☑️ * ዑዝር ቢል-ጀህልና የሙሂቡዲን ግልፅ ማደናገሪያዎች *
🔘ክፍል አንድ(1)
፨ በአሏህ ስም እጀምራለሁ፡፡ በረሱል ሰለሏሁ ወለይሒ ወሰለም ላይ ዘወትር የአሏህ እዝነት ይውረድ፡፡
በመጀመርያ በአሏህ የሚያጋራ ሰው ጃሒል ከሆነ ሙሽሪክ እንለዋለን ወይስ ሙስሊም እንለዋለን?" የሚለው ነጥባችን ሲሆን በሙሂቡዲንና በአጠቃላይ "ሙርጂኣዎች" "ጀህምዮች" "አሽዓርዮች" መንሐጅ መሠረት *ሙስሊም* ይባላል፡፡ በሐቅ ላይ መንገዳቸው ባደረጉ ሙስሊሞች ዘንድ ደግሞ "ሽርክ የሚሠራ ሰው ጃሒል ቢሆንም ሙሽሪክ ነው የሚል ግልፅ አቋም አለ፡፡ *
ይህ በሰፊው አብራራለሁ፡፡ አሁን ሙሂቡዲን የጻፈው መሆኑን የተላከልኝ ፅሁፍ ከማሥረጃ አንጻር እንመዝነው፡፡
[....] 👈 የሙሂቡዲን ፅሁፎች የማሥቀምጥበት ምልክቴ ሲሆን (.....) 👈ለማብራርያ የምጠቀማቸው ገለፃዎች የማሥቀምጥበት ምልክት ነው፡፡
ወቢላሂ አትተውፊቅ !!
[ ማንኛውም ሙስሊም ነኝ ያለ እና በአሏህ ብቸኛ ተመላኪነት እንዲሁም በመልክተኛው(ሰ.ዐ.ወ) መልክተኝነት ያመነ ሁሉ ሙስሊም ነው። እስልምናው በእርግጠኝነት ፀድቆለታል። ] ይላል፡፡
✉መልስ፦ ይህ ንግግር ሐቅ ነው፡፡ እኛም በአሏህ ብቸኛ ተመላኪነት በ"አንደበቱ ፥ በቀልቡ ፥ በሰውነቱ" ያረጋገጠ ሰው ፥ እንዲሁ በረሱልﷺ መልዕክተኝነት በትክክል ያረጋገጠ ሰው *ሙስሊም* ነው ብለን እናምናለን፡፡ እስልምናውም በእርግጠኝነት ፀድቆለታል፡፡
[ይህ ግለሰብ ኩፍር ወይም ሽርክ ላይ ከወደቀ ቀጥታ ከማክፈራችን በፊት የነገሩን ኩፍርነት እና ሽርክነት ሊብራራለት ይገባል።ከዚያ በኋላ ሽርኩ ላይ ከፀና ይከፍራል።] ይላል፡፡
✉መልስ፦ እንግዲህ የመንገዳችን ልዩነት ከዚህ ይጀምራል፡፡ ይህ በአሏህና በመልዕክተኛው ﷺ አምኛለሁ ሲል የነበረው ሰው ይህ እምነቱ አፍርሶ በአሏህ ቢያሻርክና ከአሏህ ውጪ የሆነ ሌላ ህያውም ይሁን ግዑዝ ነገር ቢያመልክ "ሙሽሪክ" አይሆንም አሉ፡፡ እኛ ደግሞ ሙሽሪክ ይሆናል አልን፡፡ የነገሩ ሽርክነት ፥ ኩፍርነት ተነግሮት እምቢ ካለ እንጂ ሙሽሪክ አይሆንም አሉ፡፡ ይህ ባጢል ነው፡፡ ከቁርኣን ጋር በግልፅ የሚጋጭ እምነት ነው፡፡ እንዴት ከቁርኣን እንደሚጋጭ የሚከተሉት ማሥረጃዎች አስቀምጣለሁ፡፡ ከዚያ በፊት ሁለት ማጭበርበርያዎች ግልፅ መሆን አለባቸው፡፡ ሙሂቡዲንም ሆነ ሌሎችም ሙርጂኣዎች ስለተክፊር ሲነሳ ሁለት ሹብሃዎች ያቀርባሉ፡፡
1ኛው). የቀደምት ሙሽሪኮች ላይ የወረደ አንቀጽ ፥ እናንተ ወደ እስልምና የገባ ሰው ላይ ትጠቀማላቹህ፡፡ ይህ ቂያስ ደግሞ ውድቅ ነው አለ ሙሂቡዲን፡፡ ለምን ሲባል የሰጠው መልስ [ ልዩነት ከመኖር ጋር ቂያስ ውድቅ ነው፡፡ ያኛው ከመሠረቱ ካፊር ነው፡፡ ወደ ኢስላም አልገባም፡፡ ይህኛው ደግሞ ወደ ኢስላም ገባ አለ፡፡ ] ስለቂያስ የጠቀሰው ቃዒዳ ትክክል ቢሆን የተጠቀመበት ቦታ ግን ስህተት ነው፡፡ ከዚህ ንግግሩ የምንረዳው አሏህ ሰዎችን ሲፈጥራቸው ከመሠረቱ ሙሽሪክ ፥ ክርስቲያን ፥ አይሁድ ፤ መጁስ አድርጎ ይፈጥራቸዋል የሚል መልዕክት ነው፡፡ ይህ ቁርኣንን ሃዲስን ውድቅ የሚያደርግ ባጢል ንግግር ነው፡፡ ምክንያቱም አሏህ ሁሉም የሰው ልጅ በእስልምና ላይ ነው የሚፈጥረው ፥ እንዲወለድ የሚያደርገው፡፡ ሰው ልጆች መሠረታቸው፥ አፈጣጠራቸው ተውሂድ ላይ መሆኑን፡፡ ይህ ቁርኣንና ሐዲስ የተረጋገጠ ሐቅ ነው፡፡ ሁሉ የቀደምት ሙሽሪክ ፥ ነሷራ ፥ አይሁድ ፥ መጁሲም ይሁን ሲፈጠር በትክክለኛ እስልምና ላይ ነው የሚፈጠረው፡፡ ማሥረጃችን አሏህ እንዲህ ብሏል፦
30:30 " ወደ እውነት ተዘንባይ ኾነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን (ሃይማኖት ያዟት)፡፡ የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፡፡ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡"
فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا فِطْرَةَ اللَّهِ الَّتِي فَطَرَ النَّاسَ عَلَيْهَا لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ اللَّهِ ذَلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ وَلَكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ (30)
-ይህ የቁርኣን አንቀጽ ሲብራራ ( فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّين ) የሚለው ዲንህን ለአሏህ ብቻ አጥራ ፥ ስራህም አስተካከክል ማለት ሲሆን (حَنِيفًا) የሚለው ደግሞ *ሙስተቂመን* ወይም *ቀጥ ያልክ ሆነህ የሚል ትርጉም አለው፡፡ ( فِطْرَةَ) የተባለውም "ዲን" ሲሆን እኛ የሰው ልጆች የተፈጠርንበት ኃይማኖት ማለት ነው፡፡ እሱም አሏህ ከአደም ጀርባ ሁሉም ሰዎች ላይ የያዘው ቃልኪዳኑ ሲሆን #ኢስላም ነው፡፡
-የአሏህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል ፦ " የሚወለድም ሰው በተፈጥሮው (ዲን) ላይ ሆኖ ይወለዳል፡፡ ወላጆቹም አይሁድ ፥ ነስራኒይ(ክርስቲያን) ፥ ወይም መጁስ(እሳት) አምላኪ ያደርጉታል፡፡"
" من يولد يولد على الفطرة ، فأبواه يهودانه أو ينصرانه أو يمجسانه.
• ከዚህ በግልፅ የምንረዳው ነገር ሰው ልጆች ሁሉ የጠመሙት የከፈሩት ሙስሊም ከነበሩ በኋላ ነው እንጂ ሙሽሪክ ሆኖ የሚወለድ የለም፡፡ እነ አቡ ጀህል ፥ እነ አቡ ለሃብ ሌልችም የቁረይሽ ሙሽሪኮች ሲወለዱ ሙስሊሞች ሆነው ተወልደው ነበር፡፡ ግን የአባቶቻቸው ፥ የአያቶቻቸው ሽርክ በጅህልናቸው ምክንያት ተክትለው ሰሩ፡፡ በዚህም ሙሽሪክ ሆኑ፡፡ ሙሽሪክ የሆኑት ሙርጂኣዎች እንደሚሉት *ተነግሯቸው እምቢ ሽርክ ይሻለናል* ብለው አይደለም፡፡ የረሱል ሰዐወ ዳዕዋ ሳይደርሳቸውም ሙሽሪክ ነበሩ፡፡ ዳዕዋ አልቀበልም ካሉ በኋላም የበለጠ ሙሽሪክ ሆነዋል፡፡
- በድሮ ሙሽሪኮችና አሁን ሙስሊም ነን ብለው ሽርክ በሚሠሩት መካከል ልዩነት አለ የተባለውም ባጢል ነው፡፡ ዝርዙር ቀጥለው ያንብቡ፡፡
1ኛው). በመጀመርያ መታወቅ ያለበት ነገር አሏህ የሰው ልጆች ሁሉ በትክክለኛ ኃይማኖት ላይ ነው የፈጠራቸው፡፡ ቀጥ ባለው የተፈጥሮ ኃይማኖት እስልምና ላይ ነው የተፈጠርነው፡፡ በአለም የሚገኙ ነሷራዎች ፥ አይሁዶች ፥ መጁሶች (እሳት አምላኪዎች) ፥ ሙሽሪኮች ሁሉም ሙስሊም ሆነው ነው የተፈጠሩት የተወለዱት፡፡
በኋላም ቤተሰቦቹ ይህን ታዳጊ ህጻን አንዱ ነሷራ ያደርገዋል፡፡ አንዱ አይሁድ ያደርገዋል፡፡ አንዱ ልጁን መጁስ ያደርገዋል፡፡ የአሏህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል ፦
كل مولود يولد على الفطرة
"ሁሉም የሚወለደው በተፈጥሮ (እምነቱ) ላይ ነው፡፡" ብለዋል፡፡ አሏህም በቁርኣን የሰው ልጅ በትክክለኛ ዲን ላይ እንደፈጠረው ገልፇል፡፡ ሽርክ ወይም ኩፍር የሚንላቸው እስልምናን የሚያፈርሱ ነገሮች *ጧሪእ* ወይም ካለመኖር በኋላ የተገኙ ነገሮች ናቸው፡፡ እንጂ ከሰውዬው ጋር አብሮ የተፈጠሩ ነገሮች አይደሉም፡፡
-አል-ቃዲይ ኢብን አልዐረቢይ(543 ዓ.ሂ) እንዲህ ብሏል ፦ " አጠቃላይ ካፊሮች መሠረታቸው ሲታይ *ሙርተዶች* ናቸው፡፡ እነዚህ ኩፋሮች መጀመርያ ላይ "በተውሂድ" ላይ ነበሩ፡፡ አጥብቀውም ይዘውት ነበር፡፡ ከዚያም ከዚያም ተመለሱ፡፡ በዚህም ተገደሉ ፥ እንዲማረኩም ተደረጉ፡፡ " ይላል፡፡
📚ዐሪዶቱል አህወዚይ፡ 10/55
ስለዚህ ሙሥሊም ነኝ እያለ በአሏህ የሚያጋራውም ፥ ይህ በመሠረቱ ካፊር ያልነውም በመካከላቸው ልዩነት የለም፡፡ ሁለቱም በመጀመርያ የተፈጠሩበት እስልምና ትተው በጅህልናቸው ከአሏህ ውጭ ያለ ነገር ያመልካሉ፡፡
2ኛው). ከመጀመርያው ካፊር ነበር ያልነው ሰው ሽርክ ተግብሯል ፥ ልክ ራሱ ከሙሥሊሞች እየቆጠረ ያለው ሰውም *በአሏህ እንደሚያጋራው ሁሉ፡፡ ይህ ሁለቱም አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ሲሆን የሚለያያቸው ነገር የለም፡፡ ያ ሙሥሊም ነኝ የሚለው ሰውዬ "ሶላት መሥገዱ" "ዘካ መሥጠቱ" ጾም መጾሞ" የመሳሰሉል ነገሮች ከሽርክ ጋር ግልጽ ማድረጉ ምንም ቦታ የሚሠጠው አይደሉም፡፡ ሽርክ ስራ ሁሉ ውድቅ ያደርጋልና፡፡ ያኛውም እኮ ጭንቀት በያዘው ጊዜ አሏህን ብቻ ነው የሚጠራው፡፡ ግን ከሽርክ ጋር በመሆኑ ዒባዳው ውድቅ ሆነ፡፡ አሏህ እንዲህ ብሏል ፦
31:32 " እንደ ጥላዎችም የሆነ ማዕበል በሸፈናቸው ጊዜ አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይጠሩታል፡፡ "
(31) وَإِذَا غَشِيَهُمْ مَوْجٌ كَالظُّلَلِ دَعَوُا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ.
• እንደገናም ሙሽሪኮች በሌሎችም በሰላም ጊዜያቸውም ሐጅ ፥ ዑምራ የመሣሰሉ ነገሮች ይሰሩ ነበር፡፡ ግን ይህ የሚሠሩት በጣዖቶቻቸው ላይ እያጋሩ ነው፡፡ ሙስሊም ነኝ ብሎ ሽርክ ላይ የተዘፈቀውም እንደዚሁ ነው፡፡
3ኛው). በመሠረቱ ካፊሩ የምንለው (የጥንቱ ሙሽሪክ ) የሚሠራው ስራ ምን እንደሆነ ያውቅ ነበር፡፡ *ኢስቲጋሳው* *እርዱ* ያውቅ ነበር፡፡ ልክ እንደዚሁ ሙስሊም ነኝ እያለ የሚያጋራውም *ኢስቲጋሳው* *እርዱ* ሲፈፅም የስራው ምንነት ያውቃል፡፡ ሀለቱም ወደአሏህ ያቃርበናል ብለው ይሰሩታል፡፡ ይህ ሌላኛው አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ነው፡፡
4ኛው). የጥንቱ ሙሽሪክ ሲሰራው የነበረው ሽርክ *የወሳኢጥ እና የተቀሩብ* ሽርክ ነው፡፡ ይህ ማለት በነሱ እና በአሏህ መካከል ጉዳያችን የሚያቃርቡልን ብለው የሚይዟቸው ተጋሪዎች ነበሩ፡፡
39:4 " እነዚያም ከእርሱ ሌላ (ጣዖታትን) ረዳቶች የያዙት «ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቀርቡን እንጅ ለሌላ አንገዛቸውም»
(ይላሉ)፡፡ "
وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِهِۦٓ أَوْلِيَآءَ مَا نَعْبُدُهُمْ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَآ إِلَى ٱللَّهِ زُلْفَى
• ልክ እንደዚሁ ሙስሊም ነኝ እያለ በአሏህ የሚያጋራውም ሼይኾቼ ፥ ወልዮቼ ፥ ነብያችን የተለያዩ ነገሮች ወደአሏህ ያቃርቡኛል ብሎ ያመልካል፡፡ ይህ ሌላኛ አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ነው፡፡ ለዚህ ነው በሁክምም አንድ ናቸው የምንለው፡፡
5ኛው). ሁለቱም (የድሮው ሙሽሪክም ሆነ ሙስሊም ነኝ እያለ በአሏህ የሚያጋራው ) ሁለቱም ጃሒሎች ናቸው፡፡ አለማወቃቸው የማያውቁ ጃሂሎች ናቸው፡፡ ሁለቱም ባሉበት ሽርክ ላይ *እኛ ትክክለኛው መንገድ ላይ ነን* የሚሉ ናቸው፡፡ እነሱ ጠማማ ሆነው ሳለ፡፡ ይህም ሌላ ሁለቱም ሽርክ ሰሪዎች አንድ የሚያደርጋቸው ነው፡፡ በሁክም ላይም አንድ አይነት ሁክም እንድንሰጥ ያስገድደናል፡፡ አሏህ እንዲህ ብሏል ፦
7:30 " እነርሱ ሰይጣናትን ከአላህ ሌላ ረዳቶች አድርገው ይዘዋልና፡፡ እነርሱም (ቅኑን መንገድ) የተመራን ነን ብለው ያስባሉ፡፡"
إِنَّهُمُ اتَّخَذُوا الشَّيَاطِينَ أَوْلِيَاءَ مِنْ دُونِ اللَّهِ وَيَحْسَبُونَ أَنَّهُمْ مُهْتَدُونَ (30)
፨ሌላው የቁርኣን አንቀጾች ለድሮዎች የወረደው ላሁን ላሉት ማሥረጃ መጠቀም አይቻልም ለተባለው ይህን አንብቡ👇
•ነጥብ (1) :- የቁርአን አንቀፆች የሚያሰሰተላልፉት መልዕክት በወረዱበት ውስን ምክንያት ሳይሆን በሚያስተላልፉት ጥቅል መልዕክት ነው የሚታዩት፡፡
( العبرة بعموم اللفظ ليست بخصوص السبب )
• "ዋናው ነገር የቁርአን አንቀፆች በያዙት ጥቅል ንግግር እንጂ በተነገሩበት ውስን ምክንያት አይደለም የሚታዩት፡፡
فمن فعل فعل المُشركين تتناوله الآيات التي نزلت فيهم وينطبق عليه الوصف الذي وصفهم الله به .
• ሙሽሪኮች የሚሰሩትን ስራ የሰራ ሰው ፥ እነዚህ በሙሽሪኮች ላይ የወረዱ አንቀፆች ያገኙታል፡፡ እነሱን አሏህ የገለፃቸው ባህሪን በሱም ላይ ይረጋገጣል፡፡ ይህ በርካታ የዕውቀት ባለቤቶች የገለፁት ና ያስቀመጡት መርሆ ነው፡፡ ሽርክ ያው ሽርክ ነው፡፡ የሚሠራው ሰው ወይ ቦታ ወይም ዘመን ቢለያይም እንኳን፡፡
• ከዚህ የምንረዳው ነጥብ አሏህ በቁርአን የሚጠቅሳቸው አንቀፆች የሙሽሪኮችን ሁኔታና ፍርዳቸው ፥ በዛሬ ዘመን የነሱ ስራ የሚሠራ ነው በራሱ በቀጥታ ይመለከተዋል፡፡ እነዚያም ከአሏህ ውጪ ያለ ነገር ያመልኩ ነበር ፥ እነዚህም ከአሏህ ውጪ ያለን ነገር ያመልካሉ፡፡ እነዚያ ወደአሏህ ለመቃረብ ብለን ነው የሚል መከራከርያ ያመጣሉ እነዚህም አናመልካቸው ለመቃረብ ነው፡፡
• እንደው የዛሬዎቹ ከድሮዎቹ ሽርካቸውም የከፋ ነው፡፡ ልክ ሼይኹል ኢስላም ኢብን ዐብድልወህሃብ እንደገለፁት፡፡
قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله فيمن جعل الآيات النازلة خاصة لمن نزلت بسببه ولا يشمل النوع أو المثال فقال
• ታላቁ ዐሊም ሼይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ (አሏህ ይዘንለት) እነዚህ የወረዱ አንቀፆች በነሱ ሰበብ ለወረደባቸው ሰዎች ብቻ የተወሰነ ነገር ስለሚያደርጉ ሰዎች ፥ ሌሎችን አካትትም ስለሚሉት እንዲህ ብሏል...
" አንድ ሙስሊም "ዚሃር"ን በተመለከተ የመጡ አንቀፆች ውስጥ አውስ ቢን አስሷሚት እንጂ ሌላ አይገባም ብሎ አይናገርም፡፡ የ"መራገም" አንቀፆችን ደግሞ ማንመሸ አያካትትም ዓሲም ቢን ዐዲይ እንጂ (ብሎ አንድ ሙስሊም አይናገርም) ፡፡ ኩፋሮችን የሚወቅሱ አንቀፆች የቁረይሽ ኩፋር እንጂ ሌላ አይገባም የመሳሰለው .. ይህ ሙስሊምም ሆነ አዕምሮ ያለው ሰው የሚናገረው ነገር አይደለም፡፡ "
[ መጅሙዕ አልፈታዋ ፡ 16/148]
: ( فلا يقول مسلم أن آية الظهار لم يدخل فيها إلا أوس بن الصامت وآية اللعان لم يدخل فيها إلا عاصم بن عدي وأن ذم الكفار لم يدخل فيه إلا كفار قريش ونحو ذلك مما لا يقوله مسلم ولا عاقل ) [الفتاوى 16/ 148].
• ኢማም አልሙጀዲድ አቡ ቡጠይን አን-ነጅዲይ (አሏህ ይዘንላቸው) እንዲህ ብሏል..
قال الإمام المجدد أبو بطين النجدي رحمه الله :
( أما قول من يقول أن الآيات التي نزلت بحكم المشركين الأولين فلا تتناول من فعل فعلهم فهذا كفر عظيم )
" ሙሽሪኮችን በተመለከተ የወረዱ አንቀፆች የነሱን ስራ የሰራ ሰው አያገኘውም የሚል ሰው ይህ ትልቅ የሆነ ኩፍር (ክህደት) ነው፡፡ "
، قال : ( ويلزم منه أن الحدود المذكورة في القرآن والسنة لأناس كانوا وانقرضوا ! فلا يُحد الزاني اليوم ولا تقطع يد السارق وبطل حكم القرآن ) [الدرر 10/418]
• እንዲህም ብለዋል ፦ " ይህ የሚያሲዘው በቁርአን ፥ በሃዲስ የተጠቀሱ ሓዶች (ቅጣቶች) ለነዚያ ድሮ ለጠፉት (ብቻ) ነበር ማለት ነው፡፡ ዚና የሰራ ሐድ አይቆምበትም፡ የሰረቀም እጁ አይቆረጥም፡፡ የቁርአን ሁክም ውድቅ ተደረገ ማለት ነው፡፡ "
[መጅሙዕ አልፈታዋ ፡ 10/418]
•ሼይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አልዑሰይሚን እንዲህ ብሏል...
[ أن معنى قولنا العبرة بعموم اللفظ لا بخصوص السبب ] يعني أن الحكم لا يختص بعين الذي ورد من أحله ، وإنما يعم من كان مثل حاله. وقد نص على هذه القاعدة ابن دقيق العيد في شرح الحديث في العمدة وهو واضح.
📚 الكنز الثمين في تفسير ابن عثيمين :٥٤٤
" አልዒብራህ ቢዑሙሚ ለፍዚ ፥ ላ ቢኹሱሲ ሰበብ " የሚለው ንግግራችን ትርጉሙ ፦ ይህ ማለት አንድ ብይን (ሁክም) በዚያ በርሱ ምክንያት ለመጣበት ነገር ብቻ አይገደብም፡፡ ነገርግን የርሱን ሁኔታ የተመሳሰለ ሁሉ የሚያጠቃልል ነው፡፡ ይህን ቃዒዳ (መርሆ) በተመለከተ ኢብን ደቂቅ አልዒድ ዑምዳ ውስጥ ሐዲስ ሲያብራራ መረጃ አድርጎ ጠቅሶታል፡፡ እሱ ግልፅ ነገር ነው፡፡
[ አልከንዝ አስሰሚን ፊ ተፍሲር አልዑሰይሚን ፡ 544]
° ስለዚህ የቁርአን አንቀፆች የድሮ ሙሽሪክ ላይ የወረደ ነው ዛሬ ላሉት አይሆንም የሚለው ውድቅ የሆነ ሹብሃ ነው፡፡ የቀደምት ሙሽሪኮች ስራ የሰራ ሁሉ ያካትታል ፡፡
ሌሎች ማደናገርያዎቹ ትክክለኛውን መንገድ ካብራራን በኋላ እናያቸዋለን፡፡
🔘ወቢላሒ አትተውፊቅ🔘
✍🏼 አቡ ሙስለሊም
📱@Aqida_muwehid
☑️ abumuslim760.blogspot.com
Thursday, November 28, 2019
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
የኢብኑ ተይሚያህ አቋም በተሃኩም ላይ...
፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን...
-
🔖 በአሏህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩህና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ በዚህ ሁፍ በአሏህ እርዳታ በመታገዝ ወደ ጧጉት መፋረድ ምን እንደሆነ እና ወደ ጧጉትም መፋረድ ያለው ሁክም እንመለከታለን፡፡ በምን አይነት...
-
✔ በአሏህ ስም እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ الحمد لله وصلاة وسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه ومن والاه ..... أما بعد ° በዚህ አጠር ያለ ትምህርት ...
-
📌 [ አል-መድኸሉ ኢላ አልጃሚዕ ፊ ኩትቢ አል ኢማን ወርረድ ዓለል ሙርጂአህ ] -------------- ክፍል _ 2 -------------- بسم الله الحمد لله والصلاة والسلام على رسول ...
No comments:
Post a Comment