፨ ስለ ዑለማዎች መታዘዝና የመሐይም ኸዋሪጆች ግንዛቤ
=========================
፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩህና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ፡፡
፨ በአህሉ ሡናዎች ዐቂዳ መሠረት የሚያከፍር መታዘዝ (الطاعة المكفرة) የሚባለው ነገር በልቁ የሚያዝ እንዳልሆነ ሙሐቂቅ ዑለሞቻችን ያስቀምጣሉ፡፡ ኸዋሪጆች ግን ከድሮም ጀምሮ ሱፈሃኡ-አህላም ናቸውና ሸሪዐን እንዴት መገንዘብ እንዳለባቸው የሚረዱ አይደሉም፡፡ የሚያከፍር መታዘዝ የሚባለው በኢስቲህላል ላይ የቆመ ነገር ነው፡፡
- ይህ ማለት በወንጀል ላይ ስንታዘዝ ሐላል በማድረግ ላይ ተመሥርተን የታዘዘን ከሆነ ብቻ እና ብቻ ነው ኩፍር አክበር የሚሆነው...
በተህሊል (ሐላል በማድረግ) እና በተሕሪም (ሐራም በማድረግ) ላይ መታዘዝ የሚባለው ነገር ኩፍር የሚሆነው በኢስቲህላል መልክ ከተፈፀመ ብቻ ነው፡፡
የአህሉ-ሡናህ ዑለሞች ይህን አንቀፅ በዚህ መልኩ ነው የተረዱና ያስቀመጡት!
42:21 * ከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አልሏቸውን? * እንደዚሁ የአሏህ ንግግር ...
9:31 * ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡* እናም
6:121 *ብትታዘዙዋቸውም እናንተ በእርግጥ አጋሪዎች ናችሁ፡፡*
: {أم لهم شركاء شرعوا لهم من الدين ما لم يأذن به الله} وقوله تعالى : {وإن أطعتموهم إنكم لمشركون} وقوله تعالى : {اتخذوا أحبارهم ورهبانهم أربابا من دون الله}
፨ እነዚህ አንቀፆች ሐላል በማድረግና ሐራም በማድረግ ላይ መታዘዝን በተመለከተ የሚያሥረዱ ናቸው፡፡ ይህ ነጥብ በሁለት መልኩ ተከፋፍሎ የሚታይ ነው፡፡
1ኛ). በወንጀል ላይ መታዘዝ ይሆናል ይህ *ወንጀል* (معصية)ነው፡፡
2ተኛ). ወይ ደግሞ ኢስቲህላል በሚያደርግ ሁኔታ በወንጀል መታዘዝ የሚለው ነው፡፡ ይህ ከሽርክ ይመደባል፡፡
፨ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሂመሁሏህ እንዲህ ያብራራዋል
يقول ابن تيمية رحمه الله :
*ሌላን አካል በመሥማትና በመታዘዝ ከከፊል የአሏህ አምልኮቶች የተኩራራ ሠው እዚህ ቦታ ላይ *ላ ኢላሃ ኢለሏህ* የሚለውን ቃል አላረጋገጠም፡፡ እነዛ ቀሳውስቶቻቸውና መነኩሴዎቻቸው ጌታ አድርግ በመያዝ አሏህ ሐራም ያደረገውን ሃላል ሲሉ ፥ አሏህ ሐላል ያደረገውን እነሱ ሐራም ሲሉ የታዘዟቸው ሠዎች በሁለት በኩል ተከፋፍሎ የሚታይ ነው!
(من استكبر عن بعض عبادة الله سامعًا مطيعًا في ذلك لغيره، لم يحقق قول: لا إله إلا اللّه، في هذا المقام. وهؤلاء الذين اتخذوا أحبارهم ورهبانهم أربابا حيث أطاعوهم في تحليل ما حرم اللّه وتحريم ما أحل اللّه 👈🏼 يكونون على وجهين:
#أحدهما: أن يعلموا أنهم بدلوا دين اللّه فيتبعوهم على التبديل، #فيعتقدون تحليل ما حرم اللّه، وتحريم ما أحل اللّه، اتباعًا لرؤسائهم، مع علمهم أنهم خالفوا دين الرسل، فهذا كفر، وقد جعله اللّه ورسوله شركًا وإن لم يكونوا يصلون لهم ويسجدون لهم، #فكان_من_اتبع_غيره_في_خلاف_الدين مع علمه أنه خلاف الدين، #واعتقد ما قاله ذلك، دون ما قاله اللّه ورسوله مشركًا مثل هؤلاء.
፨ አንደኛው. እነሱ የአሏህ ዲን እንደቀየሩ ማወቃቸውና በዚያ በቀየሩት ነገር ሲከተሏቸው ነው፡፡ አለቆቻቸው በመከተል አሏህ ሐራም ያደረገውን ሐላል ነው ብለው #ሲያምኑ ፥ አሏህ ሐላል ያደረገውን ሐራም ነው ብለው #ሲያምኑ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው የአሏህ ዲን የኻለፉ መሆናቸው ከማወቃቸው ጋር ነው፡፡ ይህ ክህደት ነው፡፡ አሏህና መልዕክተኛው ሽርክ አድርገውታል፡፡ ሠዎቹ (ለአለቆቻቸው) ባይሠግዱላቸውም እንኳን ፥ ከዲን በተቃራኒ ያለን ነገር የተከተለ ሠው ፥ ከዲን የሚፃረር ነገር መሆኑ እያወቀ ከሆነ ፥ አሏህና መልዕክተኛው ከተናገሩት ውጪ በዚያ ነገር ላይ የተናገረውንም #ካመነ እንደነዚያ ሙሽሪክ ይሆናል፡፡
#والثاني: #أن_يكون_اعتقادهم وإيمانهم بتحريم الحلال وتحليل الحرام #ثابتًا، لكنهم أطاعوهم في معصية اللّه، كما يفعل المسلم ما يفعله من المعاصي التي يعتقد أنها معاص، فهؤلاء لهم حكم أمثالهم من أهل الذنوب)
፨ ሁለተኛው ፦ " ሐላሉን ሐራም በማድርግና ሐራሙን ሐላል በማድረግ ላይ ያላቸው እምነት የተረጋገጠ ነው፡፡ ነገር ግን አሏህን በማመፅ ነው የታዘዟቸው፡ ልክ አንድ ሙሥሊም ማንኛውም ወንጀል እንደሚሠራው ፥ ያ ወንጀል መሆኑን እያመነ የሚሠራው ነው ፥ እነዚህ ሠዎች እኔደ አምሳዮቻቸው የወንጀል ባለቤቶች አይነት ሁክም ነው ያላቸው፡፡ *
📚
፨ ይህንን ነጥብ ይበልጥ በማብራራት እንመልከተው፡፡ ከሠለፎች የፀደቁ አሰሮችና የሙፈሲሮች ንግግር እየመጣን ፥ የስንኩል ግንዛቤ ባለቤቶች (ኸዋሪጆችን) እንምከር
፨ ኢማም አቡ ጃዕፈር አጥ-ጦበሪይ ረሂመሁሏህ እንዲህ ብሏል ፦ የአሏህን ንግግር [ ከአሏህ ውጪ ጌቶች አድርገው.. ] የሚለው (أربابا من دون الله) የሚለው ሲያብራራው እንዲህ ብሏል ፦ "ይህ ማለቱ ከአሏህ ውጪ ለነሡ አለቃ አደረጓቸው፡፡ #አሏህን_በማመጽ_ላይም_ይታዘዟቸዋል፡፡" አለ፡፡
يقول الإمام الطبري رحمه الله في تفسير قوله تعالى (أربابا من دون الله) : [ يعني: سادةً لهم من دون الله، #يطيعونهم_في_معاصي_الله]
፨ ይህ ንግግር ከቀልባችን አስተንትነን እንረዳው ፥ በርግጥ ኢማም አጥ-ጦበሪይ ማብራርያ አልጨረሰም፡፡ እንደ አንዳንድ ሱፈሃኡ-አህላም የሩጫ ግንዛቤ እቺን ቦታ ብቻ ቆረጠው ያመጧትና ባጢላቸውን ለመገንባት ይጣጣራሉ፡፡ ነገርግን ቀጥለን በደንብ የሚያብራራውን የኢማም አጥ-ጦበሪ ንግግር እናምጣው...
" (አለቆቻቸው) ሐላል ያደረጉትን ነገር ሐላል ነው ይላሉ ፥ በርግጥ አሏህ ሐራም አድርጎት እያለ፡፡ (አለቆቻቸው) ሐራም ያደረጉትን ሐራም ነው ይላሉ ፥ በርግጥ አሏህ ሐላል ካደረገው ነገር ሆኖ እያለ፡፡ " አለ ኢማም አጥ-ጦበሪይ ረሂመሁሏህ
[فيحلون ما أحلُّوه لهم مما قد حرَّمه الله عليهم، ويحرِّمون ما يحرِّمونه عليهم مما قد أحلَّه الله لهم]
፨ እዚህ ጋር ቆም ብለን የምናየው ነገር ቢኖር እነዚህ ሠዎች ዑለሞቻቸው አሏህ ሃላል ያደረገውን ነገር ሐራም ነው ሲሏቸው "አዎ ሃራም ነው" ሳይሉ ቢታዘዟቸውና ቢፈፅሙ ተግባራቸው ኩፍር አይሆንም፡፡ ባይሆን የማያከፍር ወንጀል ይሆንባቸዋል፡፡ ነገር ግን አሏህ ሐላል ያደረገውን ፥ አለቆቻቸው ሐራም ነው ሲሉ *አዎ! ሐራም ነው* ብለው ከታዘዟቸው ይህ ጊዜ ኩፍር ይሆንባቸዋል፡፡
የኢማም አጥ-ጦበሪይ ሙሉው ንግግር ይኽ ነው፡፡👇
(يعني: سادةً لهم من دون الله، #يطيعونهم_في_معاصي_الله فيحلون ما أحلُّوه لهم مم
ا قد حرَّمه الله عليهم، ويحرِّمون ما يحرِّمونه عليهم مما قد أحلَّه الله لهم)
፨ ይቺ ነች የምታከፍር መታዘዝ በመባል የምትታወቀው፡፡ በወንጀል ስንታዘዝ ሐላል አድርገን ከታዘዝን ማለት ነው፡፡
ከዚህ በመቀጠል ኢማም አቡጃዕፈር ረሂመሁሏህ በተፍሢሩ ላይ የተለያዩ አሳሮች አምጥቶ ይህ የአህሉ ሡናህ ዐቂዳ ያጠናክረዋል፡፡
[16633- حدثني سعيد بن عمرو السكوني قال: حدثنا بقية، عن قيس بن الربيع, عن عبد السلام بن حرب النهدي, عن غضيف, عن مصعب بن سعد, عن عدي بن حاتم قال:
* ዐዲይ ቢን ሃቲም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ "የአሏህ መልዕክተኛ ሠለሏሁ ዐለይሒ ወሠለም ሡረቱል በራኣ እየቀሩ ሠማኋቸው፡፡ "ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡" (اتخذوا أحبارهم ورهبانهم أربابًا من دون الله) የሚለው ሲቀሩ "የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! እነሱ እኮ (ለሊቃውንቶቻቸውና ለመነኮሳቶቻቸው) አይሠግዱላቸውም ነበር፡፡ " አልኩኝ አለ፡፡
- እሳቸውም "እውነት ብለሃል ፣ ነገርግን አሏህ ሐራም ያደረገውን ነገር እነሱ (ሊቃውንቶችና መነኩሴዎቹ) ሐላል ያደርጉላቹህ ነበር፡፡ #እነዚያም_ሐላል_(ያደርጉታል)_ነው_ይላሉ፡፡ አሏህ ሐላል ያደረገውን እነሱ ሐራም ያደርጉታል፡፡ እነዚያም ሐራም (ያደርጉታል) ነው ይላሉ፡፡ "
سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقرأ " سورة براءة "، فلما قرأ: (اتخذوا أحبارهم ورهبانهم أربابًا من دون الله)، قلت: يا رسول الله, إما إنهم لم يكونوا يصلون لهم! قال: صدقت, ولكن كانوا يُحلُّون لهم ما حرَّم الله #فيستحلُّونه, ويحرّمون ما أحلّ الله لهم فيحرِّمونه. (44)
፨ በዚህ የዐዲይ ቢን ሃቲም ረዲየሏሁ ዐንሁ ሐዲስ ላይ የተብራራው..
1ኛው). እነዚያ ጌታ አድርገው ያዙ የተባሉ ሠዎች ለሊቃውንቶቻቸውና ለመነኩሴዎቹ አይሠግዱላቸው ነበር፡፡ ያመልኳቸዋል የተባለው በሌላ አይነት እንደሆነ ረሡል ሠለሏሁ ዐለይሒ ወሠለም አብራሩለት፡፡
2ተኛ. እነዚያ ሠዎች አለቆቻቸው ጌታ አድርገው ያዙ የተባለው ፥ ሊቃውንቶቹና መነኩሴዎቹ ሃራምና ሃላል ብለው ሲነግሯቸው ፥ በወንጀል ስለታዘዟቸው ብቻ አይደለም፡፡ እንግዲያውስ አለቆቹ ሐላል ነው ፥ ሲሉ ተከታዮችም አዎ ሐላል ነው ብለው ይተገብሩ ስለነበር ነው፡፡ ይህ ለማረጋገጥ فيستحلُّونه በማለት በመዕሲያ ብቻ ስለታዘዟቸው እንዳልሆነ ገለፁ፡፡
፨ ሌላው የሠለፎች አሳር ፦ ከኹዘይፋህ የተዘገበ ነው፡፡ እሱም "ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡" ስለሚለው የአሏህ ቃል ተጠየቀ.. " ያመልኳቸው ነበርን?" ተብሎ ተጠየቀ፡፡
-እንዲህ መለሠ "አይ (አለቆቻቸው) ለእነሱ የሆነ ነገር ሐላል ያደረጉላቸው ጊዜ #እነሱም_ሐላል_ያደርጉታል፡፡ በእነሱ ላይ የሆነን ነገር ሐራም ያደረጉባቸው ጊዜ #ሐራም_ያደርጉት ነበር፡፡ "
16634- حدثنا محمد بن بشار قال، حدثنا عبد الرحمن بن مهدي قال، حدثنا سفيان, عن حبيب بن أبي ثابت, عن أبي البختري, عن حذيفة: أنه سئل عن قوله: (اتخذوا أحبارهم ورهبانهم أربابًا من دون الله)، أكانوا يعبدونهم؟ قال: لا كانوا إذا أحلُّوا لهم شيئًا #استحلوه, وإذا حرَّموا عليهم شيئًا حرَّموه.
በዚህ 👇 ዘገባ ደግሞ ለኹዘይፋህ እንዲህ ተባለ " ሊቃውንቶቻቸው ያዙ ..."( اتخذوا أحبارهم) ስለሚለው የአሏህ ቃል ምን ትላለህ?" ተባለ፡፡ እንዲህ አለ "እነሱማ ለነሱ ብለው አይፆሙላቸውም ፥ አይሠግዱላቸውም ነበር፡፡ ነገርግን ለነሱ አንድ ነገር ሐላል ሲያደርጉላቸው (እነሱም) #ሐላል ይሉ ነበር፡፡ አሏህ ሃላል ያደረገላቸው ነገር ሆኖ (አለቆቻቸው) ሐራም ነው ሲሉ እነሱም #ሐራም ነው ይላሉ፡፡ በዚህ መልኩ ነበር ጌታ ተደርገው የመያዛቸው ነገር፡ "
16636- حدثنا ابن وكيع قال، حدثنا يزيد بن هارون, عن العوام بن حوشب, عن حبيب عن أبي البختري قال: قيل لحذيفة: أرأيت قول الله: (اتخذوا أحبارهم) ؟ قال: أمَا إنهم لم يكونوا يصومون لهم ولا يصلون لهم, ولكنهم كانوا إذا أحلوا لهم شيئًا #استحلُّوه, وإذا حرّموا عليهم شيئًا أحله الله لهم حرَّموه, فتلك كانت رُبوبيَّتهم.]
፨ እዚህ በተጨማሪ የሚባለው ወደ-ጧጉት መፋረድ ኩፍር የሚሆነው በኢስቲህላል መልክ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም ወደጧጉቱ ተሃኩም አደርግን ማለት በሚፈርድበት ነገር #ታዘዝነው ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ተሃኩም (التحاكم) መሠረቱ መታዘዝ ነው፡፡
ለዚህም ነው አሏህ ሱብሃነሁ ወተዐላ ለነዚያ ሙናፊቆች ሲወቀሳቸው *መታዘዝን በተመለከተ ርዕስ ላይ ነው፡፡* ምክንያቱም መታዘዝ ነው የተሃኩም መሠረቱ፡፡ ይህ ማለት በአንድ መሥዐላ ላይ አ
ሏህን በቀልብና በሠውነታችን በምንሠራው ተግባር ለመታዘዝ የአሏህን ሑክም መፈለግ ማለት ነው ተሃኩም ሲባል፡፡
አሏህ እነዚያ ሙናፊቆችን ሲወቅሳቸው የተናገረውን እንይ
: {وَمَا أَرْسَلْنَا مِن رَّسُولٍ #إِلَّا_لِيُطَاعَ_بِإِذْنِ_اللَّهِ ۚ وَلَوْ أَنَّهُمْ إِذ ظَّلَمُوا أَنفُسَهُمْ جَاءُوكَ فَاسْتَغْفَرُوا اللَّهَ وَاسْتَغْفَرَ لَهُمُ الرَّسُولُ لَوَجَدُوا اللَّهَ تَوَّابًا رَّحِيمًا}
[ ማንንም መልክተኛ በአላህ ፈቃድ ሊታዘዙት እንጅ አልላክንም፡፡ እነሱም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ ወደ አንተ ቢመጡና አላህንም ምሕረትን በለመኑ መልክተኛውም ለነርሱ ምሕረትን በለመነላቸው ኖሮ አላህን ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ኾኖ ባገኙት ነበር፡፡ ] 4:64
يقول الإمام الطبري رحمه الله :
፨ ኢማም አጥ-ጦበሪይ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላል ፦ " ይህ ከአሏህ ዘንድ የሆነ ማሥፈራርያ ነው፡፡ ለነዚያ ተሃኩምን ፈልገው የሄዱትን፡፡ እነሱ በነብዩ ሠለሏሁ ዐለይሒ ወሠለም ላይ በተወረደው አምነናል ብለው ይሞግቱ ነበር፡፡ ወደጧጉትም በመካከላቸው ባለው ጉዳይ ሊፋረዱ ሄዱ ፥ ከረሡል ሠለሏሁ ዐለይሒ ወሰለም እየሸሹ፡፡" ለነሱ አሏህ እንዲህ ይላቸው: አንድም መልዕክተኛ አልላኩም ፥ ወደሱ በላኩት ነገር ላይ እንዲታዘዙት ግዴታ ባደርግ እንጂ፡፡ ሙሐመድ ሠለሏሁ ዐለይሂ ወሠለም ከነዚያ ሩሡሎች መካከል ነው፡፡ እሳቸውን መታዘዝና ሑክማቸውን መውደድ የተወ ሠው ፥ ከዚያ ወደጧጉት ሄዶ የተፋረደ የኔን ትዕዛዝ ጥሷል፡፡ ግዴታ ያደረግኩት ነገርም አጠፋ፡፡ "
(وإنما هذا من الله #توبيخ للمحتكمين من المنافقين = الذين كانوا يزعمون أنهم يؤمنون بما أنـزل إلى النبي صلى الله عليه وسلم = فيما اختصموا فيه إلى الطاغوت، صدودًا عن رسول الله صلى ال
له عليه وسلم. يقول لهم تعالى ذكره: ما أرسلتُ رسولا إلا #فرضت_طاعته على من أرسلته إليه، فمحمد صلى الله عليه وسلم من أولئك الرسل، #فمن_ترك_طاعته_والرِّضى_بحكمه_واحتكم_إلى_الطاغوت، فقد خالف أمري، وضيَّع فرضي.)
📚 አጥ-ጦበሪ
፨ ስለተሃኩም ሲወራ አስሉ መሠረቱ ከጧዐ (መታዘዝ) የሚመደብ ነገር ነው፡፡
፨ስለዚህ በሌላ ክፍል እንመጣበታለን፡፡ ዋናው የተፈለገው መልዕክት ዑለማዎች ፥ ሊቃውንቶች ፥ መነኩሴዎች የመሳሰሉት ያለ ኢስቲህላል ሐራምና ሐላል ብለው ከአሏህ ኪታብ ውጪ በሚሉት ነገር መታዘዝ ትልቁ-ኩፍር አይደለም፡፡
🔖 ወልሐምዱሊላሂ ረቢል ዐለሚን
No comments:
Post a Comment