✔ በአሏህ ስም እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡
الحمد لله وصلاة وسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه ومن والاه ..... أما بعد
° በዚህ አጠር ያለ ትምህርት ስለ ሶብር(ትዕግስት) እንመለከታለን፡፡ በመጀመርያ ትዕግስት ምን ማለት ነው ? ሶብር በሸሪዐችን ምን አይነት ቦታ ተሰጥቶታል?
° ሶብር (ትእግስት) ማለት ፦ ኢማም ኢብንል ቀይም (አሏህ ይዘንለት) እንዲህ ገልፆታል...
አቡል ዐባስ እንዲህ ብሏል " ትዕግስት ማለት ነፍስን ከምትጠላው ነገር ማገድ ነው፡፡ አንደበትን ስሞታ ከማሰማት ማቀብ ነው፡፡ ሐዘንን ችሎ መሸከም ነው ትዕግስት ማለት፡፡ (ከመቸገር በኋላም) መጨረሻው ነፃ መውጣትን መጠበቅ ነው ትእግስት ፥ "
[ ጦሪቅ አልሂጅረተይን ፡ 338]
° ይህ ማለት በየትኛው የህይወታችን ክፍል ለሚያጋጥሙን የተለያዩ ችግሮች ፥ መበደሎች ፥ ሐዘን ፥ የመሳሰሉት ከነ ችግራቸው በመሸከም ከጀርባቸውን የሚጠብቀንን ፍሬ በማሰብ መቻልን ያጠቃለለ ትርጓሜ ነው፡፡
° ሶብር (ትእግስት) የኀይማኖት ግማሹ ክፌል ነው ይባላል፡፡ ኢማን ሁለት ግማሽ ክፍሎች አሉት፡፡ አንዱ ግማሽ ሶብር ፥ ሌላኛው ደግሞ ማመስገን (ሹክር) ነው፡፡ አሏህ እንዲህ ብሏል...
ٍ ۚ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍۢ لِّكُلِّ صَبَّارٍۢ شَكُورٍۢ
" በዚህ ውስጥ በጣም ታጋሽና አመስጋኝ ለሆነ ሁሉ መገሰጫዎች አሉበት፡፡" ሰበእ፡ 19
° የአሏህ ነብይ ሰለሏሁ አለይሒ ወሰለም እንዲህ ብለዋል ፦ ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ አሏህ ለአንድ ሙእሚን አንድ ነገር አይፈፅምለትም ለርሱ መልካም ቢሆንለት እንጂ ፡፡ ደስታ የሚሰጥ ነገር ቢገጥመው ያመሰግናል ለርሱም መልካም ይሆንለታል፡፡ መጥፎም ነገር ቢገጥመው ትዕግስት ያደርጋል በዚህ መልካም ይሆንለታል፡፡ ይህ ለሙእሚን እንጂ የሚሀቀን ነገር አይደለም፡፡ "
[ ሙስሊም የዘገቡት እና ኢማም አህመድ]
° አንድ የአሏህ ባርያ በእለት እለት ስራዎቹ ፥ በዒባዳው ፥ በሚሠራቸው ዱንያዊ ተግባራት ፥ ዕውቀት ለመፈለግ በሚሄደው መንገድ ፥ ቤተሰብ ለማስተዳደር ሲሰራ በርካታ ነገሮች ይገጥሙታል፡፡ ይህን ጊዜ የሙእሚን ባህሪይ ደህና ነገር ሲያገኝ አሏህን ማመስገን ፥ መጥፎ ነገር ሲያገኘው በዚያ ላይ ትዕግስት በማድረግ ማሳለፍ ይጠበቅበታል፡፡
° ኢማም ኢብን አልቀይም ፦ እንደሚገልፁት የኢማን ደረጃ ሁሉንም በትዕግስትና በማመስገን ላይ የቆመ ነው... ይላሉ፡፡ ቀጥለውም ይህ ነገር ይበልጥ የሚያብራራው....
° አንድ ባርያ ወይ በፀጋ ውስጥ ወይም ደግሞ በችግር ውስጥ ከመሆን በጭራሽ አያገልም፡፡ በጸጋ ውስጥ ሆኖ ከሆነ ትዕግስትና ማመስገን ግድ ይለዋል፡፡ ማመስገን የተባለው (ለፀጋው) መፅናትና መቀመጥ እንዲሁም ቢጤዋንም ለማስጨመር ነው፡፡ ነገር ግን ትእግስት(በፀጋ ላይ) ይህን ነገር ከሚያስወግድብን ነገሮች መታገስ ነው፡፡ ፀጋችን የሚጠብቅልን ነገር በመሥራት ላይ መገኘት፡፡ ይህ ደግሞ ትእግስት የሚፈልግ ነው፡፡
° እዚህ ጋር ሐብታም ሆኖ አመስጋኝና ፥ ድሃ ሆኖ የታገሰ ሚስጥሩ ይታወቃል፡፡ ሁለቱንም ወደ ሶብርና ወደ ማመስገን ፈላጊዎች ናቸው (ያስፈልጋቸዋል)፡፡ አንዳንዴ የሃብታሙ ትእግስት ከድሃው ትእግስት የተሻለ ሊሆን ይችላል፡፡
° ማመስገን ትእግስትን የሚያሲዝ ነገር ነው ያለሱ የተሟላ አይሆንም፡፡ ትእግስትም ለማመስገን የሚያሲዝ ነገር ነው፡፡ ያለ እሱ የተሟላ አይሆንም፡፡ በማንኛውም ማመስገን የተወገደ ጊዜ ትእግስትም አብሮ ይወገዳል፡፡ ትዕግስትም ሲጠፋ ማመስገን አብሮ ይጠፋል፡፡
° አሏህ በባርያዎች ላይ በፀጋ ጊዜ እንደሚያመልኩት ሁሉ በችግርም ጊዜ ሊያመልኩት ይገባል፡፡
° ትእግስት 3 ደረጃዎች ይኖሩታል፡፡
1). በወንጀል ላይ መታገስ እንዳይተገብር...
2). በመታዘዝ ላይ መታገስ (ትእዛዙ እስኪፈፅም)
3). በችግር ላይ መታገስ (ወደ ጌታው ስሞታ እንዳያቀርብ)
° አንድ ባርያ ከነዚህ ሶስቱ አንዱ እንኳን ቢኖረው ሶብር በጭራሽ ከርሱ የሚወጣ ነገር አይደለም፡፡
° ትዕግስት አሏህ በቁርአን በ90 ቦታዎች ላይ ጠቅሶታል፡፡ አንዳንዴ (በትዕግስት) እያዘዘ ፥ አንዳንዴ የትዕግስት ባለቤቶች እያወደሰ ፥ አንዳንዴ ነብዩ (ሰለሏሁ አለይሒ ወሰለም) የሶብር ባለቤቶችን እንዲያበስሩ እያዘዘ ፥ አንዳንዴ የመብቃቃትና የድል መሥፈርት ሲያደርገው ፥ አንዳንዴ እርሱ አሏህ ከሶብር ባለቤቶች ጋር መሆኑ ሲገልፅ ፥ በትእግስትም ከአለማት የተመረጡትን ነብያትና ሩሱሎችን ሲያወድስበት ፥ (በተለያዩ ቦታዎች ጠቅሷል)፡፡
ስለ አሏህ ነብይ አዩብ (ዐሰ) አሏህ እንዲህ ብሏል...
وَخُذْ بِيَدِكَ ضِغْثًۭا فَٱضْرِب بِّهِۦ وَلَا تَحْنَثْ ۗ إِنَّا وَجَدْنَٰهُ صَابِرًۭا ۚ نِّعْمَ ٱلْعَبْدُ ۖ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٌۭ
«በእጅህም ጭብጥ አርጩሜን ያዝ፡፡ በእርሱም (ሚስትህን) ምታ፡፡ ማላህንም አታፍርስ» (አልነው)፡፡ እኛ ታጋሸ ኾኖ አገኘነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ እርሱ በጣም መላሳ ነው፡፡" ሷድ ፡ 44
° የነብያትና የሩሱሎች መደምደሚያ ለሆኑት እንዲህ ብሏል ፦
فَٱصْبِرْ كَمَا صَبَرَ أُو۟لُوا۟ ٱلْعَزْمِ مِنَ ٱلرُّسُلِ
" ከመልክተኞችም የቆራጥነት ባለቤቶች የኾኑት እንደ ታገሱ ሁሉ ታገስ፡፡ " አህቃፍ ፡35
° ስለ ነብዩሏህ ዩሱፍ (አሰ) አሏህ እንዲህ ብሏል ...
قَالُوٓا۟ أَءِنَّكَ لَأَنتَ يُوسُفُ ۖ قَالَ أَنَا۠ يُوسُفُ وَهَٰذَآ أَخِى ۖ قَدْ مَنَّ ٱللَّهُ عَلَيْنَآ ۖ إِنَّهُۥ مَن يَتَّقِ وَيَصْبِرْ فَإِنَّ ٱللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجْرَ ٱلْمُحْسِنِينَ
«አንተ በእርግጥ አንተ ዩሱፍ ነህን» አሉት፡፡ «እኔ ዩሱፍ ነኝ፡፡ ይህም ወንድሜ ነው፡፡ አላህ በኛ ላይ በእርግጥ ለገሰልን፡፡ እነሆ! የሚጠነቀቅና የሚታገስ ሰው (አላህ ይክሰዋል)፡፡ አላህ የበጎ አድራጊዎችን ዋጋ አያጠፋምና» አለ፡፡ " (ዩሱፍ፡90)
° ይህ የሚያመለክተው ሶብር ከትልልቅ የኢማን ጉዳዮች እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ልናዳብረውም ከሚገባን የህይወታችን ቅመሞች ሶብር አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ በሌላ መልዕክት እንገናኛለን፡፡
ወቢላሒ አት-ተውፊቅ ....
© አቡ ሙስሊም ቢን ዐብድልሃሊም
.... ሸዋል 1439
Thursday, July 5, 2018
Tuesday, July 3, 2018
🍃_____ የሺዓ ሐይማኖት _____ 🍃
......... ክፍል አራት (4)....
ምስጋና ሁሉ ለአሏህ ይገባው፡፡ በመልዕክተኛው ሰለሏሁ አለይሒ ወሰለም ላይ የአሏህ ረድኤት ሶላት ዘወትር ይውረድ፡፡ አልሐምዱሊላህ ወደዚህ ኢስላም አሏህ ባይመራን ኖሮ እኛ የተመራን አንሆንም ነበር፡፡
በዛሬም አጭር ትምህርት የሺዓ ሐይማኖት ተከታዮች የሙስሊሞችን መንገድና ዲን የተቃረኑበትን ነጥብ በመጠኑ ለማየት እንሞክራለን፡፡
በመጀመርያ እነዚህ የኢስላምና የሶሐቦች ጠላቶች " በሱና ላይ ያላቸው እምነት ምን እንደሚመስል " እንከታተል፡፡
እነዚህ ሺዓዎች በግልፅ የነብዩ ሰለሏሁ አለይሒ ወሰለም ሐዲስን ወይም ሱናን የሚዋጉ ናቸው፡፡ ለዚህም ነው አህሉ ሱናዎች የሚለው ስያሜ የነሱ ልዩ የሆነ መጠረያ የሆነው፡፡ ምክንያቱም የረሱልን ሰዐወ ሱና የሚከተሉ ናቸውና፡፡
ሺዓዎች ከአንዳንድ አኢማዎቻቸው እንደሚዘግቡት እንዲህ ይላሉ ፦
أن كل شيء مردود إلى الكتاب والسنة وكل حديث لا يوافق كتاب الله فهو زخرف... ( البهبودي / صحيح الكافي ١/١١)
《ሁሉም ነገር ወደ አሏህ ኪታብና ወደ ሱና ተመላሽ ነው፡፡ እያንዳንዱ ከአሏህ ኪታብ የማይገጥም የሆነ ሐዲስ የተጌጠ ቅጥፈት ነው፡፡》
📚 ሶሒህ አልካፊ : 1/11
እንደዚህ አይነት ሌሎችም ንግግሮቻቸው አላቸው፡፡ ይህ ንግግራቸው የሚያስጠቅመን ነገር ቢኖር ሺዓዎች የነብያችንን ሰለሏሁ አለይሒ ወሰለም ሱና እንደማይቃወሙ ነው፡፡ በርግጥ ይህ ማጭበርበርያቸው ነው፡፡ እነሱ ከኢስላም ከሱና እጅ የራቁ ናቸው፡፡ አብዛኛው የኃይማኖታቸውም ምንጭ ኢማሞቻችን ብለው ከሚጠቅሷቸው 12 መሪዎቻቸው የሚወጡ አይደሉም፡፡
------- የኢማምን (እነሱ አማም የሚሏቸውን ነው፡፡ ) ንግግር እንደአሏህ ና እንደ ሩሱል ንግግር ነው ማለታቸው -------
ሺዓዎች ዘንድ ሱና ነው ብለው የሚያምኑትን እንዲህ ይገልፁታል፦
فالسنة هي كل ما يصدر عن المعصوم من قول أو فعل أو تقرير.
📚 الأصول العامة للففه المقارن ص: ١٢٢
" ከመዕሱም (ከስህተት ፍፁም የጠራ) ከሆነ ( ሰው) የሚመነጭ እያንዳንዱ ንግግር ፥ ወይም ተግባር ወይም ደግሞ ያፀደቀው ( تقرير) ነው ሱና የሚባለው፡፡ " ይላሉ፡፡
📚 ዑሉል አማ ሊልፊቅሒ አልሙቃረን ፡ 122
የነዚህ ቡድኖች የመዝሐባቸውን ብሉሽነት ላልተረዳ ሰው ፥ ወይም አህለል በይት ይወዳሉ በሚል ማታለያ የተታለለ ሰው በዚህ ንግግራቸው የተደበቀውን መርዝ በሚገባ ሊያውቀው አይችልም፡፡ ምክንያቱም እኛ ሙስሊሞች መዕሱም (ከስህተት የተጠበቁ) ስንል ከልበወለድ የማይናገሩትና በወህይ የሚናገሩትን ነብያችንን ነው የምንፈልግበት፡፡
ነገር ግን ሺዓዎች ዘንድ ይህን ባህሪይ የሚያጎናፅፉት ከረሱላችን (ሰዐወ) ውጭ ለሆነ አካል ነው፡፡ ንግግራቸው እንደአሏህና መልዕክተኛው ንግግር ነው የተባለላቸው ረሱል (ሰዐወ) ሳይሆኑ እነሱ አስራ ሁለት ( ኢማሞቻችን ) ብለው የሚጠሯቸውን ነው፡፡
ሺዓዎች ዘንድ በወህይ እንጂ ከማናገሩት ነብያችንን (ሰዐወ) እና በአስራ ሁለቱ ኢማሞቻቸው መካከል ልዩነት ያደርጉም፡፡ አንዳንዴ አኢማዎች ከሌሎች ነብያት የበለጡ ናቸው እስከማለትም ይደርሳሉ፡፡
ኢማሞቻቸው የማይሳሳቱ ፥ የማይረሱ ፥ የማይዘናጉ ፥ ወንጀል የማይሰሩ ...ወዘተ እያሉ ድንበር እያለፉ ኢስላምን ይሞግታሉ፡፡ በዚህ ዘመን ካሉ አለቆቻቸው አንዱ እንደሚሞግተው
" በእነዚህ አኢማዎች ጥቡቅነት ማመን ከነሱ የሚመንጭ ንግግር ሁሉ ሶሂህ ማድረግ ነው፡፡ ሰነዱ ወደ ነብያችን ሰዐወ መድረሱ መስፈርት ሳይደረግ ፡፡ ልክ በአህሉ ሱና እንደሚባለው፡፡ " ( ሙሐመድ ሪዷ አልሙዘፈር)
- እነዚህ ሺዓዎች ዘንድ አኢማዎች ማለት ልክ እንደ ረሱል (የአሏህ መልዕክተኛ) አድርገው ነው የሚቆጥሩት ፡፡ በታዓምራት በተለያዩ ነገሮች ከአንቢያዎች እንደሚስተካከሉ ይሞግታሉ፡፡ እንዲህም ይላሉ ፦
《قولهم قول الله ، وأمرهم أمر الله ، وطاعتهم طاعة الله. ومعصيتهم معصية الله ، وإنهم لم ينطقوا إلا عن الله تعالى وعن وحيه.》
📚 ابن بابويه / الاعتقادات ص :١٠٦
" (የአኢማዎች) ንግግራቸው ፥ የአሏህ ንግግር ነው፡፡ ትዕዛዛቸው የአሏህ ትዕዛዝ ነው፡፡ እነሱን መታዘዝ አሏህን መታዘዝ ነው፡፡ እነሱን ማመፅ አሏህን ማመፅ ነው፡፡ እነሱ ከአሏህ ዘንድ በሆነ ወህይ እንጂ አይናገሩም፡፡ "
📚 አልኢዕቲቃዳት ፡ 106
ይህ ነው እንግዲ የሺዓ ሐይማኖት የሚባለው፡፡
አልካፊ የሚባል እጅግ የሚመረኮዙበት ኪታብ አላቸው፡፡ በዛ መፅሐፍ እንደዘገቡት እንዲህ ብሏል ፦
የአቡ ዐብድሏህ ንግግር ነው ብለው ይሞግታሉ ፦
" የኔ ሐዲስ የአባቴ ሐዲስ ነው፡፡ የአባቴ ሐዲስ የአያቴ ሐዲስ ነው፡፡ የአያቴ ሐዲስ የሑሰይን ሐዲስ ነው፡፡ የሑሰይን ሐዲስ የሐሰን ሐዲስ ነው፡፡ የሐሰን ሐዲስ የአሚረል ሙእሚኒን ሐዲስ ነው፡፡ የአሚረል ሙእሚኒን ሐዲስ የረሱል (ሰዐወ) ሐዲስ ነው፡፡ የረሱል (ሰዐወ) ሐዲስ ደግሞ የአሏህ ዐዘ ወጀል ንግግር ነው፡፡ "
📚 ዑሱል አልካፊ ፡ 1/53 ኪታብ ፈድሉል ዒልም
የዚህ ኪታብ ሸርህ ባለቤት ሲናገር በዚህ ማስረጃ አማክኝነት የአኢማዎች ንግግር ሁሉ የአሏህ ንግግር ነው ማለት ነው፡፡ በንግግራቸው ምንም አይነት መጋጨት የለበትም፡፡ ልክ በአሏህ ንግግር መጋጨት እንደሌለው ሁሉ፡፡
📚 ሸርህ ጃሚዕ አለል ካፊ ፡ 2/272
ከነዚህ ከሚያስቀምጧቸው መሠረቶች ተነስተን እነዚህ ጭፍራዎች በዓሊይ (ረ.ዓ) ላይ ወይም በልጆቹ አልፎ በአሏህ ላይ መቅጠፍና መዋሸት ቀላል ነገር አድርገው ዲን ብለው እንደያዙት ነው፡፡ ሐሰን የተናገረው ዓሊይ ብሎታል ተብሎ ሊወራ ነው፡፡ አዑዙቢላህ...
የአልካፊ ሸርህ ባለቤትም የአኢማዎች ንግግር ወደ አሏህ አስጠግቶ ማውረት የተሻለ መሆኑ ገልፇል፡፡ ይህ ትልቅ ዙልምና በአሏህ ላይ ወሰን ማለፍ ነው፡፡
-በቀጣይ ሌሎችም የዚህ መጁስ የሆነ የኩፍር ቡድን ጥመቶችና መንገዳቸው በአጭር አጭሩ እንመለከታለን፡፡
አስቀድሞ ነው እንጂ .... መደቆስ
አሁን ምን ያደርጋል ድስጥ ጥዶ ማልቀስ
እንዳይሆን ከአሁኑኑ መጠንቀቅ ነው፡፡
☞ወቢላሒ አትተውፊቅ
📮 አቡ ኀኒዕ ናሙስ
📮 ረጀብ 28 1439 ዓ.ሒ
ሼይኽ ሱለይማን ቢን ዐብድሏህ አል-ሼይኽ (አሏህ ይዘንለት) .... እንዲህ ተጠይቀዋል ፦
፩). ለአንድ ሙስሊም ወደ ኩፋሮች ሐገር ለንግድም ይሁን ለሌላ ነገር መጓዝ ይፈቀድለታልን ??
الحمد لله ، إن كان يقدر على إظهار دينه ولا يوالي المشركين ، جاز له ذلك. فقد سافر بعض الصحابة - كأبي بكر وغيره من الصحابة - الى بلدان المشركين لأجل التجارة. ولم ينكر ذلك النبي صلى الله عليه وسلم كما رواه أحمد في مسنده وغيره.
፨ መልስ ፦ [ ለአሏህ ምስጋና ይገባው፡፡ ኃይማኖቱን ግልፅ ማድረግ የሚችል ከሆነና ፥ ሙሽሪኮችን የማይወዳጅ ከሆነ ይህ ነገር ይፈቀድለታል፡፡ ከፊል ሶሃቦች አቡበክር ይመስል ሌሎችም ሶሃቦች ለንግድ ብለው ወደ ሙሽሪኮች ሐገር ሄደዋል፡፡ ይህ ነገር ነብዩ ሰለሏሁ አለይሒ ወሰለም አልተቃወትም፡፡
- ነገር ግን ዲኑን ግልፅ ማድረግ የማይችል ከሆነና እነሱን መወዳጀት መተው የማይችል ከሆነ ወደነሱ ሐገር መሔድ አይፈቀድለትም፡፡ በነዚህ ነገር ዑለሞች መረጃ እንደጠቀሱት፡፡ ይህ ነገር የሚከለክሉ ሐዲሶች በሱ ላይ ይጠቀሳሉ፡፡]
ولأن الله تعالى أوجب على الإنسان العمل بالتوحيد، وفرض عليه عداوة المشركين.
ምክንያቱም አሏህ (ሱ.ወ) በሰው ልጆች ላይ በተውሒድ እንዲሰሩ ግዴታ አድርጓል፡፡ ሙሽሪኮችንም ጠላት አድርጎ መያዝ ግዴታ አድርጓል፡፡
ይህን ነገር ውድቅ ለማድረግ መዳረሻና ምክንያት የሆነ ነገር ሁሉ አይቻልም፡፡
እንደገና ይህ ተግባሩ እነሱ ጋር ተስማምቶ ለመሄድ ፥ ለመወደድ ይዳርገዋል ፡፡
" ይህ በአብዛኛው ወደ ሙሽሪኮች አገር በሚጓዙ ፋሲቅ ሙስሊሞች ዘንድ የሚታየው ነው፡፡ "
📚 አልጁዩሽ አር-ረባኒያ ፡ 13-14
Monday, July 2, 2018
📲 አቡ ሙስሊም ቢን ዐብድልሓሊም:
▫️የቢድዓ ባለቤቶች ፥ ያሉበት አስከፊ ሁኔታ▫️
الحمد لله وصلاة وسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه أجمعين....
° ኢማም ኢብን አልቀይም (አሏህ ይዘንለት) እንዲህ ብሏል...
" ሸይጧን ተንኮሉን (ለማስረፅ ነገሮችን) ያሰማምራል..
▫️ቀብር ዘንድ ዱዓ ማድረግ ያማረ ነገር አድርጎ ያቀርባል፡፡
▫️ቀብር ዘንድ ዱዓ ማድረግ መስጅድ ውስጥ ከማድረግ የተሻለ እንደሆነ ያቀርባል፡፡
▫️ከዚያ ቀብር ዘንድ ዱዓ ከማድረግ ተሸጋግሮ በዚያ ሰው መለመንና በአሏህ ላይ በሱ መማልን ደረጃ ይደርሳል..
▫️ከዚያም የሞተውን ሰው ራሱን ከአሏህ ውጪ እንዲለምን ያሻግረዋል፡፡
▫️ከዚያ ያ የቀብር ቦታ የኢዕቲካፍ ቦታ አድርግ እንዲይዘው ያደርገዋል፡፡
▫️እዚያ ላይ የሚበሩ ሻማ ነገሮች ይለኩሳል፡፡
▫️እዛው መቃብር ላይ መጋረጃ ነገር ይሰራል፡፡
▫️(ቀብሩን) ሱጁድ እያደረገለት ፥ ጠዋፍ እያደረገ (እየዞረው) ይገዛዋል፡፡
▫️መሳለምና መሳም ይጀምራል፡፡
▫️ ወደዚያ ቦታ ሐጅ ያደርጋል፡፡
▫️ለቀብሩም ያርዳል፡፡
ከዚያ (ሸይጣን) ሰዎች ይህን እንዲያመልኩ እንዲጣራ ያደርገዋል፡፡
▫️የሚመለክ ነገር እንደሆነ አድርጎ እንዲጣራ ያደርገዋል፡፡
▫️ ከዚያ ይህን መጥፎ ተግባር የሚያወግዝ ሰው ወደ መቃወም ይወስደዋል፡፡
▫️(ይህንም ሰው) ሩቅ ጥመት የጠመመ አድርጎ ያየዋል፡፡
📚 አልቀውል ፈስል አንነፊስ፡ 45
° ቢድዓ አራማጆች ይህ መልካም ቢድዐ ነው ፥ እገሌ ኢማም ፈቅደዋል ፥ ሼይኽ ኢማም ሰርተውታል ከማለታቹ በፊት ይህን ሸሪዓ ከተደነገገባቸው የወህይ ማስረጃዎች እምነታቹን ያዙ፡፡
° በዲን ላይ እልህ አይጠቅማቹም፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ለመቃረን ብሏቹ አኼራ ወደሚያሳጣቹ መንገድ ባላወቃቹት መንገድ ከመውደቅ ተጠንቀቁ፡፡
© አቡ ሙስሊም ቢን ዐብድልሃሊም
telegram.me/abu_muslim_namus
▫️የቢድዓ ባለቤቶች ፥ ያሉበት አስከፊ ሁኔታ▫️
الحمد لله وصلاة وسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه أجمعين....
° ኢማም ኢብን አልቀይም (አሏህ ይዘንለት) እንዲህ ብሏል...
" ሸይጧን ተንኮሉን (ለማስረፅ ነገሮችን) ያሰማምራል..
▫️ቀብር ዘንድ ዱዓ ማድረግ ያማረ ነገር አድርጎ ያቀርባል፡፡
▫️ቀብር ዘንድ ዱዓ ማድረግ መስጅድ ውስጥ ከማድረግ የተሻለ እንደሆነ ያቀርባል፡፡
▫️ከዚያ ቀብር ዘንድ ዱዓ ከማድረግ ተሸጋግሮ በዚያ ሰው መለመንና በአሏህ ላይ በሱ መማልን ደረጃ ይደርሳል..
▫️ከዚያም የሞተውን ሰው ራሱን ከአሏህ ውጪ እንዲለምን ያሻግረዋል፡፡
▫️ከዚያ ያ የቀብር ቦታ የኢዕቲካፍ ቦታ አድርግ እንዲይዘው ያደርገዋል፡፡
▫️እዚያ ላይ የሚበሩ ሻማ ነገሮች ይለኩሳል፡፡
▫️እዛው መቃብር ላይ መጋረጃ ነገር ይሰራል፡፡
▫️(ቀብሩን) ሱጁድ እያደረገለት ፥ ጠዋፍ እያደረገ (እየዞረው) ይገዛዋል፡፡
▫️መሳለምና መሳም ይጀምራል፡፡
▫️ ወደዚያ ቦታ ሐጅ ያደርጋል፡፡
▫️ለቀብሩም ያርዳል፡፡
ከዚያ (ሸይጣን) ሰዎች ይህን እንዲያመልኩ እንዲጣራ ያደርገዋል፡፡
▫️የሚመለክ ነገር እንደሆነ አድርጎ እንዲጣራ ያደርገዋል፡፡
▫️ ከዚያ ይህን መጥፎ ተግባር የሚያወግዝ ሰው ወደ መቃወም ይወስደዋል፡፡
▫️(ይህንም ሰው) ሩቅ ጥመት የጠመመ አድርጎ ያየዋል፡፡
📚 አልቀውል ፈስል አንነፊስ፡ 45
° ቢድዓ አራማጆች ይህ መልካም ቢድዐ ነው ፥ እገሌ ኢማም ፈቅደዋል ፥ ሼይኽ ኢማም ሰርተውታል ከማለታቹ በፊት ይህን ሸሪዓ ከተደነገገባቸው የወህይ ማስረጃዎች እምነታቹን ያዙ፡፡
° በዲን ላይ እልህ አይጠቅማቹም፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ለመቃረን ብሏቹ አኼራ ወደሚያሳጣቹ መንገድ ባላወቃቹት መንገድ ከመውደቅ ተጠንቀቁ፡፡
© አቡ ሙስሊም ቢን ዐብድልሃሊም
telegram.me/abu_muslim_namus
Subscribe to:
Posts (Atom)
የኢብኑ ተይሚያህ አቋም በተሃኩም ላይ...
፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን...
-
🔖 በአሏህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩህና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ በዚህ ሁፍ በአሏህ እርዳታ በመታገዝ ወደ ጧጉት መፋረድ ምን እንደሆነ እና ወደ ጧጉትም መፋረድ ያለው ሁክም እንመለከታለን፡፡ በምን አይነት...
-
✔ በአሏህ ስም እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ الحمد لله وصلاة وسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه ومن والاه ..... أما بعد ° በዚህ አጠር ያለ ትምህርት ...
-
📌 [ አል-መድኸሉ ኢላ አልጃሚዕ ፊ ኩትቢ አል ኢማን ወርረድ ዓለል ሙርጂአህ ] -------------- ክፍል _ 2 -------------- بسم الله الحمد لله والصلاة والسلام على رسول ...