Thursday, May 16, 2019

📌 [  አል-መድኸሉ ኢላ አልጃሚዕ ፊ ኩትቢ አል ኢማን ወርረድ ዓለል ሙርጂአህ ]

--------------  ክፍል _ 2 --------------

بسم الله الحمد لله والصلاة والسلام على رسول الله صلى الله عليه وسلم : أما بعد _

- የአሏህ ፍቃድ ከሆነ በተከታታይ ፅሁፎች በ አሽ-ሼይኽ አቡ ዐብድሏህ ዓዲል አል ሓምዳን (አሏህ ለኸይር ይግጠመው) የተዘጋጀውን ኪታብ መግቢያ ከጠቀሳቸው አንገብጋቢ "በኢማን" ዙርያ የሚያጠነጥኑ ጉዳዮች ወደ አማርኛ ቋንቋ ብመልሰው ብዙ ሰው ትጠቅማለች ብዬ ስላሰብኩ ተርጉሜዋለሁ፡፡ አሏህ ኢኽላስ ይወፍቀን፡፡
............................................    ........

-  በዚህ ክፍል ኢማንን በተመለከተ ፤ አኢማዎች የተናገሩትን መሠረታዊ ቁምነገሮች ይቀርባሉ፡፡

1). ኢማን በቀልብ ማመን ፤ በምላስ የሚነገር ፤ በአካል የሚተገበር መሆኑን
2). የዑለሞች የጋራ ስምምነት መኖሩን እንዲሁም ከእነዚህ 3 ማዕዘናት አንዱ ቢታጣ ኢማን የተስተካከለ ሆኖ እንደማይገኝ ነው፡፡
°
°
1). አዝ-ዙህሪይ አሏህ ይዘንለት (125 ዓ.ሒ) እንዲህ ብሏል ፦

እንዲህ እንል ነበር ፦ ኢስላም በማረጋገጥ ነው፡፡ ኢማን ደግሞ #በመተግበር ነው፡፡ ኢማን ንግግርና ተግባር የተቆራኘ ነው፡፡ አንደኛቸው አይጠቅምም በሌላኛው ቢሆን እንጂ፡፡

( አቡ ዓምር አጥጠልመንኪይ) በመጅሙዕ አልፈታዋ 7/295 ዘግቦታል፡፡ )
°
°
2). ዐብድርራህማን ቢን አምር አል-ዓውዛኢይ አሏህ ይዘንለት  (157 ዓ.ሒ) እንዲህ ብሏል ፦

"ኢማን በንግግር ቢሆን እንጂ ተስተካክሎ አይቆምም፡፡ ንግግር ተስተካክሎ አይቆምም ፥ በተግባር ቢሆንም እንጂ .. ኢማን ፣ ንግግር ፣ ተግባር ተስተካክለው አይቆሙም በኒያ ቢሆን እንጂ ሱናን የገጠመ ሆኖ፡፡

- ቀደምት ያለፋ ሠለፎቻችን በኢማንና በተግባር መሐል ልዩነት አያደርጉም ነበር፡፡ ነገር ግን #ኢማን ጠቅለል ያለ ስያሜ ሲሆን ልክ እነዚህን ሓይማኖታዊ ነገሮች ስያሜው ሰብስቦ እንደሚይዘው ነው፡፡ ተግባር ደግሞ እውነት ያደርገዋል፡፡

- በአንደበቱ ያመነ ፥ በቀልቡ ያወቀ ፥ ይህንንም ነገር በተግባሩ እውነት ያደረገ ፦ ይቺ ነች መበጠሻ የሌላት ዘለበት (ገመድ) ማለት፡፡

- በአንደበቱ የተናገረ ፣ በቀልቡ ግን ያላረጋገጠ ፣ በተግባሩም እውነት ያላደረገ ከሱ ተቀባይነት የለውም፡፡ በመጨረሻውም ቀን ከከሳሪዎች ነው፡፡

[ አል-ኢባናህ አልኩብሯ ፡ 1183 ]

°
°
3). ሱፍያን አስ-ሰውሪይ (161 ዓ.ሒ) አሏህ ይዘንለት  እንዲህ ብሏል ፦

" አህለሱናህ እንዲህ ይላሉ ፦ ተግባር በኢማን ቢሆን እንጂ አይፈቀድም፡፡ ኢማንም በተግባር እንጂ አይሆንም፡፡

( አልላለካኢይ ፡ 1792)

እንዲህም አለ ፦
" (አህሉ ሱናህ) እንዲህ ይላሉ ፦ ኢማን ንግግርና ተግባር ነው፡፡ ራሳቸውን ማጥራራትን በመፍራት ነው፡፡ ተግባር ደግሞ አይሆንም #በኢማን ቢሆን እንጂ፡፡ ኢማንም አይሆንም #በተግባር ቢሆን እንጂ፡፡

( አሽ-ሸሪዓህ ፡ 2062)

- እንደገናም እንዲህ ብሏል ፦ የፊቅሕ ሊቃውንቶች እንዲህ ይሉ ነበር ፦ ንግግር በተግባር እንጂ አይቆምም ፤ ንግግርና ተግባር አይቆምም በኒያ እንጂ ፤ ንግግር ፣ ተግባር ፣ ኒያ አይቆምም ሱናን በመግጠም እንጂ፡፡

(አል ኢባናህ አልኩብሯህ ፡ 1185)
°
°
4). ታላቁ ዓሊም ወኪዕ ቢን ጀራህ (197 ዓ.ሒ) አሏህ ይዘንለት

" የኢማን ባለቤቶች ፦ ንግግር በተግባርና በእምነት እንጂ አያብቃቃም፡፡ ብለዋል፡፡ "

( ዘሙ አልከላም ፡ 472)

5). ሱፍያን ኢብን ዑየይናህ አሏህ ይዘንለት (198 ዓ.ሒ)...

" ኢማን ንግግርና ተግባር ነው፡፡ (ይህ) ከኛ በፊት ከነበሩት የያዝነው ነው፡፡ ንግግርና ተግባር ነው፡፡ እሱም ንግግር አይሆንም ያለ ተግባር፡፡ "

(አስሱናህ ፦ የ ዐብድሏህን ፡ 716)
°
°
6). ኢማም ሙሐመድ ቢን ኢድሪስ አሽ-ሻፊዒይ አሏህ ይዘንለት (204)

" ከሶሓቦችም ፥ ከታብዕዮችም ከነሱ በኋላም ያገኘናቸው ሁሉ ኢማንን ንግግረሸ ፣ ተግባር ፣ ኒያ ፣ መሆኑንና አንደኛው ከሶስቶቹ እንደማያብቃቃ በሌላው ቢሀሆን እንጂ ብለው በጋራ ተስማምተዋል፡፡ "

( ላለካኢይ ፡ 1593) ብዙዎች ተርከውታል፡፡


______________________________

ለዛሬው በዚህ እናብቃና በክፍል ሶስት የሌሎች ዑለሞች ንግግር ይቀርባል፡፡ አሏህ በሐቅ ላይ ያፅናን ፥ ወንጀላችንንም ይማር፡፡

ወቢላሒ አት-ተውፊቅ !!!

© አቡ ሙስሊም ናሙስ

ቴሌግራም ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ፡ 👇

No comments:

Post a Comment

የኢብኑ ተይሚያህ አቋም በተሃኩም ላይ...

  ፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን...