፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡
፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን ሹብሃ ሲረጭ እናውቀዋለን፡፡
1). "በአሏህ ሸሪዐ መፍረድ የተወ ሁሉ ይከፍራል" ይላል፡፡
2). "ሙሽሪኮችን መታዘዝ ያለምንም ገበድ (ማለትም ኢስቲህላል ሳይኖርበት) ትልቁ ሽርክ ነው ያከፍራል" ይላል፡፡
እነዚህ ባጢል አመለካከቶች በሼይኹል ኢስላም ላይ ከተናገረው ጋር አገናኝተን መልስ እንሠጣለን፡፡
በዚያ ፅሁፍ ላይ እኔ የሡን ኸዋሪጅነት እንደምገልፅ መናገሬና ያንንም አለማድረጌ ወቅሶኛል፡፡ በርግጥም በርካታ ቦታዎች ላይ የኸዋሪጆች ቢድዐ ደም ሥሩ ገብቶ ናላው እያዞረው እንደሆነ አስረድቼዋለሁ፡፡ አዎ! የኸዋሪጆች መንገድ ይዣለሁ ብሎ እስኪመሠክር አልጠብቀውም፡፡
አሁን ወደ ኢብኑ ተይሚያህ ንግግር እንሂድ፡፡ እኔ የጠቀስኩት የኢብኑ ተይሚያህ አጭር ንግግሩን ለቦታው የሚገጥም ስለነበር እንጂ ሠፋ ያለውን ንግግሩን ለማምጣት አለመፈለጌ አይደለም፡፡ እንደውም ከተባለ ከተባለ አቡ ኢምራን እጅግ ወሳኝ የሆነ የኢብኑ ተይሚያህ ንግግር ዘሎታል፡፡ እኔ እንዲህ ላስቀምጠው...
قال ابن تيمية
[ولا ريب أن من لم يعتقد وجوب الحكم بما أنزل الله على رسوله فهو كافر، فمن استخل أن يحكم بين الناس بما يراه عو عدلا من غير اتباع لما أنزل الله فهو كافر. فإنه ما من أمة الا وهي تأمر بالحكم بالعدل وقد يكون العدل في دينها ما راه أكابرهم، بل كثير من المنتسبين إلى الإسلام يحكمون بعاداتهم التي لم ينزلها الله سبحانه وتعالى ، كسوالف البادية وكأوامر المطاعين فيهم ، ويرون أن هذا هو الذي ينبغي الحكم به دون الكتاب والسنة وهذا هو الكفر]
<< አሏህ በረሡል ላይ ባወረደው ህግ መፍረድ ግዴታ አይደለም ብሎ #የሚያምን ሠው እሱ ካፊር ነው፡፡ በሠዎች መካከል አሏህ ያወረደውን (ህግ) ሳይከተል እሱ ፍትህ ብሎ ባሰበው ነገር መፍረድን #ሃላል_ያደረገ ሠው እሱ ካፊር ነው፡፡ ነገሩ እኮ አንድም ኡማህ የለም በፍትህ መፍረድ የምታዝ ቢሆን እንጂ፡፡ በርግጥ በዲኗ ላይ ፍትህ የሚሉት ነገር አለቆቻቸው የተመለከቱ (ይሆናል ያሉት) ነገር ነው የሚሆነው ፡፡ እንደውም ብዙ ራሳቸውን ወደኢስላም የሚያስጠጉ ሠዎች አሏህ ያላወረደው በሆነ ልማዳቸው ነው የሚፈርዱት፡፡ ለምሳሌ የገጠር ሠዎች የቆየ ባህላቸው በነሱ መካከል ያሉ የሚታዘዟቸው ሠዎች ትእዛዛት ይመሥል፡፡ ይህ ነገር ከአሏህ ኪታብና ሡና ውጪ ሊፈረድበት የሚገባ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ >>
[ فإن كثيرا من الناس #أسلموا ، ولكن مع هذا لا يحكمون إلا بالعادات الجارية لهم التي يأمر بها المطاعون ، فهؤلاء إذا عرفوا أنه لا يجوز الحكم إلا بما أنزل الله فلم يلتزموا ذلك ، #بل_استحلوا أن يحكموا بخلاف ما أنزل الله فهم كفار ، #وإلا كانوا جهالا ، #كمن_تقدم_أمرهم ]
[ ብዙ ሠዎች ወደ ኢስላም ገብተዋል፡፡ ከዚህም ጋር ግን ያቺ አለቆቻቸው የሚያዙበት የሆነው ልማዳው በሆነው ነገር ላይ እንጂ አይፈርዱም፡፡ እነዚህ ሠዎች አሏህ ባወረደው ነገር እንጂ መፍረድ እንደሚይቻል ካወቁ ፣ ያንንም ተግባራዊ ካላደረጉ እንደውም አሏህ ካወረደው ( ህግ ) ውጪ መፍረድ #ሃላል_ካደረጉ እነሱ ካፊሮች ናቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ጃሂሎች ናቸው፡፡ የነሱ ጉዳይ እንዳሳለፍናቸው ሠዎች ጉዳይ ነው፡፡ ]
📚ሚንሃጁ ሡናህ: 130
፨ በነዚህ የኢብኑ ተይሚያህ ንግግሮች ላይ አሏህ ባወረደው ሁክም መፍረድ መተው ብቻ ኩፍር አክበር ነው የሚል መልዕክት አለን? ... እስቲ ንግግሮቹ አንድ በአንድ እንያቸው፡፡
1ኛ). መጀመርያ ላይ ካፊር ይሆናሉ ያላቸው ሠዎች አሏህ ባወረደው ነገር ላይ መፍርድ ግዴታ አይደለም ብለው #የሚያምኑ ናቸው፡፡
2ኛ). ካፊር ያላቸው ሠዎች በሠዎች መካከል ከአሏህ ሌላ በሆነ አመለካከት መፍረድ ሃላል ነው የሚሉ ሠዎች ነው፡፡
3ኛ). ሠዎች ወደኢሥላም ከገቡ በኋላ አሏህ ካወረደው ህግ ውጪ በድሮ ልማዳቸው ይፈርዳሉ አለ፡፡ ታዲያ ኢብኑ ተይሚያህ ከአሏህ ውጪ ባለ ነገር መፍረድ መተዋቸው ብቻ ካፊር ያደርጋቸዋል አለን? በፍፁም...ይኸው ንግግሩ
ويرون أن هذا هو الذي ينبغي الحكم به دون الكتاب والسنة وهذا هو الكفر
" ይህ የነሱ (ልማዳዊ ህጋቸው) ከኪታብና ሡና ውጪ ሊፈርዱበት የሚገባ መሆኑ ያምናሉ፡፡ "
እዚህ ቦታ እነዚህ ሠዎች ኩፍር ላይ የጣላቸው በአሏህ ሁክም አለመፍረዳቸው ብቻ ሳይሆን ካለመፍረዳቸው ጋር በዘልማድ የያዙትን ህግጋት ከአሏህ ኪታብና ከረሡል ሡና ውጪ ሊፈርዱበት የሚገባ አድርገው ያምኑበት ነበር፡፡ በአጭሩ የነሱን ሁክም ከአሏህ ሁክም የተሻለ እንደሆነ ያምኑ ነበር፡፡ ይህ ነው ይህ ነው ኩፍር የሚሆነው፡፡ (هو الذي ينبغي الحكم به دون الكتاب والسنة) ማለታቸው ነው ኩፍር ላይ የሚጥላቸው፡፡
*** ሁለተኛው የኢብኑ ተይሚያህ ንግግር ሥንመለከት ***
1ኛ). ብዙ ሠዎች ወደኢሥላም እንደገቡ ቢገልፅም እነዚህ ሠዎች በአሏህ ኪታብ አይፈርዱም ነበር፡፡ ነገርግን እነዚህ ሠዎች በአሏህ ኪታብ አለመፍረዳቸው ብቻ ካፊር አደረጋቸውን? በፍፁም ! ንግግሩን እንይ..
فهؤلاء إذا عرفوا أنه لا يجوز الحكم إلا بما أنزل الله فلم يلتزموا ذلك ، #بل_استحلوا أن يحكموا بخلاف ما أنزل الله فهم كفار
" እነዚህ (ሠዎች) አሏህ ባወረደው ሁክም እንጂ መፍረድ እንደማይቻል ካወቁ ግን ያንን ተግባር ባያውሉት እንደውም አሏህ ካወረደው ተፃራሪ በሆነ ነገር መፍረድን ሃላል ካደረጉ እነሱ ካፊሮች ናቸው፡፡ "
ኢብኑ ተይሚያህ እነዚህ ሠዎች የሚከፍሩት አሏህ ባወረደው ነገር አለመፍረዳቸው ብቻ ሳይሆን ከአሏህ ህግ ተቃራኒ በሆነ ነገር መፍርድ #ሐላል ነው በማለታቸው እንደሆነ ያስታውቃል፡፡
ስለዚህ አለመፍረድ ብቻው ያከፍራል የሚለው ባጢል ነው ማለት ነው፡፡ ካለመፍረዳቸው ጋር ኢስቲህላል ፣ ኢስቲክባር ፣ ተፍዲል ፣ ጁሁድ የመሣሠሉት ነገሮች ተከትለው ከሆነ ነው የሚከፍረው!
፨ አሁን ወደሌላው የኢብኑ ተይሚያህ ንግግር እንለፍ!
"وَقَالَ تَعَالَى: {فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ حَتَّى يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لَا يَجِدُوا فِي أَنْفُسِهِمْ حَرَجًا مِمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا تَسْلِيمًا} فَمَنْ لَمْ يَلْتَزِمْ تَحْكِيمَ اللَّهِ وَرَسُولِهِ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ فَقَدْ أَقْسَمَ اللَّهُ بِنَفْسِهِ أَنَّهُ لَا يُؤْمِنُ، وَأَمَّا مَنْ كَانَ مُلْتَزِمًا لِحُكْمِ اللَّهِ وَرَسُولِهِ بَاطِنًا وَظَاهِرًا، لَكِنْ عَصَى وَاتَّبَعَ هَوَاهُ، فَهَذَا بِمَنْزِلَةِ أَمْثَالِهِ مِنَ الْعُصَاةِ. وَهَذِهِ الْآيَةُ مِمَّا يَحْتَجُّ بِهَا الْخَوَارِجُ عَلَى تَكْفِيرِ وُلَاةِ الْأَمْرِ الَّذِينَ لَا يَحْكُمُونَ بِمَا أَنْزَلَ اللَّهُ،" {منهاج السنة (٥/١٣١)}
- አላህ እንዲህ ይላል [ በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍፁም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም ]
" በመካከላቸው በተፈጠረ ነገር የአሏህ ና የመልዕክተኛውን ፍርድ በተግባር ያላስገኘ ሠው አሏህ በራሱ እየማለ ያ ሠው አያምን ብሏል፡፡ ነገር ግን የአሏህና የመልዕክተኛው ሁክም በውጩም በውስጡም ተግባራዊ ያደረገ ሠው ነገርግን አመፀ ሥሜቱም ተከተለ ይህ እንደአምሳዮቹ የወንጀል ባለቤት ነው፡፡ ይህ አንቀፅ ኸዋሪጆች እነዚያ አሏህ ባወረደው ነገር የማይፈርዱ መሪዎች ለማክፈር ማሥረጃ አድርገው ተጠቅመውታል፡፡ "
📚 ሚንሃጅ አሥ-ሡናህ 5/131
፨ ከዚህ የሼይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ንግግር የምናገኛቸው ቁምነገሮች ...
1ኛ). በመካከላችን በሚፈጠር ነገር በአሏህና መልዕክተኛው ፍርድ መፍረድ እንዳለብን!
2ኛ). በመካከላቸው በተፈጠረው ነገር በአሏህና በመልዕክተኛው ፍርድ የማይፈርዱ አሏህ እየማለ አያምኑም ብሏል፡፡
3ተኛ). የአሏህና የመልዕክተኛ ሁክምን በውጭም በውስጥ አረጋግጦ ነገርግን ስሜቱን በመከተል ካመፀ ከወንጀለኛ መሆኑ፡፡
4). ኸዋሪጆች አሏህ ባወረደው ነገር የሚፈርዱ መሪዎች በዚህ አንቀፅ ተጠቅመው እንደሚያከፍሩ አይተናል፡፡
፨ ኢብኑ ተይሚያህ በአሏህ ና መልዕክተኛ ፍርድ የማይፈርዱ ሲል ሁሉንም እንዳላካተተ በዚሁ ፅሁፍ መረዳት ይቻላል፡፡ ወይም ደግሞ በአሏህ ኪታብ መፍረድ መተው ብቻ ኩፍር አክበር ቢሆን ኖሮ እነዛ ወንጀለኞቹም ካፊር በተባሉ ፣ ኸዋሪጆቹም ባልተወቀሱ ነበር፡፡
ምክንያቱም ስሜቱ ተከትሎ በአሏህ ሸሪዐ ያልፈረደውና እነዚያ ኸዋሪጆች ያከፈሯቸው መሪዎች ሁሉ [ አሏህ ባወረደው ሸሪዐ የማይፈርዱ] (ومن لم يحكم بما أنزل الله) ናቸው፡፡ ለዚህ ነው ሡረቱል ማኢዳ ዟሂሩ ኩፍር አክበር አይጠቁምም የሚባለው፡፡ አይ ዟሒሩ ኩፍር አክበር የሚል ሠው እንደገና መጥቶ በስሜቱ የፈረደ ፣ በሸሪዐ ያልፈረደ መሪ ፣ በአንድ ሁለት ነጥብ የፈረደ ሠው አይከፍርም ሲል ከሠማኸው የአንቀፁ ዟሒር ዑሙም እንደሆነ ያልተረዳ መሃይም እንደሆነ እወቅ፡፡
፨ ኢብኑ ተይሚያህ ከላይ በተለያየ ንግግሮች ተፍዲል ፣ ወይም ኢስቲህላል ሸርጥ ማድረጉ አሳልፈናል፡፡
፨ ሌላው አል-ሁክም ቢገይሪ ማ አን-ዘለሏህ (الحكم بغير ما أنزل الله) ሼይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ኩፍር ከማይሆኑ ወንጀሎች መድቦታል፡፡ ይኸው ንግግሩ ....
وَأَمَّا الْمَعَاصِي الَّتِي لَيْسَ فِيهَا حَدٌّ مُقَدَّرٌ وَلَا كَفَّارَةٌ كَاَلَّذِي يُقَبِّلُ الصَّبِيَّ وَالْمَرْأَةَ الْأَجْنَبِيَّةَ أَوْ يُبَاشِرُ بِلَا جِمَاعٍ أَوْ يَأْكُلُ مَا لَا يَحِلُّ كَالدَّمِ وَالْمَيْتَةِ أَوْ يَقْذِفُ النَّاسَ بِغَيْرِ الزِّنَا أَوْ يَسْرِقُ مِنْ غَيْرِ حِرْزٍ وَلَوْ شَيْئًا يَسِيرًا أَوْ يَخُونُ أَمَانَتَهُ كَوُلَاةِ أَمْوَالِ بَيْتِ الْمَالِ أَوْ الْوُقُوفِ وَمَالِ الْيَتِيمِ وَنَحْوِ ذَلِكَ إذَا خَانُوا فِيهَا وَكَالْوُكَلَاءِ وَالشُّرَكَاءِ إذَا خَانُوا أَوْ يَغُشُّ فِي مُعَامَلَتِهِ كَاَلَّذِينَ يَغُشُّونَ فِي الْأَطْعِمَةِ وَالثِّيَابِ وَنَحْوِ ذَلِكَ أَوْ يُطَفِّفُ الْمِكْيَالَ وَالْمِيزَانَ أَوْ يَشْهَدُ بِالزُّورِ أَوْ يُلَقِّنُ شَهَادَةَ الزُّورِ أَوْ #يَرْتَشِي_فِي_حُكْمِهِ أَوْ #يَحْكُمُ_بِغَيْرِ_مَا_أَنْزَلَ_اللَّهُ أَوْ يَعْتَدِي عَلَى رَعِيَّتِهِ أَوْ يَتَعَزَّى بِعَزَاءِ الْجَاهِلِيَّةِ أَوْ يُلَبِّي دَاعِيَ الْجَاهِلِيَّةِ إلَى غَيْرِ ذَلِكَ مِنْ أَنْوَاعِ الْمُحَرَّمَاتِ : فَهَؤُلَاءِ يُعَاقَبُونَ تَعْزِيرًا وَتَنْكِيلًا وَتَأْدِيبًا بِقَدْرِ مَا يَرَاهُ الْوَالِي #عَلَى_حَسَبِ_كَثْرَةِ_ذَلِكَ الذَّنْبِ فِي النَّاسِ وَقِلَّتِهِ . #فَإِذَا_كَانَ_كَثِيرًا زَادَ فِي الْعُقُوبَةِ #بِخِلَافِ_مَا_إذَا_كَانَ_قَلِيلًا .)
[ የተወሰነ የሆነ ገደብና ከፋራህ የሌላቸው ወንጀሎች የሚባሉት ህፃንና ባዕድ ሴትን የሚሥም ወይም ያለ ግኑኝነት የሚደባብስ ፣ ወይም ሃላል ያልሆነ ነገር የሚበላ ደም በክት ይመሥል.....] ቀጠለና ለማሳጠር [ በውሸት የሚመሠክር ፣ወይም የውሸት ምሥክርነትን የሚያቀብል ወይም በሁክሙ ላይ ጉቦ የሚቀበል ፣ ወይም ደግሞ #አሏህ_ባላወረድ_ነገር_የሚፈርድ ወይም ከሥሩ ባሉ ሠዎች ድንበር የሚያልፍ...]
፨ በማለት ይዘረዝራል፡፡ እነዚህ የዘረዘራቸው ሁሉ አሏህ ባላወረደው ነገር መፍረድ ጀምሮ ከማያከፍሩ ወንጀሎች የሚመደቡ ናቸው፡፡
፨ ሌላው አንድ ጊዜ ከፈረደ ፣ ሁለት ጊዜ ከፈረደ የሚባለው ፍልስፍና ኢብኑ ተይሚያህ ውድቅ ሲያደርገው እንዲህ ብሏል ፦
فَهَؤُلَاءِ يُعَاقَبُونَ تَعْزِيرًا وَتَنْكِيلًا وَتَأْدِيبًا بِقَدْرِ مَا يَرَاهُ الْوَالِي #عَلَى_حَسَبِ_كَثْرَةِ_ذَلِكَ الذَّنْبِ فِي النَّاسِ وَقِلَّتِهِ . #فَإِذَا_كَانَ_كَثِيرًا زَادَ فِي الْعُقُوبَةِ #بِخِلَافِ_مَا_إذَا_كَانَ_قَلِيلًا
[ እነዚህ ሠዎች {ከላይ የዘረዘራቸው አሏህ ባላወረደው የሚፈርደው ጨምሮ ማለት ነው፡፡ } እነዚህ ሠዎች ለማሥጠንቀቅና ዐደብ ለማሥያዝ ለመቅጣትም ባለሥልጣኑ ይሆናል ባለው ልክ ይቀጣሉ፡፡ ያንን ወንጀል በሠዎች ያለው ብዛትነት እና ትንሽነት ታይቶ ነው፡፡ (ወንጀሉ) ብዙ ከሆነ ትንሽ ከሆነው በተቃራኒ ቅጣቱም ይጨምራል፡፡ ]
፨ ይህ ማሥረጃ ሼይኹል ኢስላም ላይ እንጠለጠላለሁ ለሚል ሠው ሁሉ በአፍ ጢሙ የምትደው ነች፡፡ አሏህ ባወረደው የማይፈርድ ሁሉ #ካፊር ነው የሚሉ ሠዎች ከኢብኑ ተይሚያ መንሐጅ የጠሩ መሆናቸው ታውቃለህ፡፡
ሌላው በአሏህ ባላወረደው ነገር መፍረዱ የፈለገ ያህል ቢጨምር ፣ ቅጣቱ ይጨምራል እንጂ ከኢስላም አያስወጣውም፡፡ ምክንያቱም እንደማንኛውም ወንጀል ነው፡፡
አሏህ ባላወረደው መፍረድ በልቁ ኩፍር አክበር ቢሆን ኖሮ አንድም ጊዜ ፈረደ ፤ ሁለት ጊዜም ፈረደ ኩፍር ይሆን ነበር፡፡ ግን ጂንሡ ወይም መሠረቱ ከወንጀሎች የሚመደብ ሥለሆነ ኩፍር ለመሆኑ የግድ ቀራኢን (ተያያዥ) ነገሮች መኖር አለባቸው፡፡ ኢስቲህላል (በሌላ መፍረድ ሃላል ነው ማለት) ፣ ወይም ጁሁድ (የአሏህ ሁክም መሆኑ በማሥተባበል) ፣ ኢስቲክባር (እንደ ኢብሊስ) ፣ ተፍዲል ( የሌላን ሁክም ከአሏህ ሁክም ይበልጣል ማለት ) የመሳሰሉ ቀሪናዎች ሊኖሩ ግድ ነው፡፡
፨ ታዲያ አሁን አንድ ሠው መጥቶ በየትኛው ድፍረቱ ነው ኢብኑ ተይሚያ በአሏህ ሁክም መፍረድ መተው ብቻው ያከፍራል የሚለው?
፨ አሏህ ወደ ሐቅ ይምራን፡፡ ወልሃምዱሊላሂ ረቢል ዐለሚን፡፡