Thursday, September 17, 2020

የኢብኑ ተይሚያህ አቋም በተሃኩም ላይ...

 

፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡

፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን ሹብሃ ሲረጭ እናውቀዋለን፡፡

1). "በአሏህ ሸሪዐ መፍረድ የተወ ሁሉ ይከፍራል" ይላል፡፡
2). "ሙሽሪኮችን መታዘዝ ያለምንም ገበድ (ማለትም ኢስቲህላል ሳይኖርበት) ትልቁ ሽርክ ነው ያከፍራል" ይላል፡፡

እነዚህ ባጢል አመለካከቶች በሼይኹል ኢስላም ላይ ከተናገረው ጋር አገናኝተን መልስ እንሠጣለን፡፡

በዚያ ፅሁፍ ላይ እኔ የሡን ኸዋሪጅነት እንደምገልፅ መናገሬና ያንንም አለማድረጌ ወቅሶኛል፡፡ በርግጥም በርካታ ቦታዎች ላይ የኸዋሪጆች ቢድዐ ደም ሥሩ ገብቶ ናላው እያዞረው እንደሆነ አስረድቼዋለሁ፡፡ አዎ! የኸዋሪጆች መንገድ ይዣለሁ ብሎ እስኪመሠክር አልጠብቀውም፡፡

አሁን ወደ ኢብኑ ተይሚያህ ንግግር እንሂድ፡፡ እኔ የጠቀስኩት የኢብኑ ተይሚያህ አጭር ንግግሩን ለቦታው የሚገጥም ስለነበር እንጂ ሠፋ ያለውን ንግግሩን ለማምጣት አለመፈለጌ አይደለም፡፡ እንደውም ከተባለ ከተባለ አቡ ኢምራን እጅግ ወሳኝ የሆነ የኢብኑ ተይሚያህ ንግግር ዘሎታል፡፡ እኔ እንዲህ ላስቀምጠው...
قال ابن تيمية

[ولا ريب أن من لم يعتقد وجوب الحكم بما أنزل الله على رسوله فهو كافر، فمن استخل أن يحكم بين الناس بما يراه عو عدلا من غير اتباع لما أنزل الله فهو كافر. فإنه ما من أمة الا وهي تأمر بالحكم بالعدل وقد يكون العدل في دينها ما راه أكابرهم،  بل كثير من المنتسبين إلى الإسلام يحكمون بعاداتهم التي لم ينزلها الله سبحانه وتعالى ، كسوالف البادية وكأوامر المطاعين فيهم ، ويرون أن هذا هو الذي ينبغي الحكم به دون الكتاب والسنة وهذا هو الكفر]
<< አሏህ በረሡል ላይ ባወረደው ህግ መፍረድ ግዴታ አይደለም ብሎ #የሚያምን ሠው እሱ ካፊር ነው፡፡ በሠዎች መካከል አሏህ ያወረደውን (ህግ) ሳይከተል እሱ ፍትህ ብሎ ባሰበው ነገር መፍረድን #ሃላል_ያደረገ ሠው እሱ ካፊር ነው፡፡ ነገሩ እኮ አንድም ኡማህ የለም በፍትህ መፍረድ የምታዝ ቢሆን እንጂ፡፡ በርግጥ በዲኗ ላይ ፍትህ የሚሉት ነገር አለቆቻቸው የተመለከቱ (ይሆናል ያሉት) ነገር ነው የሚሆነው ፡፡ እንደውም ብዙ ራሳቸውን ወደኢስላም የሚያስጠጉ ሠዎች አሏህ ያላወረደው በሆነ ልማዳቸው ነው የሚፈርዱት፡፡ ለምሳሌ የገጠር ሠዎች የቆየ ባህላቸው በነሱ መካከል ያሉ የሚታዘዟቸው ሠዎች ትእዛዛት ይመሥል፡፡ ይህ ነገር ከአሏህ ኪታብና ሡና ውጪ ሊፈረድበት የሚገባ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ >>

[ فإن كثيرا من الناس #أسلموا ، ولكن مع هذا لا يحكمون إلا بالعادات الجارية لهم التي يأمر بها المطاعون ، فهؤلاء إذا عرفوا أنه لا يجوز الحكم إلا بما أنزل الله فلم يلتزموا ذلك ، #بل_استحلوا أن يحكموا بخلاف ما أنزل الله فهم كفار ، #وإلا كانوا جهالا ، #كمن_تقدم_أمرهم ]

[ ብዙ ሠዎች ወደ ኢስላም ገብተዋል፡፡ ከዚህም ጋር ግን ያቺ አለቆቻቸው የሚያዙበት የሆነው ልማዳው በሆነው ነገር ላይ እንጂ አይፈርዱም፡፡ እነዚህ ሠዎች አሏህ ባወረደው ነገር እንጂ መፍረድ እንደሚይቻል ካወቁ ፣ ያንንም ተግባራዊ ካላደረጉ እንደውም አሏህ ካወረደው ( ህግ ) ውጪ መፍረድ #ሃላል_ካደረጉ እነሱ ካፊሮች ናቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ጃሂሎች ናቸው፡፡ የነሱ ጉዳይ እንዳሳለፍናቸው ሠዎች ጉዳይ ነው፡፡ ]

📚ሚንሃጁ ሡናህ: 130

፨ በነዚህ የኢብኑ ተይሚያህ ንግግሮች ላይ አሏህ ባወረደው ሁክም መፍረድ መተው ብቻ ኩፍር አክበር ነው የሚል መልዕክት አለን? ...  እስቲ ንግግሮቹ አንድ በአንድ እንያቸው፡፡

1ኛ). መጀመርያ ላይ ካፊር ይሆናሉ ያላቸው ሠዎች አሏህ ባወረደው ነገር ላይ መፍርድ ግዴታ አይደለም ብለው #የሚያምኑ ናቸው፡፡
2ኛ). ካፊር ያላቸው ሠዎች በሠዎች መካከል ከአሏህ ሌላ በሆነ አመለካከት መፍረድ ሃላል ነው የሚሉ ሠዎች ነው፡፡
3ኛ). ሠዎች ወደኢሥላም ከገቡ በኋላ አሏህ ካወረደው ህግ ውጪ በድሮ ልማዳቸው ይፈርዳሉ አለ፡፡ ታዲያ ኢብኑ ተይሚያህ ከአሏህ ውጪ ባለ ነገር መፍረድ መተዋቸው ብቻ ካፊር ያደርጋቸዋል አለን? በፍፁም...ይኸው ንግግሩ
ويرون أن هذا هو الذي ينبغي الحكم به دون الكتاب والسنة وهذا هو الكفر
" ይህ የነሱ (ልማዳዊ ህጋቸው) ከኪታብና ሡና ውጪ ሊፈርዱበት የሚገባ መሆኑ ያምናሉ፡፡ "

እዚህ ቦታ እነዚህ ሠዎች ኩፍር ላይ የጣላቸው በአሏህ ሁክም አለመፍረዳቸው ብቻ ሳይሆን ካለመፍረዳቸው ጋር በዘልማድ የያዙትን ህግጋት ከአሏህ ኪታብና ከረሡል ሡና ውጪ ሊፈርዱበት የሚገባ አድርገው ያምኑበት ነበር፡፡ በአጭሩ የነሱን ሁክም ከአሏህ ሁክም የተሻለ እንደሆነ ያምኑ ነበር፡፡ ይህ ነው ይህ ነው ኩፍር የሚሆነው፡፡ (هو الذي ينبغي الحكم به دون الكتاب والسنة) ማለታቸው ነው ኩፍር ላይ የሚጥላቸው፡፡

*** ሁለተኛው የኢብኑ ተይሚያህ ንግግር ሥንመለከት ***

1ኛ). ብዙ ሠዎች ወደኢሥላም እንደገቡ ቢገልፅም እነዚህ ሠዎች በአሏህ ኪታብ አይፈርዱም ነበር፡፡ ነገርግን እነዚህ ሠዎች በአሏህ ኪታብ አለመፍረዳቸው ብቻ ካፊር አደረጋቸውን? በፍፁም ! ንግግሩን እንይ..

فهؤلاء إذا عرفوا أنه لا يجوز الحكم إلا بما أنزل الله فلم يلتزموا ذلك ، #بل_استحلوا أن يحكموا بخلاف ما أنزل الله فهم كفار
" እነዚህ (ሠዎች) አሏህ ባወረደው ሁክም እንጂ መፍረድ እንደማይቻል ካወቁ ግን ያንን ተግባር ባያውሉት እንደውም አሏህ ካወረደው ተፃራሪ በሆነ ነገር መፍረድን ሃላል ካደረጉ እነሱ ካፊሮች ናቸው፡፡ "

ኢብኑ ተይሚያህ እነዚህ ሠዎች የሚከፍሩት አሏህ ባወረደው ነገር አለመፍረዳቸው ብቻ ሳይሆን ከአሏህ ህግ ተቃራኒ በሆነ ነገር መፍርድ #ሐላል ነው በማለታቸው እንደሆነ ያስታውቃል፡፡

ስለዚህ አለመፍረድ ብቻው ያከፍራል የሚለው ባጢል ነው ማለት ነው፡፡ ካለመፍረዳቸው ጋር ኢስቲህላል ፣ ኢስቲክባር ፣ ተፍዲል ፣ ጁሁድ የመሣሠሉት ነገሮች ተከትለው ከሆነ ነው የሚከፍረው!

፨ አሁን ወደሌላው የኢብኑ ተይሚያህ ንግግር እንለፍ!

"وَقَالَ تَعَالَى: {فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ حَتَّى يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لَا يَجِدُوا فِي أَنْفُسِهِمْ حَرَجًا مِمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا تَسْلِيمًا} فَمَنْ لَمْ يَلْتَزِمْ تَحْكِيمَ اللَّهِ وَرَسُولِهِ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ فَقَدْ أَقْسَمَ اللَّهُ بِنَفْسِهِ أَنَّهُ لَا يُؤْمِنُ، وَأَمَّا مَنْ كَانَ مُلْتَزِمًا لِحُكْمِ اللَّهِ وَرَسُولِهِ بَاطِنًا وَظَاهِرًا، لَكِنْ عَصَى وَاتَّبَعَ هَوَاهُ، فَهَذَا بِمَنْزِلَةِ أَمْثَالِهِ مِنَ الْعُصَاةِ. وَهَذِهِ الْآيَةُ مِمَّا يَحْتَجُّ بِهَا الْخَوَارِجُ عَلَى تَكْفِيرِ وُلَاةِ الْأَمْرِ الَّذِينَ لَا يَحْكُمُونَ بِمَا أَنْزَلَ اللَّهُ،" {منهاج السنة (٥/١٣١)}

- አላህ እንዲህ ይላል [ በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍፁም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም ]

" በመካከላቸው በተፈጠረ ነገር የአሏህ ና የመልዕክተኛውን ፍርድ በተግባር ያላስገኘ ሠው አሏህ በራሱ እየማለ ያ ሠው አያምን ብሏል፡፡ ነገር ግን የአሏህና የመልዕክተኛው ሁክም በውጩም በውስጡም ተግባራዊ ያደረገ ሠው ነገርግን አመፀ ሥሜቱም ተከተለ ይህ እንደአምሳዮቹ የወንጀል ባለቤት ነው፡፡ ይህ አንቀፅ ኸዋሪጆች እነዚያ  አሏህ ባወረደው ነገር የማይፈርዱ መሪዎች ለማክፈር ማሥረጃ አድርገው ተጠቅመውታል፡፡ "

📚 ሚንሃጅ አሥ-ሡናህ 5/131

፨ ከዚህ የሼይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ንግግር የምናገኛቸው ቁምነገሮች ...

1ኛ). በመካከላችን በሚፈጠር ነገር በአሏህና መልዕክተኛው ፍርድ መፍረድ እንዳለብን!
2ኛ). በመካከላቸው በተፈጠረው ነገር በአሏህና በመልዕክተኛው ፍርድ የማይፈርዱ አሏህ እየማለ አያምኑም ብሏል፡፡
3ተኛ). የአሏህና የመልዕክተኛ ሁክምን በውጭም በውስጥ አረጋግጦ ነገርግን ስሜቱን በመከተል ካመፀ ከወንጀለኛ መሆኑ፡፡
4). ኸዋሪጆች አሏህ ባወረደው ነገር የሚፈርዱ መሪዎች በዚህ አንቀፅ ተጠቅመው እንደሚያከፍሩ አይተናል፡፡

፨ ኢብኑ ተይሚያህ በአሏህ ና መልዕክተኛ ፍርድ የማይፈርዱ ሲል ሁሉንም እንዳላካተተ በዚሁ ፅሁፍ መረዳት ይቻላል፡፡ ወይም ደግሞ በአሏህ ኪታብ መፍረድ መተው ብቻ ኩፍር አክበር ቢሆን ኖሮ እነዛ ወንጀለኞቹም ካፊር በተባሉ ፣ ኸዋሪጆቹም ባልተወቀሱ ነበር፡፡

ምክንያቱም ስሜቱ ተከትሎ በአሏህ ሸሪዐ ያልፈረደውና እነዚያ ኸዋሪጆች ያከፈሯቸው መሪዎች ሁሉ [ አሏህ ባወረደው ሸሪዐ የማይፈርዱ] (ومن لم يحكم بما أنزل الله) ናቸው፡፡ ለዚህ ነው ሡረቱል ማኢዳ ዟሂሩ ኩፍር አክበር አይጠቁምም የሚባለው፡፡ አይ ዟሒሩ ኩፍር አክበር የሚል ሠው እንደገና መጥቶ በስሜቱ የፈረደ ፣ በሸሪዐ ያልፈረደ መሪ ፣ በአንድ ሁለት ነጥብ የፈረደ ሠው አይከፍርም ሲል ከሠማኸው የአንቀፁ ዟሒር ዑሙም እንደሆነ ያልተረዳ መሃይም እንደሆነ እወቅ፡፡

፨ ኢብኑ ተይሚያህ ከላይ በተለያየ ንግግሮች ተፍዲል ፣ ወይም ኢስቲህላል ሸርጥ ማድረጉ አሳልፈናል፡፡

፨ ሌላው አል-ሁክም ቢገይሪ ማ አን-ዘለሏህ (الحكم بغير ما أنزل الله) ሼይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ኩፍር ከማይሆኑ ወንጀሎች መድቦታል፡፡ ይኸው ንግግሩ ....

وَأَمَّا الْمَعَاصِي الَّتِي لَيْسَ فِيهَا حَدٌّ مُقَدَّرٌ وَلَا كَفَّارَةٌ كَاَلَّذِي يُقَبِّلُ الصَّبِيَّ وَالْمَرْأَةَ الْأَجْنَبِيَّةَ أَوْ يُبَاشِرُ بِلَا جِمَاعٍ أَوْ يَأْكُلُ مَا لَا يَحِلُّ كَالدَّمِ وَالْمَيْتَةِ أَوْ يَقْذِفُ النَّاسَ بِغَيْرِ الزِّنَا أَوْ يَسْرِقُ مِنْ غَيْرِ حِرْزٍ وَلَوْ شَيْئًا يَسِيرًا أَوْ يَخُونُ أَمَانَتَهُ كَوُلَاةِ أَمْوَالِ بَيْتِ الْمَالِ أَوْ الْوُقُوفِ وَمَالِ الْيَتِيمِ وَنَحْوِ ذَلِكَ إذَا خَانُوا فِيهَا وَكَالْوُكَلَاءِ وَالشُّرَكَاءِ إذَا خَانُوا أَوْ يَغُشُّ فِي مُعَامَلَتِهِ كَاَلَّذِينَ يَغُشُّونَ فِي الْأَطْعِمَةِ وَالثِّيَابِ وَنَحْوِ ذَلِكَ أَوْ يُطَفِّفُ الْمِكْيَالَ وَالْمِيزَانَ أَوْ يَشْهَدُ بِالزُّورِ أَوْ يُلَقِّنُ شَهَادَةَ الزُّورِ أَوْ #يَرْتَشِي_فِي_حُكْمِهِ أَوْ #يَحْكُمُ_بِغَيْرِ_مَا_أَنْزَلَ_اللَّهُ أَوْ يَعْتَدِي عَلَى رَعِيَّتِهِ أَوْ يَتَعَزَّى بِعَزَاءِ الْجَاهِلِيَّةِ أَوْ يُلَبِّي دَاعِيَ الْجَاهِلِيَّةِ إلَى غَيْرِ ذَلِكَ مِنْ أَنْوَاعِ الْمُحَرَّمَاتِ : فَهَؤُلَاءِ يُعَاقَبُونَ تَعْزِيرًا وَتَنْكِيلًا وَتَأْدِيبًا بِقَدْرِ مَا يَرَاهُ الْوَالِي #عَلَى_حَسَبِ_كَثْرَةِ_ذَلِكَ الذَّنْبِ فِي النَّاسِ وَقِلَّتِهِ . #فَإِذَا_كَانَ_كَثِيرًا زَادَ فِي الْعُقُوبَةِ #بِخِلَافِ_مَا_إذَا_كَانَ_قَلِيلًا .)

[ የተወሰነ የሆነ ገደብና ከፋራህ የሌላቸው ወንጀሎች የሚባሉት ህፃንና ባዕድ ሴትን የሚሥም ወይም ያለ ግኑኝነት የሚደባብስ ፣ ወይም ሃላል ያልሆነ ነገር የሚበላ ደም በክት ይመሥል.....] ቀጠለና ለማሳጠር [ በውሸት የሚመሠክር ፣ወይም የውሸት ምሥክርነትን የሚያቀብል ወይም በሁክሙ ላይ ጉቦ የሚቀበል ፣ ወይም ደግሞ #አሏህ_ባላወረድ_ነገር_የሚፈርድ ወይም ከሥሩ ባሉ ሠዎች ድንበር የሚያልፍ...]

፨ በማለት ይዘረዝራል፡፡ እነዚህ የዘረዘራቸው ሁሉ አሏህ ባላወረደው ነገር መፍረድ ጀምሮ ከማያከፍሩ ወንጀሎች የሚመደቡ ናቸው፡፡

፨ ሌላው አንድ ጊዜ ከፈረደ ፣ ሁለት ጊዜ ከፈረደ የሚባለው ፍልስፍና ኢብኑ ተይሚያህ ውድቅ ሲያደርገው እንዲህ ብሏል ፦

فَهَؤُلَاءِ يُعَاقَبُونَ تَعْزِيرًا وَتَنْكِيلًا وَتَأْدِيبًا بِقَدْرِ مَا يَرَاهُ الْوَالِي #عَلَى_حَسَبِ_كَثْرَةِ_ذَلِكَ الذَّنْبِ فِي النَّاسِ وَقِلَّتِهِ . #فَإِذَا_كَانَ_كَثِيرًا زَادَ فِي الْعُقُوبَةِ #بِخِلَافِ_مَا_إذَا_كَانَ_قَلِيلًا

[ እነዚህ ሠዎች {ከላይ የዘረዘራቸው አሏህ ባላወረደው የሚፈርደው ጨምሮ ማለት ነው፡፡ } እነዚህ ሠዎች ለማሥጠንቀቅና ዐደብ ለማሥያዝ ለመቅጣትም ባለሥልጣኑ ይሆናል ባለው ልክ ይቀጣሉ፡፡ ያንን ወንጀል በሠዎች ያለው ብዛትነት እና ትንሽነት ታይቶ ነው፡፡ (ወንጀሉ) ብዙ ከሆነ ትንሽ ከሆነው በተቃራኒ  ቅጣቱም ይጨምራል፡፡ ]

፨ ይህ ማሥረጃ ሼይኹል ኢስላም ላይ እንጠለጠላለሁ ለሚል ሠው ሁሉ በአፍ ጢሙ የምትደው ነች፡፡ አሏህ ባወረደው የማይፈርድ ሁሉ #ካፊር ነው የሚሉ ሠዎች ከኢብኑ ተይሚያ መንሐጅ የጠሩ መሆናቸው ታውቃለህ፡፡

ሌላው በአሏህ ባላወረደው ነገር መፍረዱ የፈለገ ያህል ቢጨምር ፣ ቅጣቱ ይጨምራል እንጂ ከኢስላም አያስወጣውም፡፡ ምክንያቱም እንደማንኛውም ወንጀል ነው፡፡

አሏህ ባላወረደው መፍረድ በልቁ ኩፍር አክበር ቢሆን ኖሮ አንድም ጊዜ ፈረደ ፤ ሁለት ጊዜም ፈረደ ኩፍር ይሆን ነበር፡፡ ግን ጂንሡ ወይም መሠረቱ ከወንጀሎች የሚመደብ ሥለሆነ ኩፍር ለመሆኑ የግድ ቀራኢን (ተያያዥ) ነገሮች መኖር አለባቸው፡፡ ኢስቲህላል (በሌላ መፍረድ ሃላል ነው ማለት) ፣ ወይም ጁሁድ (የአሏህ ሁክም መሆኑ በማሥተባበል) ፣ ኢስቲክባር (እንደ ኢብሊስ) ፣ ተፍዲል ( የሌላን ሁክም ከአሏህ ሁክም ይበልጣል ማለት ) የመሳሰሉ ቀሪናዎች ሊኖሩ ግድ ነው፡፡

፨ ታዲያ አሁን አንድ ሠው መጥቶ በየትኛው ድፍረቱ ነው ኢብኑ ተይሚያ በአሏህ ሁክም መፍረድ መተው ብቻው ያከፍራል የሚለው?

፨ አሏህ ወደ ሐቅ ይምራን፡፡ ወልሃምዱሊላሂ ረቢል ዐለሚን፡፡


Wednesday, September 16, 2020

፨ የኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ) ንግግርና የአቡ ጧኢሽ ጅሕልና !!

፨ የኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ) ንግግርና የአቡ ጧኢሽ ጅሕልና !!

❀❀❀❀  በአሏህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩህና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ❀❀❀❀

በዚህ ፅሁፍ በአሏህ ፍቃድ የኸዋሪጆችን ሹብሃ ያደናገራቸው ሠዎች ከሚያነሷቸው ነጥቦች ፣ ሹብሃ እንኳን የማይባሉ ነገሮች አንዱ የኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ) ንግግር ነው፡፡

እስቲ የአቡ ጧኢሽ ምልከታዎች በከፊሉ እየተመለከትን ያለ ዕውቀቱ የዘባረቀውን እናጥራ፡፡

[  በምናደርገው ውይይት ከሱ የዐረብኛ እውቀት አናሳ መሆን የተነሳ የሸይኽ ሱለይማንን ንግግር ቆርጬ በማምጣት ወቅሶኝ ካበቃ በኋላ ቻናሉ ላይ በሚያሳፍር ሁኔታ የኢብን አል ቀይምን ንግግር ቆራርጦ አመጣና ኢብን አል ቀይም እንደራሱ የተጣመመ አመለካከት ያላቸው በማስመስል ሰውን
ሊያጭበረብርበት ሞከረ። ] ይላል አቡ ኢምራን (አቡ ጧኢሽ)፡፡

መልስ ፦ እዚህ ቦታ ሁለት ነገሮች አነሳለሁ፡፡ አንደኛው እኔን በዐረብኛ እውቀት ማነስ መኮነኑ ሲሆን በእርግጥም እኔ በዐረብኛ የመጠቀ እውቀት የለኝም፡፡ ነገርግን ኑሱሶች የምረዳበት ያህል ግን አውቃለሁ፡፡ አልሃምዱሊላህ፡፡ ወደፊትም በደንብ እማራለሁ፡፡ ነገር ግን አቡ ኢምራን አንድ የአረብኛ ቋንቋ ገና ጀማሪ የሆነ ተማሪ ሠው እንኳን የማይሳታቸው ስህተቶች በርካታ ቦታ ይሳሳታል፡፡ ለምሳሌ የሠዎች ሥም ሲፅፍ እንዲህ ነው፡፡
عبد الله ابن صالح ابن محمد ابن محمد
• እንግዲህ አጁሩሚያህ የሞጠለ ሠው በዚህ ሁኔታ ፅሁፍ ይፅፋል ብዬ አልጠብቅም፡፡ በሁለት ዐለመይን መካከል አሊፍ ስትወድቅ አትፃፍም፡፡ የምትጻፈው የመጀመርያ ሠጥር ላይ ካገኘናት ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ማሥተካከል የማያውቅ ሙቀት የሞላው ጃሂል እከሌ ዐረብኛ አያውቅም ሲል ያሳፍራል፡፡ እኔ በራሴ በዐረብኛ ብዙ እውቀት የለኝም፡፡ እንዲህ የወረደ ነገር ግን ኢንሻ አሏህ አልሳሳትም፡፡ ደሞ አንዴ ቢሆን ተሳስቶ ነው ትላለህ ሲደጋገምስ?
عبد الله بن صالح بن محمد بن محمد....
እያልክ መፃፍ ይኖርብሃል፡፡ እኛ ዐረብኛ ከሚያስተምሩን ሼይኾች የተማርነው ይህ ነው፡፡

• ሁለተኛው ፦ የኢብኑል ቀይም ንግግር አሳስቶ የተረጎመበት ሲሆን ይህ ወደኋላ እንመለከተዋለን፡፡

- በመቀጠል የኢማም ኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ ንግግር አመጣውና እንዲህ አለ [ አቡ ሙስሊም ይህን የኢብን አል ቀይም ንግግር አልተረጎመውም እንዳለ ነው
ቁጭ ያደረገው ምክንያቱም ከተረጎመው አቂዳዬ ብሎት የያዘውን ያፈርስበታልና ነው፡፡ ] ይላል፡፡

መልስ ፦ እኔ የኢብኑል ቀይም ንግግር ያልተረጎምኩት ዐቂዳዬ ስለሚፃረር አይደለም፡፡ ዐቂዳዬ የሚፃረር ነገር በዐረብኛ ስላስቀመጥኩት ምን ይጠቅመኛል? እኔ ዐረብኛ አላውቅም ቢባል እንኳን በቻናሌ ዐረብኛ የሚያውቁ አሉ! የዚህ ልጅ ንግግሮች እኮ መልስ ሊሰጣቸው ቀርቶ መሳሳቂያ ናቸው፡፡ እስቲ የኢብኑል ቀይም ንግግር የማን ዐቂዳ እንደሚያወድም እናያለን፡፡

[ ለማንኛውም ዋናው የአቡ ሙስሊም ቅጥፈት ኢብን አል ቀይም ይህን ንግግር ከማስቀመጣቸው በፊት የተናገሩትን ነገር መተው ነው። ይህን ንግግር ከመናገራቸው በፊት ሸይኹ ያስቀመጡት ገለፃ አቡ ሙስሊም ወደ ግሩፕ ሊወያየኝ የመጣበትን አመለካከት እንዳለ ውድቅ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ በሰው ላይ የሚቀጥፍ መሆኑንም የሚያጋልጥ ነው። ] ይላል፡፡

መልስ ፦ እኔ ያቀረብኩት ንግግር ኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ የተለያዩ አመለካከቶች ያቀራባቸውን ንግግሮች ከጨረሰ በኋላ እሱ ዘንድ ትክክለኛውን አቋም ብሎ የተናገረውን ነው፡፡ ሌሎቹ ንግግሮች የኢብኑል ቀይም አቋም የሚገልፁ ሥላልሆኑ [ የኢብኑል ቀይም አቋም ይህ ነው] ብዬ ላቀርብ አልችልም፡፡ ነገርግን አጠቃላይ በቦታው የሠፈረው ነገር እያወራሁ ቢሆን ኖሮ የሌሎቹ ንግግር ለምን ተውከው ያስብላል፡፡ እኔ ግን ያደረግኩት የራሱ የኢብኑል ቀይም አቋም ነው ያመጣሁት ሥለዚህ ትክክል ነኝ ምንም ቅጥፈት የለውም፡፡

• ሌላው ኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ ከንግግራቸው ቀድሞ ያመጧቸው ሃሳቦች የኔን አመለካከት ውድቅ የሚያደርጉ መሆናቸው ይናገራል፡፡ እዛ ጋ ያሉ ንግግሮች እኮ ትክክል አይደሉም ብለው የተናገሩት ራሳቸው ኢብኑል ቀይም ናቸው፡፡ አንባቢ ግራ እንዳይጋባ ሁሉም ንግግራቸው እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ፡፡
.................................................................

📚 [ መዳሪጁ ሣሊኪን ] 1/ ገፅ 516-520 የኢማም ኢብኑል ቀይም ንግግር ከገጽ:516 ይጀምራል፡፡ የኢማም ኢብኑል ቀይም ንግግር በዚህ ምልክት 👉【】 ውስጥ ብቻ አስቀምጣለሁ፡፡ ሌላው የኔ ማብራርያ ነው፡፡
ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ) የተለያዩ ወንጀሎችን ጠቅሰው እነዚህ ተውበት ሊደረግባቸው የሚገቡ ነጥቦች ናቸው በማለት የተለያዩ ወንጀሎችን ዘረዘሩ፡፡ እንዲህም አሉ ፦
【فأما الكفر، فنوعان : كفر أكبر وكفر أصغر 】

【ኩፍር (ክህደት) ሁለት አይነት ነው፡፡ ትልቁ ከህደት (ኩፍር አክበር) እና ትንሹ ክህደት (ኩፍር አስገር) ናቸው፡፡ 】

እንግዲህ አሁን ኢብኑል ቀይም የኩፍር አይነቶች ሊነገርን ነው፡፡ ከዚያ መካከል በቁርኣን "አሏህ ባወረደው ነገር የማይፈርዱ" (من لم يحكم بما أنزل الله) የሚለው ነጥብ ከኩፍር አክበር ይመድበዋል ወይስ ከኩፍር አስገር ይመድበዋል? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ እንቀጥል...
【فالكفر الأكبر:  هو الموجب للخلود في النار.
والأصغر:  لاستحقاق الوعيد دون الخلود ،كما في قوله تعالى وكان مما يتلى فنسخ لفظه « لا ترغبوا عن آبائكم فإنه كفر بكم» وقوله في الحديث صحيح «اثنتان في أمتي، هما بهم الكفر ، الطعن في النسب والنياحة»】
【ትልቁ ኩፍር የሚባለው ፦ በእሳት ውስጥ መዘውተርን ግድ የሚያደርግ ኩፍር ነው፡፡ ትንሹ ኩፍር ደግሞ በእሳት ከመዘውተር ውጪ (ባነሰ) ለዛቻ የሚዳርግ ነው፡፡ አሏህ በንግግሩ እንዳለው ይህ ንግግሩ የሚነበብ ነበር ከዚያ ቃላቶቹ ተሽረዋል፡፡ "ከአባቶቻቹህ አትሽሹ ይህ በናንተ ላይ ኩፍር ነው፡፡" ሶሂህ በሆነ ሃዲስ ደግሞ " ሁለት ነገሮች በህዝቦቼ ውስጥ በነሱ ላይ ኩፍር ናቸው፡፡ በዘር ማነወርና በሟች ላይ እያለቀሱ መግጠም (ሙሾ)፡፡ 】

፨ ከዚህ የኢብኑል ቀይም ንግግር የምንረዳው ኩፍር ሁለት አይነት ነው፡፡ ትልቁና ትንሹ፡፡ አሁን ትንሹ ኩፍር የሆኑ ነገሮች እየዘረዘሩ ነው፡፡ በሸሪዐችን በዟሂር "ኩፍር" በሚል ቃል ተጠርተው ግን ትንሹ ኩፍር የሆኑ ነገሮች እየዘረዘሩ ነው፡፡ ትንሹ ኩፍር የተባሉ ነገሮች ጠቅሰው ከጨረሱ በኋላ ትልቁ የተባሉ ነገሮች ያመጣሉ፡፡ እንቀጥል...

【وقوله في سنن: « من أتى امرأة في دبرها فقد كفر بما أنزل على محمد صلى الله عليه وسلم»  وفي الحديث الآخر:  «من أتى كاهنا،  فصدقه بما يقول،  فقد كفر بما أنزل على محمد صلى الله عليه وسلم»، وقوله:  «لا ترجعوا  بعدي كفارا يضرب بعضكم رقاب بعض】

【የረሡል ﷺ ንግግር  በሡነኖች ውስጥ የተዘገበ እንዲህ ይላል ፦ "ሴት ልጅን ከኋላዋ በኩል የተገናኛት በሙሃመድ ﷺ ላይ በወረደው ክዷል፡፡ በሌላ ሃዲስ ደግሞ " ጠንቋይ ዘንድ የመጣ በሚናገረውም ነገር እውት ነው ያለ በርግጥም በሙሃመድ ﷺ  ላይ በወረደው ክዷል፡፡" ሌላም የረሡል ንግግር " ከኔ በኋላ  ከፊላቹህ የሌላውን አንገት የሚመታ ካፊር ወደ-መሆን አትመለሱ 】📚 [ መዳሪጁ ሣሊኪን ] 1/ ገፅ 518

፨ እንግዲህ ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ) ሸሪዐህ ኩፍር በማለት ቢገልፃቸውም ሐቂቃቸው ግን ትንሹ ኩፍር የሆኑ ነገሮች እየገለፁ ነው፡፡ አሁን ደግሞ እሳቸው እዚሁ ቦታ " አሏህ ባወረደው ነገር የማይፈርዱ" (من لم يحكم بما أنزل الله) የሚለው አንቀፅ ከትንሹ ኩፍር ዝርዝር ውስጥ በማሥቀመጥ እንዲህ ብለዋል...

【وهذا تأويل ابن عباس وعامة أصحابه في قوله تعالى "  ومن لم يحكم بما أنزل الله فأولئك هم الكافرون" قال ابن عباس:  ليس بكفر ينقل عن الملة،  بل إذا فعله فهو به كفر وليس كمن كفر بالله واليوم الآخر. وكذلك قال طاووس. وقال عطاء:  هو كفر دون كفر،  وظلم دون ظلم   وفسق دون فسق】

【ይህ (ኩፍር አስገር) የሚለው [ አሏህ ባወረደው ነገር የማይፈርዱ እነዚያ ካፊሮች እነሱ ናቸው፡፡] በሚለው የቁርኣን አንቀፅ ላይ የኢብኑ ዐባስ እና #የአጠቃላይ_ባልደረቦቹ ተፍሲር ነው፡፡ ኢብኑ ዐባስ እንዲህ አለ "ከኢሥላም የሚያስወጣ ኩፍር አይደለም፡፡ እንደውም ይህ ሥራ የሠራ ጊዜ በሡ ላይ ኩፍር ይሆንበታል፡፡ ይህ በአሏህና በመጨረሻው እንደመካድ አይደለም፡፡ ልክ እንደዚሁ ጣውውስ ብሏል፡፡ ዓጧእ ቢን ረባህ እንዲህ ብሏል "ኩፍሩን ዱነ ኩፍር ፣ ዙልሙን ዱነ ዙልም ፣ ፊስቁን ዱነ ፊስቅ】

፨ አሁን አቡ ኢምራን (አቡ ጧኢሽ) በጅህልናው ለሚዘባርቃቸው ነገሮች ኢብኑል ቀይም መልስ እየሠጡ ነው፡፡ ምን ለምሣሌ ብትሉኝ...

1ኛ). አቡ ጧኢሽ በተለያዩ ዝባዝንኬ ፅሁፎቹ የኢብኑ ዐባስ ተፍሢር ኩፍር አክበር ያመለክታል ሲል ሲፅፍ ነበር፡፡ ይኸው ኢብኑል ቀይም ኢብኑ ዐባስም ሆነ አጠቃላይ የኢብኑ ዐባስ ባልደረቦቹ ይህች አንቀፅ *ኩፍር አስገር* ታመለክታለች ብለው ያምኑ እንደነበር ይገልፃል፡፡ ሥለዚህ የዚህ ጧኢሽና የኢማሙ መንሐጅ ለየቅል ነው፡፡

2ኛ). የኢብኑል ቀይም ንግግር የአቡ ሙሥሊሥ አካሄድ ውድቅ ያደርጋል ሲል ነበር በተቃራኒው ኢብኑል ቀይም ይህን አንቀጽ ከኩፍር አስገር ዝርዝር ውስጥ አስቀምጠውታል፡፡ እሳቸውም የበለጠ ይጠቅሱታል፡፡ እንመጣበታለን፡፡

• እስቲ አሁን ኢማም ኢብኑል ቀይም ኺላፍ ብሎ ያመጣቸው ነገሮች እንያቸው ከዚያም የአቡ ጧኢሽ ፍልስፍና እናያለን፡፡ በዚህ ምልክት【  】የኢማም ኢብኑል ቀይም  ነቅል ነው የማስቀምጠው ...እንቀጥል፡፡
【ومنهم من تأول الآية على ترك الحكم بما أنزل الله جاحدا له ، وهو قول عكرمة وهو تأويل مرجوح، فإن نفس جحوده كفر سواء حكم أو لم يحكم】

【ከነሡ መካከል አንቀፁን አሏህ ባወረደው ነገር ሁክሙን  በማሥተባበል መፍረድ የተወን ሠው ያመልክታል ብለው የፈሠሩ አሉ፡፡ ይህ የዒክሪማህ ንግግር ነው፡፡ የሱ ተፍሲርም ሚዛን የማይደፋ ተፍሲር ነው፡፡ ማሥባበል ራሱ (አሏህ ባወረደው) ኩፍር ነው፡፡ ቢፈርድም ባይፈርድም እኩል ነው፡፡】

፨ ይህ የኢክራማህ ንግግር ሐቂቃው ለተረዳው ሠው የኢማም ኢብኑል ቀይም ንግግር አይጠፋውም፡፡ ይህ አንቀፅ በልቁ የተቀመጠና ዟሒሩ ሲታይ ዑሙም (ጥቅል መልዕክት) የሚሠጥ ነው፡፡ ስለዚህ ዟሒሩ በአንድ ጉዳይ ላይ የተገደበ አይደለም፡፡ ነገርግን ሠበቡ ኑዙሉ ላይ አይሁዶች የአሏህን ሁክም ጀህድ አላደረጉም ለማለት ነው ከተባለ ይህ ባጢል ነው ምክንያቱም በንግግሩ ላይ ስለዚያ ጉዳይ ጭራሽ አላነሳም፡፡ አይሁዶች ጀህድ አላደረጉም ሁክም የተወ ብቻ ይከፍራል ቢል ኖሮ ኢብኑል ቀይም የአቡ ጧኢሽ ዐቂዳ የሚያድመውን አቋማቸው ግልጽ ባላደረጉ ነበር፡፡ ሌላኛው ኺላፍ ያሉት ንግግር እንይ ...

【  ومنهم من تأولها على ترك الحكم بجميع ما أنزل الله: قال ويدخل في ذلك الحكم بالتوحيد والإسلام. وهذا تأويل عبد العزبز الكناني. وهو أيضا بعيد، إذ الوعيد على نفي الحكم بالمنزل ، وهو يتناول تعطيل الحكم بجميعه وببعضه】

【ከነሱም መካከል አጠቃላይ አሏህ ባወረደው ነገር መፍረድ የተወ ተፈልጎበት ነው ብሎ የፈሠረ አለ፡፡ እንዳለውም " በዚህ ውስጥ በተውሒድና በኢስላም መፍረድም ይካተታል" ብሏል፡፡ ይህ የዐብዱልዐዚዝ አል-ኪናኒ ተፍሢር ነው፡፡ ይህ ራሱ የራቀ ነው፡፡ በወረደው (ሸሪዐ) ሑክምን ውድቅ በማድረግ የመጣው ዛቻ ባጠቃላይ ሁክሞች ውድቅ ማድረግም ሆነ በከፊሎቹ አካቶ የሚይዝ ነው፡፡ 】

፨ ኢብኑል ቀይም ይህን ተፍሢር ውድቅ ያደረገበት ምክንያቱ አል-ኪናኒ እንዳለው አጠቃላይ ነገሮች ላይ መፍረድ ሲተው ነው የሚከፍረው የሚል አቋም ሲያንፀባርቅ ፣ ኢብኑል ቀይም ደግሞ አንቀጹ ላይ የተቀመጠው ዛቻ አጠቃላይ ነገሮች ላይ መፍረድ የተወ ብቻ ሳይሆን ከፊል ነገሮችም ላይ ሁክምን ውድቅ ያደረገ ያክታትል እያለ ነው፡፡ አሁንም ኢብኑል ቀይም የአንቀፁ ዑሙም መልዕክት አስረግጦ እየገለፀ ነው፡፡ ሌላኛው እንቀጥል...

【ومنهم من تأولها على الحكم بمخالفة النص تعمدا من غير جهل به ولا خطأ في تأويل، حكاه البغوي عن علماء عموما】

【ከነሱ መካከል  እያወቀ ጅህልና ሳይኖርበት በተዕዊል ላይ ሳይሳሳት የወህይ ማሥረጃዎችን በመቃረን ፍርድ መሥጠት ላይ የፈሠረው አለ፡፡ ከአጠቃላይ ዑለማዎች አልበገዊ አስተላልፎታል፡፡ 】

፨ ይህ የአል-በገዊ ተፍሢር ኢብኑል ቀይም እዚሁ ቦታ ውድቅ ሳያደርገው አልፎታል፡፡ ስለዚህ እንቀጥል ኺላፍ ብሎ ያመጣቸውን ...
【  ومنهم من تأولها على أهل الكتاب. وهو قول قتادة والضحاك وغيرهما. وهو بعيد خلاف ظاهر اللفظ فلا يصار عليه 】
【ከነሱ መካከል በመፅሃፍ ባለቤቶች ላይ የፈሠረው አለ፡፡ ይህ የቀታዳህ ፣ የአድዶሃክ የሌሎችም አቋም (ንግግር) ነው፡፡ ይህ ራሱ የራቀና በዟሒር ከሚታየው ቃል የሚፃረር ነው፡፡ ወደዚህ አቋም አይኬድም፡፡ 】

፨ በዚህ የኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ ንግግር ቀታዳና ዶሃክ እንዲሁም ሌሎችም ንግግር የአንቀፁ ዟሂር አህሉል ኪታቦች የተገደበ እንዳልሆነ ያስቀምጣሉ፡፡ ይህ ሁሉም መረዳት ያለበት ነገር ነው፡፡ ሠበበ-ኑዙሉ አይሁዶች ላይ የወረደ መሆኑ ሁሉም ያውቃል፡፡ እዚህ ጋር ኢብኑል ቀይም የተቃወሙት የአንቀጹ ዟሒር ዑሙም ነው ነው፡፡ የተገደበ አይደለም፡፡ (خلاف ظاهر اللفظ) በማለት ኢብኑል ቀይም ያስቀምጣል፡፡ ይህ ሃቅ ነው ዟሒሩ አህሉል ኪታብ ላይ የተገደበ አይደለም፡፡ እንቀጥል ...
【  ومنهم من جعله كفرا ينقل عن الملة】
【 ከነሱ መካከል ከኢሥላም የሚስወጣ ኩፍር ያደረገው አለ፡፡ ]

፨ እዚህ ቦታ ኢብኑል ቀይም ይህ ንግግር ማን እንደተናገረ አላስቀመጠም፡፡ እንደዚህ የሚሉ እንዳሉ ግን በልቁ ነገረን፡፡ ነገርግን የኢብኑል ቀይም አቋም ይህ እንዳልሆነ በመቀጠል ራሱ ኢብኑል ቀይም ወስ-ሶሂሁ (وصحيح) ትክክለኛ አቋም በማለት አስቀምጧል እናየዋለን፡፡  ትክክለኛው አቋም ብሎ ማሥቀመጡ ከላይ ያሉ የሃሳብ ልዩነቶች ኢብኑል ቀይም እንዳልተቀበላቸው ማሳያ ነው፡፡

የደውላው አቡ ጧኢሽ እንዲህ ብሎ ነበር ፦ [ እኔ ይህች አያ ኩፍር አክበር ነች በማለቴ በተደጋጋሚ ይህ የኸዋሪጅ እንጂ
በጭራሽ የአህሉ ሱና አቋም አይደለም ሲለኝ ነበር] ብሏል፡፡

መልስ፦ ይህ አንቀፅ እንደአገባቡ ነው የሚፈሠረው ሁሌም የምለው ይህ ነው፡፡ ዟሒሩ ጥቅል መልዕክት ሥላለው ኩፍር አስገር የሚጠቁም ሲሆን ፣ አንቀፁ እንደወረደበት ሠበብ ከታየ ግን የአሏህን ሑክም ጀህድ ስላደረጉ አይሁዶች ነውና ኩፍር አክበር ነው፡፡ ይህ ነው ንግግሬ፡፡ አንተ እኮ የአንቀፁ ዟሂር ኩፍር አክበር ነው ትላለህ ይህ የኸዋሪጆች ዐቂዳህ እንደሆነ እኔ ሳይሆን ያስቀመጥኩት የአህሉ ሡና ዑለሞች ናቸው፡፡ ይኸው ንግግራቸው ላቅርብ..
❀ አቡል ሙዞፈር አሥ-ሠምዐኒ ረሂመሁሏህ በተፍሢሩ እንዲህ አለ ፦

ﻗﺎﻝ ﺃﺑﻮ ﺍﻟﻤﻈﻔﺮ ﺍﻟﺴﻤﻌﺎﻧﻲ ﻓﻲ ﺗﻔﺴﻴﺮﻩ ‏[ /2 42 ‏] : ﺍﻋﻠﻢ ﺃﻥ ﺍﻟﺨﻮﺍﺭﺝ ﻳﺴﺘﺪﻟﻮﻥ ﺑﻬﺬﻩ ﺍﻵﻳﺔ ﻭﻳﻘﻮﻟﻮﻥ ﻣﻦ ﻟﻢ ﻳﺤﻜﻢ ﺑﻤﺎ ﺃﻧﺰﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻬﻮ ﻛﺎﻓﺮ ﻭﺃﻫﻞ السنة ﻻ ﻳﻜﻔﺮﻭﻥ ﺑﺘﺮﻙ ﺍﻟﺤﻜﻢ. ﺍﻫـ
【እወቅ! ኸዋሪጆች በዚህ አንቀፅ ላይ ማሥረጃነት ይጠቀማሉ፡፡ አሏህ ባወረደው ነገር ያልፈረደ ካፊር ነው ይላሉ፡፡ #አህሉ_ሡናዎች ግን ሁክምን በመተው ብቻ #አያከፍሩም፡፡】

፨ ይህ የአህሉ-ሡና ዑለሞች ኢጅማዕ ነው፡፡ አቡ ጧኢሽና ጓደኞቹ ከዚህ በተቃራኒ ሁክም መተው ብቻ ያከፍራል ይላሉ፡፡ ታዲያ እኔ ነኝ እንዴ ኸዋሪጅ ያልኩህ ራስህ ኸዋሪጅ ሆነህ መጣህብን እንጂ... ሌላም ተመልከቱ

ኢብኑ ዐብዱልበር [ አት-ተምሂድ 16/17]

ﻗﺎﻝ ﺍﺑﻦ ﻋﺒﺪ ﺍﻟﺒﺮ ﻓﻲ ﺍﻟﺘﻤﻬﻴﺪ ‏[ 16 /17 ‏] : ﻭﻗﺪ ﺿﻠﺖ ﺟﻤﺎﻋﺔ ﻣﻦ ﺃﻫﻞ ﺍﻟﺒﺪﻉ ﻣﻦ ﺍﻟﺨﻮﺍﺭﺝ ﻭﺍﻟﻤﻌﺘﺰﻟﺔ ﻓﻲ ﻫﺬﺍ ﺍﻟﺒﺎﺏ ﻭﺍﺣﺘﺠﻮﺍ ﺑﺂﻳﺎﺕ ﻟﻴﺴﺖ ﻋﻠﻰ ﻇﺎﻫﺮﻫﺎ ﻣﺜﻞ ﻗﻮﻟﻪ ﻋﺰ ﻭﺟﻞ : } ﻭﻣﻦ ﻟﻢ ﻳﺤﻜﻢ
ﺑﻤﺎ ﺃﻧﺰﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﺄﻭﻟﺌﻚ ﻫﻢ ﺍﻟﻜﺎﻓﺮﻭﻥ {. ﺍﻫـ
【በዚህ ርዕስ ላይ በርግጥም ከቢድዐ ባለቤት የሆኑ  ጀመዐዎች ጠመዋል ፤ ኸዋራጆችና ሙዕተዚላዎች፡፡ በዟሂር ትርጉሟ በማትያዝ አንቀፅ ላይ ማሥረጃን አደረጉ፡፡ ለምሳሌ "አሏህ ባወረደው ነገር የማይፈርዱ እነዚያ ከሃዲዎች እነሱ ናቸው፡፡ " የሚለው አንቀፅ፡፡】

፨ ይኸው በግልፅ ኸዋሪጆች አንቀፁ በዟሂሩ ይፈስሩት ነበር፡፡ አቡ ጧኢሽም እያደረገ ያለው ይኸው ነው፡፡ እስቲ በሱ መንሃጅ ላይ ነኝ የሚለው ኢብኑ ተይሚያህ የሚለው እንይ...

ﻭﻗﺎﻝ ﺷﻴﺦ ﺍﻹﺳﻼﻡ ﺍﺑﻦ ﺗﻴﻤﻴﺔ ﻓﻲ ﻣﻨﻬﺎﺝ ﺍﻟﺴﻨﺔ ‏[ 5 / 131 ‏] : } ﻓﻼ ﻭﺭﺑﻚ ﻻ ﻳﺆﻣﻨﻮﻥ ﺣﺘﻰ ﻳﺤﻜﻤﻮﻙ ﻓﻴﻤﺎ ﺷﺠﺮ ﺑﻴﻨﻬﻢ .... { ﻭﻫﺬﻩ ﺍﻵﻳﺔ ﻣﻤﺎ ﻳﺤﺘﺞ ﺑﻪ ﺍﻟﺨﻮﺍﺭﺝ ﻋﻠﻰ ﺗﻜﻔﻴﺮ ﺍﻟﻮﻻﺓ ﺍﻟﺬﻳﻦ ﻳﺤﻜﻤﻮﻥ ﺑﻐﻴﺮ ﻣﺎ ﺃﻧﺰﻝ ﺍﻟﻠﻪ. ﺍﻫـ
【በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ...ድረስ አያምኑም" ይህ አንቀፅ ኸዋሪጆች አሏህ ባወረደው ነገር የማይፈርዱ መሪዎችን ለማክፈር ለማሥረጃነት ይጠቀሙበታል፡፡ 】

፨ ኢብኑ ተይሚያህ አሏህ ባወረደው ነገር የማይፈርዱ ሙስሊም መሪዎች እንዳሉ ጭምር እየጠቆመ ነው፡፡ አቡ ጧኢሽ ደግሞ የማይፈርዱ ሁሉ ካፊር ነው ይላል፡፡ ሥለዚህ ከኸዋሪጆች በምን ተለየህብን፡፡ ከነሱ የተለየ ያልከው ምን አለ? እስቲ የሚለው አንብቡ...

[ ከዚህ በታች ያለው ፅሁፍ ኢብን አል ቀይም የመረጡትን አቋም እና ኩፍር አስገር ነው ያሉት በአንድ ወይ ሁለት ጉዳይ ላይ ድንገት ድንበር ያለፈን ብቻ እንጂ በዘመናችን ያሉትን
የአሜሪካን እና እንግሊዝ ባሪያ የሆኑትን ጠዋጊቶች (የአቡ ሙስሊም ወዳጆች) እንደማይጨምር ያረጋገጥኩበት ነው። ] ይላል የደውላው ሼይኽ አቡ ጧኢሽ...

መልስ:- በዚህ የጅህልና ንግግሩ ጭራሽ በኢብኑል ቀይም ንግግር ላይ የሌሉ ጥመቶቹን አነባብሮ አስቀምጧል፡፡

1ኛው). [ ኩፍር አስገር ነው ያሉት በአንድ ወይ ሁለት ጉዳይ ላይ ድንገት ድንበር ያለፈን ብቻ እንጂ...] ብሏል፡፡ ይህን ቅጥፈት በሚከተለው የኢብኑል ቀይም ንግግር በማብራራት እንየው!

【ﻭﺍﻟﺼﺤﻴﺢ ﺃﻥ ﺍﻟﺤﻜﻢ ﺑﻐﻴﺮ ﻣﺎ ﺃﻧﺰﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻳﺘﻨﺎﻭﻝ ﺍﻟﻜﻔﺮﻳﻦ ﺍﻷﺻﻐﺮ ﻭﺍﻷﻛﺒﺮ ﺑﺤﺴﺐ ﺣﺎﻝ ﺍﻟﺤﺎﻛﻢ، ﻓﺈﻧﻪ ﺇﻥ ﺍﻋﺘﻘﺪ ﻭﺟﻮﺏ ﺍﻟﺤﻜﻢ ﺑﻤﺎ ﺃﻧﺰﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻲ # ﻫﺬﻩ _ ﺍﻟﻮﺍﻗﻌﺔ ﻭﻋﺪﻝ ﻋﻨﻪ ﻋﺼﻴﺎﻧﺎً ﻣﻊ ﺍﻋﺘﺮﺍﻓﻪ ﺑﺄﻧﻪ ﻣﺴﺘﺤﻖ ﻟﻠﻌﻘﻮﺑﺔ ﻓﻬﺬﺍ ﻛﻔﺮ ﺃﺻﻐﺮ، ﻭﺇﻥ ﺍﻋﺘﻘﺪ ﺃﻧﻪ ﻏﻴﺮ ﻭﺍﺟﺐ ﻭﺃﻧﻪ ﻣﺨﻴﺮ ﻓﻴﻪ ﻣﻊ ﺗﻴﻘﻨﻪ ﺑﺄﻧﻪ ﺣﻜﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﻬﺬﺍ ﻛﻔﺮ ﺃﻛﺒﺮ، ﻭﺇﻥ ﺟﻬﻠﻪ ﻭﺃﺧﻄﺄﻩ ﻓﻬﺬﺍ ﻣﺨﻄﺊ ﻟﻪ ﺣﻜﻢ ﺍﻟﻤﺨﻄﺌﻴﻦ】

【ትክክለኛ (አቋም) አሏህ ባላወረደው ነገር መፍረድ እንደ ሃኪሙ (ፈራጁ) ሁኔታ ሁለቱንም የኩፍር አይነቶች ያካትታል፡፡ ትንሹም ትልቁም፡፡ ሠውዬው በዚህች ክስተት አሏህ ባወረደው ነገር መፍረድ ግዴታነቱ #የሚያምን ከሆነና ለቅጣት የሚዳርገው መሆኑን እያረጋገጠ ለማመፅ በሚል ቢያዘነብል ይህ ኩፍር አስገር ነው፡፡ ግዴታ አይደለም ብሎ ቢያምንና እኔ ምርጫ አለኝ ቢል የአሏህ ፍርድ መሆኑን እርግጠኛ ሆኖ ይህ ትልቁ ኩፍር ነው፡፡ ባያውቀውና ቢሳሳት ይህ ተሳሳች ነው፡፡ ስህተት ላይ የወደቁ ሠዎች ሑክም አለው፡፡ 】📚መዳሪጁ አሥ-ሣሊኪን

፨ በዚህ ንግግር ላይ ኢብኑል ቀይም አንድ ጊዜ ፣ ሁለት ጊዜ ፣ ሶስት ጊዜ የሚል ንግግር ጭራሽ የላቸውም፡፡ እንዲህ ለማለት የሚወስድ ፍንጭ እንኳን የለውም፡፡ በዚህች ክስተት () ያሉት እየተናገሩበት ያለውን የፍርድ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ በዚህ ብለው አልገደቡትም፡፡ በቁጥርም አልገለፁትም፡፡ (الواقعة) የሚለው ቃል ጥቅል መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው፡፡ አንድ ይሁን ሁለት ይሁን እየተናገሩ አይደለም፡፡ ለዚህም ነው ሼይኹ " ከሱ የተዘነበለ" (ﻭﻋﺪﻝ ﻋﻨﻪ) ማለት ከአሏህ ሑክም የተዘነበለ እያሉ ነው፡፡ አቡ ጧኢሽ በጅህልናው እንደዘባረቀው ሼይኹ (الواقعة) ክስተት እየተናገሩ ቢሆን ኖሮ (وعدل عنها) ይሉ ነበር፡፡ ምክንያቱም (الواقعة) የሚለው ተእኒስ እንስት መደብ ላይ የተቀመጠ ነው፡፡ ሼይኹ ያሉት ግን አጠቃላይ ንግግራቸው የሚያጠነጥንበት የአሏህ ሁክምን በተመለከተ ነው የተናገሩት፡፡ ስለዚህ "አል-ዋቂዐህ" የሚለው የቁጥር ብዛት የሚያመለክት አይደለም፡፡

፨ በመቀጠል ማንሳት ያለብኝ ነጥብ አንድ ሃኪም በአንድ መሥዐላ ቢፈርድ ፣ በሶስት መሥዐላ ሲፈርድ መዐሲ (ወንጀል) ነው ከተባለ ፣ በአንድ ሺህ ነገር ሲፈርድ ኩፍር የሚሆንበት በምን አግባብ ነው? ዐጂብ ይህ ሠው ቢያንስ ሁኔታው ወንጀል ላይ ዘውታሪ (ሙሲር አል-መዐሲ) ተብሎ ነው የሚገለፀው፡፡ እንጂ ካፊር አይባልም፡፡ የኢብኑል ቀይም ንግግር አጣሞ የፈሠረበት አሁን መጥቀስ አልችልም ረዝሟል፡፡

በሌላ ፅሁፍ እንገናኛለን፡፡ አሏህ ሃቅ ይግጠመን፡፡ ወልሃምዱሊላህ፡፡ 




የኢብኑ ተይሚያህ አቋም በተሃኩም ላይ...

  ፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን...