፨ የኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ) ንግግርና የአቡ ጧኢሽ ጅሕልና !!
❀❀❀❀ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩህና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ❀❀❀❀
በዚህ ፅሁፍ በአሏህ ፍቃድ የኸዋሪጆችን ሹብሃ ያደናገራቸው ሠዎች ከሚያነሷቸው ነጥቦች ፣ ሹብሃ እንኳን የማይባሉ ነገሮች አንዱ የኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ) ንግግር ነው፡፡
እስቲ የአቡ ጧኢሽ ምልከታዎች በከፊሉ እየተመለከትን ያለ ዕውቀቱ የዘባረቀውን እናጥራ፡፡
[ በምናደርገው ውይይት ከሱ የዐረብኛ እውቀት አናሳ መሆን የተነሳ የሸይኽ ሱለይማንን ንግግር ቆርጬ በማምጣት ወቅሶኝ ካበቃ በኋላ ቻናሉ ላይ በሚያሳፍር ሁኔታ የኢብን አል ቀይምን ንግግር ቆራርጦ አመጣና ኢብን አል ቀይም እንደራሱ የተጣመመ አመለካከት ያላቸው በማስመስል ሰውን
ሊያጭበረብርበት ሞከረ። ] ይላል አቡ ኢምራን (አቡ ጧኢሽ)፡፡
መልስ ፦ እዚህ ቦታ ሁለት ነገሮች አነሳለሁ፡፡ አንደኛው እኔን በዐረብኛ እውቀት ማነስ መኮነኑ ሲሆን በእርግጥም እኔ በዐረብኛ የመጠቀ እውቀት የለኝም፡፡ ነገርግን ኑሱሶች የምረዳበት ያህል ግን አውቃለሁ፡፡ አልሃምዱሊላህ፡፡ ወደፊትም በደንብ እማራለሁ፡፡ ነገር ግን አቡ ኢምራን አንድ የአረብኛ ቋንቋ ገና ጀማሪ የሆነ ተማሪ ሠው እንኳን የማይሳታቸው ስህተቶች በርካታ ቦታ ይሳሳታል፡፡ ለምሳሌ የሠዎች ሥም ሲፅፍ እንዲህ ነው፡፡
عبد الله ابن صالح ابن محمد ابن محمد
• እንግዲህ አጁሩሚያህ የሞጠለ ሠው በዚህ ሁኔታ ፅሁፍ ይፅፋል ብዬ አልጠብቅም፡፡ በሁለት ዐለመይን መካከል አሊፍ ስትወድቅ አትፃፍም፡፡ የምትጻፈው የመጀመርያ ሠጥር ላይ ካገኘናት ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ማሥተካከል የማያውቅ ሙቀት የሞላው ጃሂል እከሌ ዐረብኛ አያውቅም ሲል ያሳፍራል፡፡ እኔ በራሴ በዐረብኛ ብዙ እውቀት የለኝም፡፡ እንዲህ የወረደ ነገር ግን ኢንሻ አሏህ አልሳሳትም፡፡ ደሞ አንዴ ቢሆን ተሳስቶ ነው ትላለህ ሲደጋገምስ?
عبد الله بن صالح بن محمد بن محمد....
እያልክ መፃፍ ይኖርብሃል፡፡ እኛ ዐረብኛ ከሚያስተምሩን ሼይኾች የተማርነው ይህ ነው፡፡
• ሁለተኛው ፦ የኢብኑል ቀይም ንግግር አሳስቶ የተረጎመበት ሲሆን ይህ ወደኋላ እንመለከተዋለን፡፡
- በመቀጠል የኢማም ኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ ንግግር አመጣውና እንዲህ አለ [ አቡ ሙስሊም ይህን የኢብን አል ቀይም ንግግር አልተረጎመውም እንዳለ ነው
ቁጭ ያደረገው ምክንያቱም ከተረጎመው አቂዳዬ ብሎት የያዘውን ያፈርስበታልና ነው፡፡ ] ይላል፡፡
መልስ ፦ እኔ የኢብኑል ቀይም ንግግር ያልተረጎምኩት ዐቂዳዬ ስለሚፃረር አይደለም፡፡ ዐቂዳዬ የሚፃረር ነገር በዐረብኛ ስላስቀመጥኩት ምን ይጠቅመኛል? እኔ ዐረብኛ አላውቅም ቢባል እንኳን በቻናሌ ዐረብኛ የሚያውቁ አሉ! የዚህ ልጅ ንግግሮች እኮ መልስ ሊሰጣቸው ቀርቶ መሳሳቂያ ናቸው፡፡ እስቲ የኢብኑል ቀይም ንግግር የማን ዐቂዳ እንደሚያወድም እናያለን፡፡
[ ለማንኛውም ዋናው የአቡ ሙስሊም ቅጥፈት ኢብን አል ቀይም ይህን ንግግር ከማስቀመጣቸው በፊት የተናገሩትን ነገር መተው ነው። ይህን ንግግር ከመናገራቸው በፊት ሸይኹ ያስቀመጡት ገለፃ አቡ ሙስሊም ወደ ግሩፕ ሊወያየኝ የመጣበትን አመለካከት እንዳለ ውድቅ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ በሰው ላይ የሚቀጥፍ መሆኑንም የሚያጋልጥ ነው። ] ይላል፡፡
መልስ ፦ እኔ ያቀረብኩት ንግግር ኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ የተለያዩ አመለካከቶች ያቀራባቸውን ንግግሮች ከጨረሰ በኋላ እሱ ዘንድ ትክክለኛውን አቋም ብሎ የተናገረውን ነው፡፡ ሌሎቹ ንግግሮች የኢብኑል ቀይም አቋም የሚገልፁ ሥላልሆኑ [ የኢብኑል ቀይም አቋም ይህ ነው] ብዬ ላቀርብ አልችልም፡፡ ነገርግን አጠቃላይ በቦታው የሠፈረው ነገር እያወራሁ ቢሆን ኖሮ የሌሎቹ ንግግር ለምን ተውከው ያስብላል፡፡ እኔ ግን ያደረግኩት የራሱ የኢብኑል ቀይም አቋም ነው ያመጣሁት ሥለዚህ ትክክል ነኝ ምንም ቅጥፈት የለውም፡፡
• ሌላው ኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ ከንግግራቸው ቀድሞ ያመጧቸው ሃሳቦች የኔን አመለካከት ውድቅ የሚያደርጉ መሆናቸው ይናገራል፡፡ እዛ ጋ ያሉ ንግግሮች እኮ ትክክል አይደሉም ብለው የተናገሩት ራሳቸው ኢብኑል ቀይም ናቸው፡፡ አንባቢ ግራ እንዳይጋባ ሁሉም ንግግራቸው እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ፡፡
.................................................................
📚 [ መዳሪጁ ሣሊኪን ] 1/ ገፅ 516-520 የኢማም ኢብኑል ቀይም ንግግር ከገጽ:516 ይጀምራል፡፡ የኢማም ኢብኑል ቀይም ንግግር በዚህ ምልክት 👉【】 ውስጥ ብቻ አስቀምጣለሁ፡፡ ሌላው የኔ ማብራርያ ነው፡፡
ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ) የተለያዩ ወንጀሎችን ጠቅሰው እነዚህ ተውበት ሊደረግባቸው የሚገቡ ነጥቦች ናቸው በማለት የተለያዩ ወንጀሎችን ዘረዘሩ፡፡ እንዲህም አሉ ፦
【فأما الكفر، فنوعان : كفر أكبر وكفر أصغر 】
【ኩፍር (ክህደት) ሁለት አይነት ነው፡፡ ትልቁ ከህደት (ኩፍር አክበር) እና ትንሹ ክህደት (ኩፍር አስገር) ናቸው፡፡ 】
እንግዲህ አሁን ኢብኑል ቀይም የኩፍር አይነቶች ሊነገርን ነው፡፡ ከዚያ መካከል በቁርኣን "አሏህ ባወረደው ነገር የማይፈርዱ" (من لم يحكم بما أنزل الله) የሚለው ነጥብ ከኩፍር አክበር ይመድበዋል ወይስ ከኩፍር አስገር ይመድበዋል? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ እንቀጥል...
【فالكفر الأكبر: هو الموجب للخلود في النار.
والأصغر: لاستحقاق الوعيد دون الخلود ،كما في قوله تعالى وكان مما يتلى فنسخ لفظه « لا ترغبوا عن آبائكم فإنه كفر بكم» وقوله في الحديث صحيح «اثنتان في أمتي، هما بهم الكفر ، الطعن في النسب والنياحة»】
【ትልቁ ኩፍር የሚባለው ፦ በእሳት ውስጥ መዘውተርን ግድ የሚያደርግ ኩፍር ነው፡፡ ትንሹ ኩፍር ደግሞ በእሳት ከመዘውተር ውጪ (ባነሰ) ለዛቻ የሚዳርግ ነው፡፡ አሏህ በንግግሩ እንዳለው ይህ ንግግሩ የሚነበብ ነበር ከዚያ ቃላቶቹ ተሽረዋል፡፡ "ከአባቶቻቹህ አትሽሹ ይህ በናንተ ላይ ኩፍር ነው፡፡" ሶሂህ በሆነ ሃዲስ ደግሞ " ሁለት ነገሮች በህዝቦቼ ውስጥ በነሱ ላይ ኩፍር ናቸው፡፡ በዘር ማነወርና በሟች ላይ እያለቀሱ መግጠም (ሙሾ)፡፡ 】
፨ ከዚህ የኢብኑል ቀይም ንግግር የምንረዳው ኩፍር ሁለት አይነት ነው፡፡ ትልቁና ትንሹ፡፡ አሁን ትንሹ ኩፍር የሆኑ ነገሮች እየዘረዘሩ ነው፡፡ በሸሪዐችን በዟሂር "ኩፍር" በሚል ቃል ተጠርተው ግን ትንሹ ኩፍር የሆኑ ነገሮች እየዘረዘሩ ነው፡፡ ትንሹ ኩፍር የተባሉ ነገሮች ጠቅሰው ከጨረሱ በኋላ ትልቁ የተባሉ ነገሮች ያመጣሉ፡፡ እንቀጥል...
【وقوله في سنن: « من أتى امرأة في دبرها فقد كفر بما أنزل على محمد صلى الله عليه وسلم» وفي الحديث الآخر: «من أتى كاهنا، فصدقه بما يقول، فقد كفر بما أنزل على محمد صلى الله عليه وسلم»، وقوله: «لا ترجعوا بعدي كفارا يضرب بعضكم رقاب بعض】
【የረሡል ﷺ ንግግር በሡነኖች ውስጥ የተዘገበ እንዲህ ይላል ፦ "ሴት ልጅን ከኋላዋ በኩል የተገናኛት በሙሃመድ ﷺ ላይ በወረደው ክዷል፡፡ በሌላ ሃዲስ ደግሞ " ጠንቋይ ዘንድ የመጣ በሚናገረውም ነገር እውት ነው ያለ በርግጥም በሙሃመድ ﷺ ላይ በወረደው ክዷል፡፡" ሌላም የረሡል ንግግር " ከኔ በኋላ ከፊላቹህ የሌላውን አንገት የሚመታ ካፊር ወደ-መሆን አትመለሱ 】📚 [ መዳሪጁ ሣሊኪን ] 1/ ገፅ 518
፨ እንግዲህ ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ) ሸሪዐህ ኩፍር በማለት ቢገልፃቸውም ሐቂቃቸው ግን ትንሹ ኩፍር የሆኑ ነገሮች እየገለፁ ነው፡፡ አሁን ደግሞ እሳቸው እዚሁ ቦታ " አሏህ ባወረደው ነገር የማይፈርዱ" (من لم يحكم بما أنزل الله) የሚለው አንቀፅ ከትንሹ ኩፍር ዝርዝር ውስጥ በማሥቀመጥ እንዲህ ብለዋል...
【وهذا تأويل ابن عباس وعامة أصحابه في قوله تعالى " ومن لم يحكم بما أنزل الله فأولئك هم الكافرون" قال ابن عباس: ليس بكفر ينقل عن الملة، بل إذا فعله فهو به كفر وليس كمن كفر بالله واليوم الآخر. وكذلك قال طاووس. وقال عطاء: هو كفر دون كفر، وظلم دون ظلم وفسق دون فسق】
【ይህ (ኩፍር አስገር) የሚለው [ አሏህ ባወረደው ነገር የማይፈርዱ እነዚያ ካፊሮች እነሱ ናቸው፡፡] በሚለው የቁርኣን አንቀፅ ላይ የኢብኑ ዐባስ እና #የአጠቃላይ_ባልደረቦቹ ተፍሲር ነው፡፡ ኢብኑ ዐባስ እንዲህ አለ "ከኢሥላም የሚያስወጣ ኩፍር አይደለም፡፡ እንደውም ይህ ሥራ የሠራ ጊዜ በሡ ላይ ኩፍር ይሆንበታል፡፡ ይህ በአሏህና በመጨረሻው እንደመካድ አይደለም፡፡ ልክ እንደዚሁ ጣውውስ ብሏል፡፡ ዓጧእ ቢን ረባህ እንዲህ ብሏል "ኩፍሩን ዱነ ኩፍር ፣ ዙልሙን ዱነ ዙልም ፣ ፊስቁን ዱነ ፊስቅ】
፨ አሁን አቡ ኢምራን (አቡ ጧኢሽ) በጅህልናው ለሚዘባርቃቸው ነገሮች ኢብኑል ቀይም መልስ እየሠጡ ነው፡፡ ምን ለምሣሌ ብትሉኝ...
1ኛ). አቡ ጧኢሽ በተለያዩ ዝባዝንኬ ፅሁፎቹ የኢብኑ ዐባስ ተፍሢር ኩፍር አክበር ያመለክታል ሲል ሲፅፍ ነበር፡፡ ይኸው ኢብኑል ቀይም ኢብኑ ዐባስም ሆነ አጠቃላይ የኢብኑ ዐባስ ባልደረቦቹ ይህች አንቀፅ *ኩፍር አስገር* ታመለክታለች ብለው ያምኑ እንደነበር ይገልፃል፡፡ ሥለዚህ የዚህ ጧኢሽና የኢማሙ መንሐጅ ለየቅል ነው፡፡
2ኛ). የኢብኑል ቀይም ንግግር የአቡ ሙሥሊሥ አካሄድ ውድቅ ያደርጋል ሲል ነበር በተቃራኒው ኢብኑል ቀይም ይህን አንቀጽ ከኩፍር አስገር ዝርዝር ውስጥ አስቀምጠውታል፡፡ እሳቸውም የበለጠ ይጠቅሱታል፡፡ እንመጣበታለን፡፡
• እስቲ አሁን ኢማም ኢብኑል ቀይም ኺላፍ ብሎ ያመጣቸው ነገሮች እንያቸው ከዚያም የአቡ ጧኢሽ ፍልስፍና እናያለን፡፡ በዚህ ምልክት【 】የኢማም ኢብኑል ቀይም ነቅል ነው የማስቀምጠው ...እንቀጥል፡፡
【ومنهم من تأول الآية على ترك الحكم بما أنزل الله جاحدا له ، وهو قول عكرمة وهو تأويل مرجوح، فإن نفس جحوده كفر سواء حكم أو لم يحكم】
【ከነሡ መካከል አንቀፁን አሏህ ባወረደው ነገር ሁክሙን በማሥተባበል መፍረድ የተወን ሠው ያመልክታል ብለው የፈሠሩ አሉ፡፡ ይህ የዒክሪማህ ንግግር ነው፡፡ የሱ ተፍሲርም ሚዛን የማይደፋ ተፍሲር ነው፡፡ ማሥባበል ራሱ (አሏህ ባወረደው) ኩፍር ነው፡፡ ቢፈርድም ባይፈርድም እኩል ነው፡፡】
፨ ይህ የኢክራማህ ንግግር ሐቂቃው ለተረዳው ሠው የኢማም ኢብኑል ቀይም ንግግር አይጠፋውም፡፡ ይህ አንቀፅ በልቁ የተቀመጠና ዟሒሩ ሲታይ ዑሙም (ጥቅል መልዕክት) የሚሠጥ ነው፡፡ ስለዚህ ዟሒሩ በአንድ ጉዳይ ላይ የተገደበ አይደለም፡፡ ነገርግን ሠበቡ ኑዙሉ ላይ አይሁዶች የአሏህን ሁክም ጀህድ አላደረጉም ለማለት ነው ከተባለ ይህ ባጢል ነው ምክንያቱም በንግግሩ ላይ ስለዚያ ጉዳይ ጭራሽ አላነሳም፡፡ አይሁዶች ጀህድ አላደረጉም ሁክም የተወ ብቻ ይከፍራል ቢል ኖሮ ኢብኑል ቀይም የአቡ ጧኢሽ ዐቂዳ የሚያድመውን አቋማቸው ግልጽ ባላደረጉ ነበር፡፡ ሌላኛው ኺላፍ ያሉት ንግግር እንይ ...
【 ومنهم من تأولها على ترك الحكم بجميع ما أنزل الله: قال ويدخل في ذلك الحكم بالتوحيد والإسلام. وهذا تأويل عبد العزبز الكناني. وهو أيضا بعيد، إذ الوعيد على نفي الحكم بالمنزل ، وهو يتناول تعطيل الحكم بجميعه وببعضه】
【ከነሱም መካከል አጠቃላይ አሏህ ባወረደው ነገር መፍረድ የተወ ተፈልጎበት ነው ብሎ የፈሠረ አለ፡፡ እንዳለውም " በዚህ ውስጥ በተውሒድና በኢስላም መፍረድም ይካተታል" ብሏል፡፡ ይህ የዐብዱልዐዚዝ አል-ኪናኒ ተፍሢር ነው፡፡ ይህ ራሱ የራቀ ነው፡፡ በወረደው (ሸሪዐ) ሑክምን ውድቅ በማድረግ የመጣው ዛቻ ባጠቃላይ ሁክሞች ውድቅ ማድረግም ሆነ በከፊሎቹ አካቶ የሚይዝ ነው፡፡ 】
፨ ኢብኑል ቀይም ይህን ተፍሢር ውድቅ ያደረገበት ምክንያቱ አል-ኪናኒ እንዳለው አጠቃላይ ነገሮች ላይ መፍረድ ሲተው ነው የሚከፍረው የሚል አቋም ሲያንፀባርቅ ፣ ኢብኑል ቀይም ደግሞ አንቀጹ ላይ የተቀመጠው ዛቻ አጠቃላይ ነገሮች ላይ መፍረድ የተወ ብቻ ሳይሆን ከፊል ነገሮችም ላይ ሁክምን ውድቅ ያደረገ ያክታትል እያለ ነው፡፡ አሁንም ኢብኑል ቀይም የአንቀፁ ዑሙም መልዕክት አስረግጦ እየገለፀ ነው፡፡ ሌላኛው እንቀጥል...
【ومنهم من تأولها على الحكم بمخالفة النص تعمدا من غير جهل به ولا خطأ في تأويل، حكاه البغوي عن علماء عموما】
【ከነሱ መካከል እያወቀ ጅህልና ሳይኖርበት በተዕዊል ላይ ሳይሳሳት የወህይ ማሥረጃዎችን በመቃረን ፍርድ መሥጠት ላይ የፈሠረው አለ፡፡ ከአጠቃላይ ዑለማዎች አልበገዊ አስተላልፎታል፡፡ 】
፨ ይህ የአል-በገዊ ተፍሢር ኢብኑል ቀይም እዚሁ ቦታ ውድቅ ሳያደርገው አልፎታል፡፡ ስለዚህ እንቀጥል ኺላፍ ብሎ ያመጣቸውን ...
【 ومنهم من تأولها على أهل الكتاب. وهو قول قتادة والضحاك وغيرهما. وهو بعيد خلاف ظاهر اللفظ فلا يصار عليه 】
【ከነሱ መካከል በመፅሃፍ ባለቤቶች ላይ የፈሠረው አለ፡፡ ይህ የቀታዳህ ፣ የአድዶሃክ የሌሎችም አቋም (ንግግር) ነው፡፡ ይህ ራሱ የራቀና በዟሒር ከሚታየው ቃል የሚፃረር ነው፡፡ ወደዚህ አቋም አይኬድም፡፡ 】
፨ በዚህ የኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ ንግግር ቀታዳና ዶሃክ እንዲሁም ሌሎችም ንግግር የአንቀፁ ዟሂር አህሉል ኪታቦች የተገደበ እንዳልሆነ ያስቀምጣሉ፡፡ ይህ ሁሉም መረዳት ያለበት ነገር ነው፡፡ ሠበበ-ኑዙሉ አይሁዶች ላይ የወረደ መሆኑ ሁሉም ያውቃል፡፡ እዚህ ጋር ኢብኑል ቀይም የተቃወሙት የአንቀጹ ዟሒር ዑሙም ነው ነው፡፡ የተገደበ አይደለም፡፡ (خلاف ظاهر اللفظ) በማለት ኢብኑል ቀይም ያስቀምጣል፡፡ ይህ ሃቅ ነው ዟሒሩ አህሉል ኪታብ ላይ የተገደበ አይደለም፡፡ እንቀጥል ...
【 ومنهم من جعله كفرا ينقل عن الملة】
【 ከነሱ መካከል ከኢሥላም የሚስወጣ ኩፍር ያደረገው አለ፡፡ ]
፨ እዚህ ቦታ ኢብኑል ቀይም ይህ ንግግር ማን እንደተናገረ አላስቀመጠም፡፡ እንደዚህ የሚሉ እንዳሉ ግን በልቁ ነገረን፡፡ ነገርግን የኢብኑል ቀይም አቋም ይህ እንዳልሆነ በመቀጠል ራሱ ኢብኑል ቀይም ወስ-ሶሂሁ (وصحيح) ትክክለኛ አቋም በማለት አስቀምጧል እናየዋለን፡፡ ትክክለኛው አቋም ብሎ ማሥቀመጡ ከላይ ያሉ የሃሳብ ልዩነቶች ኢብኑል ቀይም እንዳልተቀበላቸው ማሳያ ነው፡፡
የደውላው አቡ ጧኢሽ እንዲህ ብሎ ነበር ፦ [ እኔ ይህች አያ ኩፍር አክበር ነች በማለቴ በተደጋጋሚ ይህ የኸዋሪጅ እንጂ
በጭራሽ የአህሉ ሱና አቋም አይደለም ሲለኝ ነበር] ብሏል፡፡
መልስ፦ ይህ አንቀፅ እንደአገባቡ ነው የሚፈሠረው ሁሌም የምለው ይህ ነው፡፡ ዟሒሩ ጥቅል መልዕክት ሥላለው ኩፍር አስገር የሚጠቁም ሲሆን ፣ አንቀፁ እንደወረደበት ሠበብ ከታየ ግን የአሏህን ሑክም ጀህድ ስላደረጉ አይሁዶች ነውና ኩፍር አክበር ነው፡፡ ይህ ነው ንግግሬ፡፡ አንተ እኮ የአንቀፁ ዟሂር ኩፍር አክበር ነው ትላለህ ይህ የኸዋሪጆች ዐቂዳህ እንደሆነ እኔ ሳይሆን ያስቀመጥኩት የአህሉ ሡና ዑለሞች ናቸው፡፡ ይኸው ንግግራቸው ላቅርብ..
❀ አቡል ሙዞፈር አሥ-ሠምዐኒ ረሂመሁሏህ በተፍሢሩ እንዲህ አለ ፦
ﻗﺎﻝ ﺃﺑﻮ ﺍﻟﻤﻈﻔﺮ ﺍﻟﺴﻤﻌﺎﻧﻲ ﻓﻲ ﺗﻔﺴﻴﺮﻩ [ /2 42 ] : ﺍﻋﻠﻢ ﺃﻥ ﺍﻟﺨﻮﺍﺭﺝ ﻳﺴﺘﺪﻟﻮﻥ ﺑﻬﺬﻩ ﺍﻵﻳﺔ ﻭﻳﻘﻮﻟﻮﻥ ﻣﻦ ﻟﻢ ﻳﺤﻜﻢ ﺑﻤﺎ ﺃﻧﺰﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻬﻮ ﻛﺎﻓﺮ ﻭﺃﻫﻞ السنة ﻻ ﻳﻜﻔﺮﻭﻥ ﺑﺘﺮﻙ ﺍﻟﺤﻜﻢ. ﺍﻫـ
【እወቅ! ኸዋሪጆች በዚህ አንቀፅ ላይ ማሥረጃነት ይጠቀማሉ፡፡ አሏህ ባወረደው ነገር ያልፈረደ ካፊር ነው ይላሉ፡፡ #አህሉ_ሡናዎች ግን ሁክምን በመተው ብቻ #አያከፍሩም፡፡】
፨ ይህ የአህሉ-ሡና ዑለሞች ኢጅማዕ ነው፡፡ አቡ ጧኢሽና ጓደኞቹ ከዚህ በተቃራኒ ሁክም መተው ብቻ ያከፍራል ይላሉ፡፡ ታዲያ እኔ ነኝ እንዴ ኸዋሪጅ ያልኩህ ራስህ ኸዋሪጅ ሆነህ መጣህብን እንጂ... ሌላም ተመልከቱ
ኢብኑ ዐብዱልበር [ አት-ተምሂድ 16/17]
ﻗﺎﻝ ﺍﺑﻦ ﻋﺒﺪ ﺍﻟﺒﺮ ﻓﻲ ﺍﻟﺘﻤﻬﻴﺪ [ 16 /17 ] : ﻭﻗﺪ ﺿﻠﺖ ﺟﻤﺎﻋﺔ ﻣﻦ ﺃﻫﻞ ﺍﻟﺒﺪﻉ ﻣﻦ ﺍﻟﺨﻮﺍﺭﺝ ﻭﺍﻟﻤﻌﺘﺰﻟﺔ ﻓﻲ ﻫﺬﺍ ﺍﻟﺒﺎﺏ ﻭﺍﺣﺘﺠﻮﺍ ﺑﺂﻳﺎﺕ ﻟﻴﺴﺖ ﻋﻠﻰ ﻇﺎﻫﺮﻫﺎ ﻣﺜﻞ ﻗﻮﻟﻪ ﻋﺰ ﻭﺟﻞ : } ﻭﻣﻦ ﻟﻢ ﻳﺤﻜﻢ
ﺑﻤﺎ ﺃﻧﺰﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﺄﻭﻟﺌﻚ ﻫﻢ ﺍﻟﻜﺎﻓﺮﻭﻥ {. ﺍﻫـ
【በዚህ ርዕስ ላይ በርግጥም ከቢድዐ ባለቤት የሆኑ ጀመዐዎች ጠመዋል ፤ ኸዋራጆችና ሙዕተዚላዎች፡፡ በዟሂር ትርጉሟ በማትያዝ አንቀፅ ላይ ማሥረጃን አደረጉ፡፡ ለምሳሌ "አሏህ ባወረደው ነገር የማይፈርዱ እነዚያ ከሃዲዎች እነሱ ናቸው፡፡ " የሚለው አንቀፅ፡፡】
፨ ይኸው በግልፅ ኸዋሪጆች አንቀፁ በዟሂሩ ይፈስሩት ነበር፡፡ አቡ ጧኢሽም እያደረገ ያለው ይኸው ነው፡፡ እስቲ በሱ መንሃጅ ላይ ነኝ የሚለው ኢብኑ ተይሚያህ የሚለው እንይ...
ﻭﻗﺎﻝ ﺷﻴﺦ ﺍﻹﺳﻼﻡ ﺍﺑﻦ ﺗﻴﻤﻴﺔ ﻓﻲ ﻣﻨﻬﺎﺝ ﺍﻟﺴﻨﺔ [ 5 / 131 ] : } ﻓﻼ ﻭﺭﺑﻚ ﻻ ﻳﺆﻣﻨﻮﻥ ﺣﺘﻰ ﻳﺤﻜﻤﻮﻙ ﻓﻴﻤﺎ ﺷﺠﺮ ﺑﻴﻨﻬﻢ .... { ﻭﻫﺬﻩ ﺍﻵﻳﺔ ﻣﻤﺎ ﻳﺤﺘﺞ ﺑﻪ ﺍﻟﺨﻮﺍﺭﺝ ﻋﻠﻰ ﺗﻜﻔﻴﺮ ﺍﻟﻮﻻﺓ ﺍﻟﺬﻳﻦ ﻳﺤﻜﻤﻮﻥ ﺑﻐﻴﺮ ﻣﺎ ﺃﻧﺰﻝ ﺍﻟﻠﻪ. ﺍﻫـ
【በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ...ድረስ አያምኑም" ይህ አንቀፅ ኸዋሪጆች አሏህ ባወረደው ነገር የማይፈርዱ መሪዎችን ለማክፈር ለማሥረጃነት ይጠቀሙበታል፡፡ 】
፨ ኢብኑ ተይሚያህ አሏህ ባወረደው ነገር የማይፈርዱ ሙስሊም መሪዎች እንዳሉ ጭምር እየጠቆመ ነው፡፡ አቡ ጧኢሽ ደግሞ የማይፈርዱ ሁሉ ካፊር ነው ይላል፡፡ ሥለዚህ ከኸዋሪጆች በምን ተለየህብን፡፡ ከነሱ የተለየ ያልከው ምን አለ? እስቲ የሚለው አንብቡ...
[ ከዚህ በታች ያለው ፅሁፍ ኢብን አል ቀይም የመረጡትን አቋም እና ኩፍር አስገር ነው ያሉት በአንድ ወይ ሁለት ጉዳይ ላይ ድንገት ድንበር ያለፈን ብቻ እንጂ በዘመናችን ያሉትን
የአሜሪካን እና እንግሊዝ ባሪያ የሆኑትን ጠዋጊቶች (የአቡ ሙስሊም ወዳጆች) እንደማይጨምር ያረጋገጥኩበት ነው። ] ይላል የደውላው ሼይኽ አቡ ጧኢሽ...
መልስ:- በዚህ የጅህልና ንግግሩ ጭራሽ በኢብኑል ቀይም ንግግር ላይ የሌሉ ጥመቶቹን አነባብሮ አስቀምጧል፡፡
1ኛው). [ ኩፍር አስገር ነው ያሉት በአንድ ወይ ሁለት ጉዳይ ላይ ድንገት ድንበር ያለፈን ብቻ እንጂ...] ብሏል፡፡ ይህን ቅጥፈት በሚከተለው የኢብኑል ቀይም ንግግር በማብራራት እንየው!
【ﻭﺍﻟﺼﺤﻴﺢ ﺃﻥ ﺍﻟﺤﻜﻢ ﺑﻐﻴﺮ ﻣﺎ ﺃﻧﺰﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻳﺘﻨﺎﻭﻝ ﺍﻟﻜﻔﺮﻳﻦ ﺍﻷﺻﻐﺮ ﻭﺍﻷﻛﺒﺮ ﺑﺤﺴﺐ ﺣﺎﻝ ﺍﻟﺤﺎﻛﻢ، ﻓﺈﻧﻪ ﺇﻥ ﺍﻋﺘﻘﺪ ﻭﺟﻮﺏ ﺍﻟﺤﻜﻢ ﺑﻤﺎ ﺃﻧﺰﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻲ # ﻫﺬﻩ _ ﺍﻟﻮﺍﻗﻌﺔ ﻭﻋﺪﻝ ﻋﻨﻪ ﻋﺼﻴﺎﻧﺎً ﻣﻊ ﺍﻋﺘﺮﺍﻓﻪ ﺑﺄﻧﻪ ﻣﺴﺘﺤﻖ ﻟﻠﻌﻘﻮﺑﺔ ﻓﻬﺬﺍ ﻛﻔﺮ ﺃﺻﻐﺮ، ﻭﺇﻥ ﺍﻋﺘﻘﺪ ﺃﻧﻪ ﻏﻴﺮ ﻭﺍﺟﺐ ﻭﺃﻧﻪ ﻣﺨﻴﺮ ﻓﻴﻪ ﻣﻊ ﺗﻴﻘﻨﻪ ﺑﺄﻧﻪ ﺣﻜﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻬﺬﺍ ﻛﻔﺮ ﺃﻛﺒﺮ، ﻭﺇﻥ ﺟﻬﻠﻪ ﻭﺃﺧﻄﺄﻩ ﻓﻬﺬﺍ ﻣﺨﻄﺊ ﻟﻪ ﺣﻜﻢ ﺍﻟﻤﺨﻄﺌﻴﻦ】
【ትክክለኛ (አቋም) አሏህ ባላወረደው ነገር መፍረድ እንደ ሃኪሙ (ፈራጁ) ሁኔታ ሁለቱንም የኩፍር አይነቶች ያካትታል፡፡ ትንሹም ትልቁም፡፡ ሠውዬው በዚህች ክስተት አሏህ ባወረደው ነገር መፍረድ ግዴታነቱ #የሚያምን ከሆነና ለቅጣት የሚዳርገው መሆኑን እያረጋገጠ ለማመፅ በሚል ቢያዘነብል ይህ ኩፍር አስገር ነው፡፡ ግዴታ አይደለም ብሎ ቢያምንና እኔ ምርጫ አለኝ ቢል የአሏህ ፍርድ መሆኑን እርግጠኛ ሆኖ ይህ ትልቁ ኩፍር ነው፡፡ ባያውቀውና ቢሳሳት ይህ ተሳሳች ነው፡፡ ስህተት ላይ የወደቁ ሠዎች ሑክም አለው፡፡ 】📚መዳሪጁ አሥ-ሣሊኪን
፨ በዚህ ንግግር ላይ ኢብኑል ቀይም አንድ ጊዜ ፣ ሁለት ጊዜ ፣ ሶስት ጊዜ የሚል ንግግር ጭራሽ የላቸውም፡፡ እንዲህ ለማለት የሚወስድ ፍንጭ እንኳን የለውም፡፡ በዚህች ክስተት () ያሉት እየተናገሩበት ያለውን የፍርድ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ በዚህ ብለው አልገደቡትም፡፡ በቁጥርም አልገለፁትም፡፡ (الواقعة) የሚለው ቃል ጥቅል መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው፡፡ አንድ ይሁን ሁለት ይሁን እየተናገሩ አይደለም፡፡ ለዚህም ነው ሼይኹ " ከሱ የተዘነበለ" (ﻭﻋﺪﻝ ﻋﻨﻪ) ማለት ከአሏህ ሑክም የተዘነበለ እያሉ ነው፡፡ አቡ ጧኢሽ በጅህልናው እንደዘባረቀው ሼይኹ (الواقعة) ክስተት እየተናገሩ ቢሆን ኖሮ (وعدل عنها) ይሉ ነበር፡፡ ምክንያቱም (الواقعة) የሚለው ተእኒስ እንስት መደብ ላይ የተቀመጠ ነው፡፡ ሼይኹ ያሉት ግን አጠቃላይ ንግግራቸው የሚያጠነጥንበት የአሏህ ሁክምን በተመለከተ ነው የተናገሩት፡፡ ስለዚህ "አል-ዋቂዐህ" የሚለው የቁጥር ብዛት የሚያመለክት አይደለም፡፡
፨ በመቀጠል ማንሳት ያለብኝ ነጥብ አንድ ሃኪም በአንድ መሥዐላ ቢፈርድ ፣ በሶስት መሥዐላ ሲፈርድ መዐሲ (ወንጀል) ነው ከተባለ ፣ በአንድ ሺህ ነገር ሲፈርድ ኩፍር የሚሆንበት በምን አግባብ ነው? ዐጂብ ይህ ሠው ቢያንስ ሁኔታው ወንጀል ላይ ዘውታሪ (ሙሲር አል-መዐሲ) ተብሎ ነው የሚገለፀው፡፡ እንጂ ካፊር አይባልም፡፡ የኢብኑል ቀይም ንግግር አጣሞ የፈሠረበት አሁን መጥቀስ አልችልም ረዝሟል፡፡
በሌላ ፅሁፍ እንገናኛለን፡፡ አሏህ ሃቅ ይግጠመን፡፡ ወልሃምዱሊላህ፡፡
No comments:
Post a Comment