🔖 በአሏህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩህና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ፡፡
በዚህ ሁፍ በአሏህ እርዳታ በመታገዝ ወደ ጧጉት መፋረድ ምን እንደሆነ እና ወደ ጧጉትም መፋረድ ያለው ሁክም እንመለከታለን፡፡ በምን አይነት ሁኔታ ወደ ተሃኩም መፋረድ ኩፍር አክበር የሚሆነው? እናያለን፡፡
🔖 ይህ አንቀፅ የወረደባቸው ሠዎች ክህደት ያገኛቸው ወደ ጧጉት በመፋረዳቸው ብቻ ነውን ወይስ የጧጉትን ሁክም ከአሏህ ሁክም የበለጠ ፥ ወይም እኩል የሆነ ፥ ወይም ኢስቲህላል ያደርጉም ስለነበር ነው ፥ ወይስ በአሏህ ሁክም አይወዱም ነበር?
እዚህ ቦታ ንግግራችን ሁሉ ሊሽከረከርበት የሚችልበትን ሁለት መግቢያ አስቀድመን የምንመለከት ይሆናል፡፡
#የመጀመርያው). በዚህ አንቀፅ ላይ ተሃኩም ያደረጉት ሠዎች ትክክለኛው ተግባራቸው ምን እንደነበረ ማረጋገጥ፡፡
#ሁለተኛው) .እነዚያ ሠዎች በትክክል ይተገብሩ የነበረው #ተግባራቸው ከዑለሞች በማረጋጥ እንመለከታለን፡፡
ይህ አሁን በዝርዝር የምንመለከተው መስዐላ *አሏህ ባላወረደው ነገር መፍረድ* የሚለው ውስጥ ሊካተት የሚችል ነገር ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ሠለፎች ዘንድ እንኳን በተቅኒን ደረጃ ተከስቷል፡፡ በታብዕዮች ዘመን ሙኩስ የተባለን በሸሪዐ የሌለ ህግ አውጥተው ያስተዳድሩ ነበር፡፡ በኒ ኡመዮችን በዚህ ያከፈራቸው አንድም የለም፡፡ ( አንዳንዶች ይህ ሲባል በዘመናችን ያሉ የአሏህን ሁክም የመለሱ ፥ ኢስላማዊ መንግስት ኋላቀርነት ነው የሚሉ ፥ ኢስቲህላልና ሌሎችም ኩፍርያት የሆኑ ነገሮች የሞሉበት *ዲሞክራሲያዊ* ሥርዐት አራማጆችን እንዲሁም በሙሥሊሞች ካፊርን እያገዙ ያሉ ሙርተዶችን በዚህ ርዕስ የሚመደቡ ይመሥላቸዋል፡፡ ነገሮቹ ልዩነታቸው ለማወቅ የዑለሞች ትክክለኛ መንሐጅ ይዘን ራሳችን ከጥመት ተጣሪዎች መጠበቅ ይኖርብናል፡፡
፨ በቀጥታ ወደ አንቀፁ ማብራርያ ስንገባ ልብ ብለን መረዳት ያለብን ነገር ይኖራል፡፡
1ኛ). ተሃኩም ማድረጋቸው የኒፋቃቸው ምልክት እንደነበር
2ኛ). ተሃኩም አድርገው የነበረው የአሏህ ሁክም ከመፈፀም ኩራት ይዟቸው (በኢስቲክባር) እንደነበር እና የአሏህ ሑክምን ወደው የሚቀበሉ ስላልነበሩ ነው ክህደት ላይ የወደቁት..
በመጀመርያ አንቀፁን እናቅርበው፡፡ ትክክለኛ የኩፍራቸው ሁኔታ እንዴት እንደነበረና አሏህም ምን አይነት ሁክም እንደወሠነባቸው እንይ፡፡
፨ አሏህ የሙናፊቆችን ሁኔታ እንዲህ በማለት ይነግረናል፡፡ አስተንትነት እናንብበው፡፡
4:61* ወደ እነዚያ እነርሱ በአንተ ላይ በተወረደውና ከአንተ በፊትም በተወረደው አምነናል ወደሚሉት፤ አላየህምን በእርሱ እንዲክዱ በእርግጥ የታዘዙ ሲኾኑ ወደ ጣዖት መፋረድን ይፈልጋሉ፡፡ ሰይጣንም (ከእውነት) የራቀን መሳሳት ሊያሳስታቸው ይፈልጋል፡፡ *
قال الله تعالى : {ألم ترَ إلى الذين يزعمون أنهم آمنوا بما أنزل إليك وما أنزل من قبلك يريدون أن يتحاكموا إلى الطاغوت وقد أمروا أن يكفروا به ويريد الشيطان أن يضلهم ضلالا بعيدا
4:65 * ለእነርሱም፡- «አላህ ወደ አወረደው (ቁርኣን)ና ወደ መልክተኛው ኑ» በተባሉ ጊዜ መናፍቃን ከአንተ መሸሽን ሲሸሹ ታያቸዋለህ፡፡*
وإذا قيل لهم تعالوا إلى ما أنزل الله وإلى الرسول رأيت المنافقين #يصدون_عنك_صدودا
4:66 * እጆቻቸውም ባስቀደሙት (ጥፋት) መከራ በደረሰችባቸውና ከዚያም «ደግን ሐሳብና ማስማማትን እንጅ ሌላ አልሻንም» በማለት በአላህ የሚምሉ ኾነው በመጡህ ጊዜ እንዴት ይኾናሉ? *
فكيف إذا أصابتهم مصيبة بما قدمت أيديهم ثم جاؤك #يحلفون_بالله_إن أردنا إلا #إحسانا_وتوفيقا ,
* እነዚህ እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፡፡ እነርሱንም ተዋቸው ገሥጻቸውም፡፡ ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው፡፡ *
أولئك الذين يعلم الله #ما_في_قلوبهم #فأعرض_عنهم وعظهم وقل لهم في أنفسهم قولا بليغا}
.................. ሙሉ አንቀፁ ይህ ይመሥላል፡፡ በዚህ አንቀፅ መነሳት የሚኖርባቸው ወሳኝ ነጥቦች እያየን እንቀጥላለን፡፡
1ኛው). አሏህ እንደሚጠቅስልን እነዚህ ሠዎች ፥ አሏህ ካወረደው ኪታብ (ሑክም) ይሸሻሉ፡፡ ይህ ማለት ከአሏህ ሁክም ይሸሻሉ (ኢዕራድ ያደርጋሉ) ማለት ነው፡፡
፨ ኢብኑል ሙንዚር ተፍሢሩ ላይ እንደመጣው ፦
جاء في تفسير إبن المنذر :
1949 - حَدَّثَنَا زكريا، قَالَ: حَدَّثَنَا أَبُو جعفر مُحَمَّد بْن أحمد بْن نصر، قَالَ: حَدَّثَنَا يوسف بْن عدي، قَالَ: حَدَّثَنَا رشدين، عَنْ يونس بْن يزيد، عَنْ عطاء، فِي قول الله جل ثناؤه "{يَصُدُّونَ عَنْكَ صُدُودًا} ، قَالَ: الصدود: الإعراض "
በዚህ ሠነድ ላይ ታብዒዩ ዐጧእ ( ረሂመሁሏህ) * ከአንተ መሸሽን ሲሸሹ ታያቸዋለህ፡፡* (يَصُدُّونَ عَنْكَ صُدُودًا) የሚለው ሲተረጉም *አስ-ሱዱድ* (الصدود) የተባለው መሸሽ ኢዕራድ (الإعراض) ነው ብሏል፡፡ 📚 ተፍሢር ኢብኑል ሙንዚር
፨ ኢብኑ ከሢር ረሂመሁሏህ ተፍሢሩ ላይ እንዲህ አስቀምጧል፡፡
- وفي تفسير ابن كثير
"( يصدون عنك صدودا ) أي : يعرضون عنك #إعراضا_كالمستكبرين عن ذلك."
* " ከአንተ መሸሽን ሲሸሹ ታያቸዋለህ" ( يصدون عنك صدودا ) የሚለው ማለት የተፈለገው * እንደኩራተኞች (كالمستكبرين) በመሆን ካንተ መሸሽን ይሸሻሉ፡፡* ብሎ አስቀምጧል፡፡ እንግዲህ ሙናፊቆቹ ኢስቲክባር (መኩራት) እንደነበረባቸው ግልፅ ሆነ ማለት ነው፡፡
፨ እንደሚታወቀው አል-ኢስቲክባር (والاستكبار) የኢብሊስ ክህደት አይነቶች ሥር የሚገባ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የኢብሊስ ኩፍር ኢስቲክባር (መኩራት) የነበረበት ነው፡፡ እነዚህ ሙናፊቆችም ይህን *ኢስቲክባር* የተጠናወታቸው ነበሩ፡፡ "መፋረድን መተው" ብቻ የሚመለከት ነገር አልነበረም፡፡
-አንድ ሠው በአሏህ ሁክም የዝሙትን ሐራምነት ላይ ኩራት ይዞት ፥ ዝሙት ቢፈፅም ካፊር ይሆናል፡፡ ነገርግን ያለኩራት ዝሙት የፈፀመ እንደሆነ ካፊር አይሆንም፡፡ የነዚህ ሙናፊቆችም " መፋረድን መተዋቸው" ብቻ አልነበረም ለዚህ የዳረጋቸው *ኢስቲክባር* ስለነበረባቸው ነው፡፡
፨ ሙቃቲል ቢን ሡለይማን 📚 ተፍሢር ላይ እንዲህ ይገልፀዋል፡፡
* ከአንተ መሸሽን ሲሸሹ ታያቸዋለህ * (يصدون عنك صدودا) የሚለውን ፥ ማለት የተፈለገበት "አንተ ሙሃመድ ሆይ! ካንተ ውጪ ወደሆነ አካል መሸሽን ይሸሻሉ፡፡ ይህ ያደረጉት በፍርድ ላይ እንዳትበድላቸው በመፍራት ነው፡፡ * 📚 ተፍሢር ሙቃቲል
- وفي تفسير مقاتل بن سليمان
"(يصدون عنك صدودا) يعني يعرضون عنك يا محمد إعراضا إلى غيرك، #مخافة_أن_تحيف_عليهم"
፨ እነዚህ ሙናፊቆች ከረሡል ﷺ በኩል በደል ይደርስብናል ፥ ይበድለናል ብለው በራሳቸው ላይ ይፈሩ ነበር፡፡ ምንም ጥርጥር የሌለው ነገር የኢሥላም ሸሪዐህ ፍትሐዊ እንደሆነና በደል እንደሌለበት የማያምን ሠው ካፊር ነው፡፡
-2ተኛው). አሏህ ስለነዚህ ሙናፊቆች ሲገልፅ ፥ እነሱ በአሏህ ይምሉ ነበር፡፡ እነሱ (በዚህ ተሃኩም ፈልጋ ወደሌላ መሄዳቸው) «ደግን ሐሳብና ማስማማትን እንጅ ሌላ አልሻንም» በማለት ነበር፡፡ አሏህ ሡብሃነሁ ወተዐላ ግን በቀልቦቻቸው የያዙት የደበቁትን ያውቅ ነበር፡፡ ይህ በዋናነት ከሚሠጠን ማሥረጃ መካከል ፥ እነዚህ ሙናፊቆች በውስጣቸው ካለ የተለየ ነገር በውጭ ገፅታቸው ያሳዩ ነበር፡፡ በውስጣቸው ኒፋቅ ነበር፡፡
፨ ኢብኑ ዘመነይን እንዲህ ብሏል ፦
قال ابن زمنين :
(فكيف إذا أصابتهم مصيبة) قال الحسن : وهذا كلام منقطع عما قبله وعما بعده ؛ يقول : (إذا أصابتهم) يعني : #أن_يظهروا_ما_في_قلوبهم_فيقتلهم رسول الله - صلى الله عليه وسلم -
*መከራ በደረሰችባቸውና ከዚያም «ደግን ሐሳብና ማስማማትን እንጅ ሌላ አልሻንም» በማለት በአላህ የሚምሉ ኾነው በመጡህ ጊዜ እንዴት ይኾናሉ* የሚለው ላይ (فكيف إذا أصابتهم مصيبة) "መከራ ባጋጠማቸው ጊዜ እንዴት ይኾናሉ" የሚለው የአሏህ ንግግር ከፊትና ከኋላ ካለው ንግግር የተቋረጠ ነው፡፡ *ባገኛቸው ጊዜ * ሲል በቀልቦቻቸው የደበቁትን ግልፅ ባደረጉ ጊዜ ረሡል ይገድሏቸዋል፡፡ ማለት ነው፡፡
(ثم جاءوك يحلفون بالله إن أردنا إلا إحسانا وتوفيقا) أي :
#إن_أردنا_إلا_الخير .(أولئك الذين يعلم الله ما في قلوبهم) : #من_الشرك_والنفاق}
* ከዚያም «ደግን ሐሳብና ማስማማትን እንጅ ሌላ አልሻንም» በማለት በአላህ የሚምሉ ኾነው በመጡህ ጊዜ እንዴት ይኾናሉ* ማለቱ መልካምን እንጂ ሌላ ፈልግን አይደለም አሉ፡፡ * እነዚህ እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፡፡ እነርሱንም ተዋቸው ገሥጻቸውም፡፡ ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው፡፡ *
📚 ተፍሢር ኢብኑ ዘመነይን
፨ እንደዚሁም ሙናፊቆቹ በውጣቸው ያለው ሌላ ፥ በውጭ ገፅታቸው የሚያሳዩት ሌላ እንደሆነ ከሚጠቁሙት መካከል
وفي تفسير البغوي :
"( أولئك الذين يعلم الله ما في قلوبهم ) من النفاق ، أي : #علم_ان_ما_في_قلوبهم #خلاف_ما_في_ألسنتهم"
[ አል-በገዊ ፦ እንዲህ ብሏል *እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፡፡* ከነፍቅና የተነሳ ይህ በሚለው የተፈለገበት በቀልባቸው የቋጠሩት ፥ በምላሳቸው ከሚሉት ተቃራኒ ነው፡፡
وفي تفسير الحافظ عز الدين الرسعني الحنبلي :
፨ ዒዘዲን አርረሥዐኒ አልሃንበሊ በተፍሲሩ እንዲህ ብሏል ፦
* እጆቻቸው ባስቀደመው (ጥፋት)* ሲል አሏህ #ኒፋቃቸው እና #ወደ_ጧጉት_መፋረዳቸውን_ነው፡፡ *ደግን ሐሳብና ማስማማትን እንጅ ሌላ አልሻንም* ሲሉ ደግሞ ማለት የፈለጉት መልካም ነገር ፥ ሐቅን የሚገጥም ነገር በመፈለግ ነው፡፡ ማለታቸው ነው፡፡ በሌላም እንደተባለው * ከአንተ ውጪ ወደ አለ ሄደን መፋረድ አልፈለግንም በሁለቱ ተከራካሪዎች ዘንድ መልካም ነገርና ማስማማት እንጂ፡፡* ይላሉ፡፡ የአንተን ሑክም ለመቃረን ብለን ወይም ባንተ ፍርድ ወደን የማንቀበል ሆነን አይደለም፡፡ #ይህ_ከነሱ_የሆነ_ውሸት_ነው፡፡ አታይምን አሏህ የሚለውን *እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፡፡* በልቦቻቸው ያለው ሲል ኒፋቅና ኩፍር ፥ እንዲሁም ከደበቁት ተቃራኒ ነገር ግልፅ ማድረጋቸውን ነው፡፡ ]
[( بما قدمت ايديهم ) #من_النفاق_والتحاكم_إلى_الطاغوت .
( إلا إحسانا وتوفيقا ) اي : #خيرا_وطلبا #لما_يوافق_الحق .
وقيل : #ما_اردنا_بالتحاكم إلى غيرك #إلا_إحسانا_وتوفيقا #بين_الخصمين #لا_مخالفة_حكمك #وعدم_الرضى_بقضائك #وذلك_كذب_منهم ، ألا تراه يقول ( أولئك الذين يعلم الله ما في قلوبهم ) يعني #من_الكفر_والنفاق #وإضمارهم_خلاف_ما_يبطنون .}
📚ተፍሢር ዒዘዲን
፨ ሙፈሢሩ ኢብኑ ከሢር ረሂመሁሏህ እንዲህ ብሏል ፦* እነዚህ እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፡፡ እነርሱንም ተዋቸው ገሥጻቸውም፡፡ ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው፡፡ * ሲል አሏህ ማለት የተፈለገው " ወደ አንተ ዑዝራቸውን ያቀርባሉ፡፡ ይምላሉም፡፡ " እኛ ካንተ ውጪ በመሄዳችን ፥ ካንተ ውጪ ወደሆነ አካል መፋረዳችን ደግን ሐሳብንና ማስማማትን እንጂ ሌላ ፈልገን አይደለም ይላሉ፡፡ እንዲሁ በውጪ ገጽታ ለማሥመሠል ብለን እንጂ ከውስጣችን እዛ ያለው ፍርድ አምነንበት አይደለም፡፡ " ይላሉ፡፡
وفي تفسير ابن كثير [ (ثمّ جاءوك يحلفون باللّه إن أردنا إلا إحسانًا وتوفيقًا) أي: يعتذرون إليك ويحلفون : ما أردنا بذهابنا إلى غيرك، #وتحاكمنا_إلى_عداك إلّا إلإحسان والتوفيق ، أي: #المدارة_والمصانعة، #لا_إعتقادا_منا #صحة_تلك_الحكومة،]
፨ እነሡ ውሸታቸውን እኛ የአሏህን ሑክም እንወዳለን ብለው ይሞግታሉ፡፡ በአሏህ ሁክም ወደው የሚቀበሉ አይደሉም፡፡ እንደውም የአሏህ ሁክም ትክክለኝነት አይቀበሉም፡፡
3ተኛው). አሁን ወደ ዋናው ነጥብ መጥተናል፡፡ በመጨረሻም አሏህ ስለነዚህ ሠዎች ሲናገር እንዲህ ነበር ያለው ፦
{فأعرض عنهم وعِظْهم وقل لهم في أنفسهم قولاً بليغاً}
*እነርሱንም ተዋቸው ገሥጻቸውም፡፡ ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው፡፡* አለ አሏህ፡፡
፨ይህ የጌታችን ትዕዛዝ ብቻውን ወደ ጧጉት መፋረድ ብቻውን ኩፍር አክበር ነው ፥ ከኢስላም ያስወጣል የሚሉ ሠዎችን መሠረት ለማውደም በቂ ይሆን ነበር፡፡
፨ ልብ በል ‼️እነዚህ ሙናፊቆች በገሃድ የሠሩት ሥራ [ ከሸሪዐ ውጪ ወደ ሆነ ነገር መፋረድ ብቻ ] ሆኖ ፥ ያለምንም ኢስቲክባር ፥ ኢስቲህላል ኩፍር አክበር ነው ቢባል ኖሮ ፥ አሏህ መልዕክተኛውን (ሠለሏሁ ዐለይሂ ወሠለም) *ኢስቲታባ* እንዲያርጓቸው ያዝ ነበር ወይም ከኩፍር ተውበት እንዲያደርጉ አለበለዚያ እንደገደሉ ያደርግ ነበር፡፡
- የኩፍር አህካሞችን በነዚህ ሠዎች እንዲፈፀም ባደረጉ ነበር ፥ ነገር ግን አሏህ ረሡልን *ተዋቸው ነው ያላቸው ፥ ከነሱ እንዲሸሹ ነው የነገራቸው፡፡ * ምክንያቱ ምንድነው ከተባለ አሏህ ለረሡል ሠለሏሁ ዐለይሒ ወሠለም የነዚህ ሠዎች ውስጣዊ ምንነታቸው አሳወቃቸው፡፡ እነዚህ ሠዎች ወደጧጉት ሲፋረዱ ፥ በጧጉቱ ሁክም ወደው እንደሆነ ፥ የጧጉቱ ሑክም ከአሏህና መልዕክተኛ ሑክም የተሻለ ነው ብሎ እንደሄዱ ወይም ከአሏህ ሁክም እኩኩል ነው ብለው በማሠብ ሄደው እንደተፋረዱ አሳወቃቸው፡፡ ከላይ በውጪ ገፅታቸው የሚያሳዩት በውስጣቸው ካለው የተቃረነ ነበር፡፡ በውኮጣቸው አምቀው የያዙት ነገር ግልፅ ቢያደርጉ ኖሮ የአሏህ መልዕክተኛ በተጋደሏቸው ነበር፡፡ ምክንያቱም *ሙርተድ* ሆነው ነበር እና፡፡
፨ ኢብኑ ዘመነይን እንዲህ ብሏል ፦
قال بن زمنين :
" (أولئك الذين يعلم الله ما في قلوبهم) : #من_الشرك_والنفاق
(فأعرض عنهم) : #فلا_تقتلهم #لما_جعلوا #يظهر
ون_الإيمان
(وعظهم وقل لهم في أنفسهم قولا بليغا) يقول لهم : #إن_أظهرتم_ما #في_قلوبكم_قتلتكم ."
* እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው* የሚለው አንቀፅ ሽርክና ኒፋቅ ማለቱ ነው፡፡ *ከነሱ መሸሽን ሽሽ* (فأعرض عنهم) የሚለው ደግሞ #ኢማንን_ግልፅ_እያደረጉ_ሥለሆነ_አትግደላቸው_ማለቱ ነው፡፡ *እነርሱንም ተዋቸው ገሥጻቸውም፡፡ ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው፡፡ * የሚለው ቃል ደግሞ #በቀልቦቻቹህ_ውስጥ_ያለውን_ግልፅ_ካደረጋቹህ_ትገደላላቹህ፡፡ " እያላቸው ነው፡፡
✅ ይህ ወደጧጉት ተሃኩም ማድረግ ብቻውን ኩፍር አክበር እንዳልሆነና ሙናፊቆቹም ኩፍር የሚወድቅባቸው በቀልባቸው በቋጠሩት እንደሆነ አንቀፁ በደንብ ይገልፃል፡፡
፨ ሙፈሲሩ አል-በገዊ እንዲህ ብሏል ፦
ويقول البغوي :
"( فأعرض عنهم ) أي : عن عقوبتهم وقيل : فأعرض عن قبول عذرهم وعظهم باللسان ، وقل لهم قولا بليغا ، وقيل : هو التخويف بالله ، وقيل : أن توعدهم بالقتل إن لم يتوبوا ، قال الحسن : القول البليغ أن يقول لهم : #إن_أظهرتم #ما_في_قلوبكم #من_النفاق_قتلتم لأنه يبلغ من نفوسهم كل مبلغ"
*ከነሱ ሽሽ(ራቅ)* የሚለው የተፈለገበት እነሱ ከመቅጣት ራቅ ማለት ነው፡፡ በሌላም እንደተባለው *ዑዝራቸውን ከመቀበል ራቅ፡፡ በአንደበትህ ገስፃቸው፡፡ *ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው* የሚለው ደግሞ ይህ በአሏህ እንዲያሥፈራራቸው ነው፡፡ በሌላ እንደተባለው ደግሞ ተውበት ካላደረጉ ፥ ትገድላቸዋለህ እንደማለት ነው፡፡ አል-ሐሰን እንዲህ ብሏል ፦* ስሜት ያለው ቃል* ሲል እንዲህ እንዲላቸው ነው [ በቀልባቹህ ውስጥ ያለ ኒፋቅ ግልፅ ካደረጋቹህ ትገደላላቹህ፡፡
ويقول الرسعني الحنبلي :
፨ ዒዘዲን አርረሥዐኒ አልሃንበሊ እንዲህ ብሏል ፦
" ከነሱ ሽሽ(ራቅ) * የሚለው አያ ቅጣታቸውን ተውላቸው ማለት ነው፡፡ *ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው፡፡* የሚለው ደግሞ ለነሱ ተናገራቸው ፥ በሐይልም ገስፃቸው፡፡ በነፍሶቻቸው ተፅዕኖ ሊያሳድር የሚችል ግሳፄ አድርግላቸው፡፡* ማለት ነው፡፡ አልሐሰን አልበስሪ እንዲህ ብሏል ፦ "ለነሱ ተናገራቸው ማለቱ *በቀልቦቻቹህ ያለውን ኒፋቅ ግልፅ ብታደርጉ ትገደላላቹህ* እየተባሉ ነው፡፡
" (فأعرض عنهم ) دع عقوبتهم .
( وقل لهم في أنفسهم قولا بليغا ) : قل لهم وبالغ في وعظهم مبالغة تؤثر في نفوسهم وتبلغ كنه قلوبهم ، قال الحسن البصري - رحمه الله - المعنى : قل لهم : #إن_أظهرتم #ما_في_قلوبكم #من_النفاق_قتلتم"
📚ተፍሢር አርረሥዐኒ
፨ ኢብኑ ከሢር እንዲህ ብሏል ፦
ويقول الحافظ بن كثير
* ከእነሱ ራቅ(ሽሽ) * የሚለው ይህ ማለት በቀልባቸው ውስጥ ባለ ነገር አትጨክንባቸው (ሺዳህ አታሳያቸው)፡፡ ገስፃቸው የሚለው ደግሞ በቀልቦቻቸው ውስጥ ካለ ኒፋቅና የውስጥ ሸር ከልክላቸው፡፡ * እያለ ነው፡፡
"ولهذا قال له: (فأعرض عنهم) أي: #لا_تعنفهم #على_ما_في_قلوبهم (وعظهم) أي: #وانههم_على_ما #في_قلوبهم #من_النفاق_وسرائر_الشر"
📚 ተፍሢር ኢብኑ ከሢር
‼️ እዚህ ወሳኝ ነጥብ አለ፡፡ ይህች አንቀፅ የወረደችው እነዚያ ሠዎች በውጣቸው የካዱ እንደነበሩ ለመግለፅ ነው፡፡ ያደረጉት ተሃኩም ወይም ወደጧጉት ሄደው ፍርድ የፈለጉበት ገፅታም #አምነውበት ነበር ሄደው የተፋረዱት፡፡ ግን ያንን ግልፅ አላደረጉም፡፡ ነገርግን ቁርኣን ነው በውስጣቸው ያለውን ኩፍር ለረሡል ሠለሏሁ ወለይሒ ወሠለም ያጋለጠው፡፡
፨ ይህ ነው እንግዲህ የቁርኣኑ አንቀፅ አገባብ ፥ ከዕውቀት ባለቤቶች ተፍሢር ጋር ፡፡ እነዚህ ሙናፊቆች በአሏህ ሑክም ላይ ኩራት የሚይዛቸው (ሙስተክቢሪን) ነበሩ፡፡ የጧጉቱንም ህግ ከአሏህ ህግ ያስበልጡ ነበር፡፡ ይህ የዕውቀት ባለቤቶች ያረጋገጡ ሐቅ ነው፡፡ ጃሒሎች ቢስቱትም፡፡ ወደ ጧጉቱ ሄደው የተፋረዱበት ሁኔታም አስቀምጠዋል፡፡
‼️ለምሳሌ ኢማም አቡ ጃዕፈር አጥጦበሪ ረሂመሁሏህ ተፍሢሩ ላይ እንዲህ ብሏል ፦
يقول الإمام الطبري رحمه الله في تفسيره الآية :
[ *የልቅናው ባለቤት አሏህ በዚህ ንግግሩ ማለት የፈለገው * አንተ ሙሃመድ ሆይ! በቀልብህ አትመለከትምን* (ألم تر) ልታውቅ ዘንዳ፡፡ ወደእነዚያ ወደአንተ በተወረደው ኪታብ እውነት ብለን ተቀብለናል ብለው የሚሞግቱትን ፥ ወደእነዚያ ካንተ በፊት በወረዱት መፅሃፍ አምነናል ብለው የሚሞግቱትን (አታይምን) ፥ በመካከላቸው በሚፈጠር አለመግባባት ወደጧጉት ሄደው መፋረድን ይፈልጋሉ፡፡ #አሏህ_ይህ_ማለቱ #ወደሚያልቁት እና በንግግሩም እውነት ብሏል ወደሚሉት ፥ ከአሏህ ሁክም ውጪ የእሱን ሁክም ወደሚወዱለት ጧጉት ሄደው ይፈረዳሉ፡፡ በእሱ እንዲክዱ ታዘው ነበር፡፡ እንደሚለው *አሏህ የሚፋረዱበትን ጧጉት ይዞላቸው በመጣው ነገር እንዲያስተባብሉ አዟቸው ነበር፡፡ የአሏህ ትዕዛዝ ተዉ፡፡ የሸይጧን ትዕዛዝ ተከተሉ፡፡ ሸይጧን ደግሞ ሩቅ የሆነ ጥመትን ሊያጠማቸው ይፈልጋል፡፡ ]
📚ተፍሲር አጥጦበሪ
(قال أبو جعفر: يعني بذلك جل ثناؤه: " ألم تر "، يا محمد، بقلبك، فتعلم = إلى الذين يزعمون أنهم صدقوا بما أنـزل إليك من الكتاب، وإلى الذين يزعمون أنهم آمنوا بما أنـزل من قبلك من الكتب، يريدون أن يتحاكموا في خصومتهم إلى الطاغوت = #يعني إلى #من_يعظمونه_ويصدرون_عن_قوله_ويرضون_بحكمه_من_دون_حكم_الله =" وقد أمروا أن يكفروا به "، يقول: وقد أمرهم الله أن #يكذبوا بما جاءهم به الطاغوتُ الذي يتحاكمون إليه، فتركوا أمرَ الله واتبعوا أمر الشيطان =" ويريد الشيطان أن يضلهم ضلالا بعيدًا)
፨ እነዚህ ሙናፊቆች የጧጉቱን ህግ የአሏህን ህግ ትተው እሱን ይወዱ ነበር፡፡ እውነተኛ ነው ይላሉ፡፡ ያልቁታልም፡፡ ከአሏህ ሁክም ውጪ በሆነ ሑክም ወዶ መቀበል ደግሞ ኩፍር ነው፡፡ ምክንያቱም ወይ ትክክለኛ ነው ብሎ ማመን ወይ ከአሏህ ሸሪዐ እኩል ማድረግ ፥ ወይ ከአሏህ ሁክም ማሥበለጥ አለ፡፡
፨ ይህ የሚያረጋግጥልን የአሽ-ሻጢቢ ንግግር እንመልከት..
يقول الشَّاطبي في الاعتصام :
" *ወደ እነዚያ እነርሱ በአንተ ላይ በተወረደውና ከአንተ በፊትም በተወረደው አምነናል ወደሚሉት፤ አላየህምን በእርሱ እንዲክዱ በእርግጥ የታዘዙ ሲኾኑ ወደ ጣዖት መፋረድን ይፈልጋሉ፡፡* ልክ እዚጋ እነዚያ ሠዎች በተሃኩሙ አረጋግጠዋል፡፡ ግን መፋረዱ የነሡ ሥሜት በሚገጥም መልኩ እንዲሆን ፈለጉ፡፡ ይህም የሆነ ከሐቅ ስለጠመሙ ፥ ሁሉም ደግሞ መፋረጃ ነው (ልዩነት የለም) ማለታቸው ፥ ከዕብ ቢን አሽረፍ የሚፈርድበትን ወይም ሌሎቹ የሚፈርዱበትን ፥ ያው እንደረሡል ሠለሏሁ ዐለይሒ ወሠለም አምሳያ ነው ብለው ጠረጠሩ (አሰቡ)፡፡ ያላወቁት ነገር ቢኖር የረሡል ሠለሏሁ ዐለይሒ ወሠለም ሁክም ማለት የማይመለስ የሆነው የአሏህ ሁክም ነው፡፡ ከሱ ጋር የሌሎች በአሏህ ሁክም ላይ ካልገጠመ ሑክሙ ውድቅ ነው (ተመላሽ ነው) ፡፡ ለዚህ አሏህ [ ሸይጧን ሩቅ የሆነ ጥመትን ሊያጠማቸው ይፈልጋል፡፡] ምክንያቱም አንቀፁ የሚጠቁመው *ኢስላም* ውስጥ በገቡ ሠዎች መውረዱን ነው፡፡
(وقال تعالى: {ألم تر إلى الذين يزعمون أنهم آمنوا بما أنزل إليك وما أنزل من قبلك يريدون أن يتحاكموا إلى الطاغوت} فكأن هؤلاء قد أقروا بالتحكيم، غير أنهم أرادوا أن يكون التحكيم على وفق أغراضهم زيغا عن الحق، #وظنا_منهم_أن_الجميع_حكم، #وأن_ما_يحكم به كعب بن الأشرف أو غيره #مثل_ما يحكم به النبي صلى الله عليه وسلم، #وجهلوا أن حكم النبي صلى الله عليه وسلم هو حكم الله الذي لا يرد، #وأن_حكم_غيره معه #مردود إن لم يكن جاريا على حكم الله، فلذلك قال تعالى: {ويريد الشيطان أن يضلهم ضلالا بعيدا}، لأن ظاهر الآية يدل على أنها نزلت فيمن دخل في الإسلام)
📚 ኢዕቲሷም ፥ አሽ-ሻጢቢ
፨ ይህ ግልፅ ንግግር ነው፡፡ እነዚያ ሙናፊቆች የአሏህ ሁክምና የሌላው ሁክም እኩኩል አድርገው ያስቧቸው ነበር፡፡
እስካሁን ባየነው *የአሏህን ሑክም መተው ብቻውን* ወይም ወደሌላ ሸሪዐ መፈረድ ከኢስላም የሚያስወጣ ወንጀል አይደለም፡፡ ከኢስላም የሚያስወጣ ኩፍር ለመሆኑ ሌሎች ቀሪና (ተዛማጅ የሆኑ) ነገሮች ይፈልጋል፡፡ ለምሳሌ *ሪዷ* ሌላን ሁክም መውደድ ፥ ወይ ከሸሪዐ ህግ ሌላ ሠው ሠራሽ ይሻላል ማለት ፥ ወይ እኩል ናቸው ማለት የመሣሠሉ ነገሮች ተጎራብቶት ከተገኘ ትልቁ ኩፍር ይሆናል፡፡
፨ አሏህ ወደ ቀጥተኛ መንገድ ይምራን፡፡ ወልሐምዱሊላሂ ረቢል ዐለሚን፡፡
No comments:
Post a Comment