያለ ነው፡፡ 

"ولهذا قال له: (فأعرض عنهم) أي: #لا_تعنفهم #على_ما_في_قلوبهم (وعظهم) أي: #وانههم_على_ما #في_قلوبهم #من_النفاق_وسرائر_الشر"

📚 ተፍሢር ኢብኑ ከሢር


‼️ እዚህ ወሳኝ ነጥብ አለ፡፡ ይህች አንቀፅ የወረደችው እነዚያ ሠዎች በውጣቸው የካዱ እንደነበሩ ለመግለፅ ነው፡፡ ያደረጉት ተሃኩም ወይም ወደጧጉት ሄደው ፍርድ የፈለጉበት ገፅታም #አምነውበት ነበር ሄደው የተፋረዱት፡፡ ግን ያንን ግልፅ አላደረጉም፡፡ ነገርግን ቁርኣን ነው በውስጣቸው ያለውን ኩፍር ለረሡል ሠለሏሁ ወለይሒ ወሠለም ያጋለጠው፡፡ 


፨ ይህ ነው እንግዲህ የቁርኣኑ አንቀፅ አገባብ ፥ ከዕውቀት ባለቤቶች ተፍሢር ጋር ፡፡ እነዚህ ሙናፊቆች በአሏህ ሑክም ላይ ኩራት የሚይዛቸው (ሙስተክቢሪን) ነበሩ፡፡ የጧጉቱንም ህግ ከአሏህ ህግ ያስበልጡ ነበር፡፡ ይህ የዕውቀት ባለቤቶች ያረጋገጡ ሐቅ ነው፡፡ ጃሒሎች ቢስቱትም፡፡ ወደ ጧጉቱ ሄደው የተፋረዱበት ሁኔታም አስቀምጠዋል፡፡ 


‼️ለምሳሌ ኢማም አቡ ጃዕፈር አጥጦበሪ ረሂመሁሏህ ተፍሢሩ ላይ እንዲህ ብሏል ፦

يقول الإمام الطبري رحمه الله في تفسيره الآية :

[ *የልቅናው ባለቤት አሏህ በዚህ ንግግሩ ማለት የፈለገው * አንተ ሙሃመድ ሆይ! በቀልብህ አትመለከትምን* (ألم تر) ልታውቅ ዘንዳ፡፡ ወደእነዚያ ወደአንተ በተወረደው ኪታብ እውነት ብለን ተቀብለናል ብለው የሚሞግቱትን ፥ ወደእነዚያ ካንተ በፊት በወረዱት መፅሃፍ አምነናል ብለው የሚሞግቱትን (አታይምን) ፥ በመካከላቸው በሚፈጠር አለመግባባት ወደጧጉት ሄደው መፋረድን ይፈልጋሉ፡፡ #አሏህ_ይህ_ማለቱ #ወደሚያልቁት እና በንግግሩም እውነት ብሏል ወደሚሉት ፥ ከአሏህ ሁክም ውጪ የእሱን ሁክም ወደሚወዱለት ጧጉት ሄደው ይፈረዳሉ፡፡ በእሱ እንዲክዱ ታዘው ነበር፡፡ እንደሚለው *አሏህ የሚፋረዱበትን ጧጉት ይዞላቸው በመጣው ነገር እንዲያስተባብሉ አዟቸው ነበር፡፡ የአሏህ ትዕዛዝ ተዉ፡፡ የሸይጧን ትዕዛዝ ተከተሉ፡፡ ሸይጧን ደግሞ ሩቅ የሆነ ጥመትን ሊያጠማቸው ይፈልጋል፡፡ ] 


📚ተፍሲር አጥጦበሪ


(قال أبو جعفر: يعني بذلك جل ثناؤه: " ألم تر "، يا محمد، بقلبك، فتعلم = إلى الذين يزعمون أنهم صدقوا بما أنـزل إليك من الكتاب، وإلى الذين يزعمون أنهم آمنوا بما أنـزل من قبلك من الكتب، يريدون أن يتحاكموا في خصومتهم إلى الطاغوت = #يعني إلى #من_يعظمونه_ويصدرون_عن_قوله_ويرضون_بحكمه_من_دون_حكم_الله =" وقد أمروا أن يكفروا به "، يقول: وقد أمرهم الله أن #يكذبوا بما جاءهم به الطاغوتُ الذي يتحاكمون إليه، فتركوا أمرَ الله واتبعوا أمر الشيطان =" ويريد الشيطان أن يضلهم ضلالا بعيدًا) 

፨ እነዚህ ሙናፊቆች የጧጉቱን ህግ የአሏህን ህግ ትተው እሱን ይወዱ ነበር፡፡ እውነተኛ ነው ይላሉ፡፡ ያልቁታልም፡፡ ከአሏህ ሁክም ውጪ በሆነ ሑክም ወዶ መቀበል ደግሞ ኩፍር ነው፡፡ ምክንያቱም ወይ ትክክለኛ ነው ብሎ ማመን ወይ ከአሏህ ሸሪዐ እኩል ማድረግ ፥ ወይ ከአሏህ ሁክም ማሥበለጥ አለ፡፡ 


፨ ይህ የሚያረጋግጥልን የአሽ-ሻጢቢ ንግግር እንመልከት..


يقول الشَّاطبي في الاعتصام : 

" *ወደ እነዚያ እነርሱ በአንተ ላይ በተወረደውና ከአንተ በፊትም በተወረደው አምነናል ወደሚሉት፤ አላየህምን በእርሱ እንዲክዱ በእርግጥ የታዘዙ ሲኾኑ ወደ ጣዖት መፋረድን ይፈልጋሉ፡፡* ልክ እዚጋ እነዚያ ሠዎች በተሃኩሙ አረጋግጠዋል፡፡ ግን መፋረዱ የነሡ ሥሜት በሚገጥም መልኩ እንዲሆን ፈለጉ፡፡ ይህም የሆነ ከሐቅ ስለጠመሙ ፥ ሁሉም ደግሞ መፋረጃ ነው (ልዩነት የለም) ማለታቸው ፥ ከዕብ ቢን አሽረፍ የሚፈርድበትን ወይም ሌሎቹ የሚፈርዱበትን ፥ ያው እንደረሡል ሠለሏሁ ዐለይሒ ወሠለም አምሳያ ነው ብለው ጠረጠሩ (አሰቡ)፡፡ ያላወቁት ነገር ቢኖር የረሡል ሠለሏሁ ዐለይሒ ወሠለም ሁክም ማለት የማይመለስ የሆነው የአሏህ ሁክም ነው፡፡ ከሱ ጋር የሌሎች በአሏህ ሁክም ላይ ካልገጠመ  ሑክሙ ውድቅ ነው (ተመላሽ ነው) ፡፡ ለዚህ አሏህ [ ሸይጧን ሩቅ የሆነ ጥመትን ሊያጠማቸው ይፈልጋል፡፡] ምክንያቱም አንቀፁ የሚጠቁመው *ኢስላም* ውስጥ በገቡ ሠዎች መውረዱን ነው፡፡ 


(وقال تعالى: {ألم تر إلى الذين يزعمون أنهم آمنوا بما أنزل إليك وما أنزل من قبلك يريدون أن يتحاكموا إلى الطاغوت} فكأن هؤلاء قد أقروا بالتحكيم، غير أنهم أرادوا أن يكون التحكيم على وفق أغراضهم زيغا عن الحق، #وظنا_منهم_أن_الجميع_حكم، #وأن_ما_يحكم به كعب بن الأشرف أو غيره #مثل_ما يحكم به النبي صلى الله عليه وسلم، #وجهلوا أن حكم النبي صلى الله عليه وسلم هو حكم الله الذي لا يرد، #وأن_حكم_غيره معه #مردود إن لم يكن جاريا على حكم الله، فلذلك قال تعالى: {ويريد الشيطان أن يضلهم ضلالا بعيدا}، لأن ظاهر الآية يدل على أنها نزلت فيمن دخل في الإسلام)

📚 ኢዕቲሷም ፥ አሽ-ሻጢቢ


፨ ይህ ግልፅ ንግግር ነው፡፡ እነዚያ ሙናፊቆች የአሏህ ሁክምና የሌላው ሁክም እኩኩል አድርገው ያስቧቸው ነበር፡፡ 


እስካሁን ባየነው *የአሏህን ሑክም መተው ብቻውን* ወይም ወደሌላ ሸሪዐ መፈረድ ከኢስላም የሚያስወጣ ወንጀል አይደለም፡፡ ከኢስላም የሚያስወጣ ኩፍር ለመሆኑ ሌሎች ቀሪና (ተዛማጅ የሆኑ) ነገሮች ይፈልጋል፡፡ ለምሳሌ *ሪዷ* ሌላን ሁክም መውደድ ፥ ወይ ከሸሪዐ ህግ ሌላ ሠው ሠራሽ ይሻላል ማለት ፥ ወይ እኩል ናቸው ማለት የመሣሠሉ ነገሮች ተጎራብቶት ከተገኘ ትልቁ ኩፍር ይሆናል፡፡ 

 

፨ አሏህ ወደ ቀጥተኛ መንገድ ይምራን፡፡ ወልሐምዱሊላሂ ረቢል ዐለሚን፡፡

የኢብኑ ተይሚያህ አቋም በተሃኩም ላይ...

  ፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን...