☑️ * ዑዝር ቢል-ጀህልና የሙሂቡዲን ግልፅ ማደናገሪያዎች *
🔘ክፍል አንድ(2)
፨ በአሏህ ስም እጀምራለሁ፡፡ በረሱል ሰለሏሁ ወለይሒ ወሰለም ላይ ዘወትር የአሏህ እዝነት ይውረድ፡፡
-በዚህ ፅሁፍ በቀጥታ የአህሉ ሱናዎች አቋም እናረጋግጣለን፡፡ ሙኻሊፎች (ትክክለኛውን መንገድ) የሚቃረኑ ሰዎች ንግግር ደግሞ በስተመጨረሻ እንመለከተዋለን፡፡
[ ይህ (ሙስሊም ነኝ የሚለው) ግለሰብ ኩፍር ወይም ሽርክ ላይ ከወደቀ ቀጥታ ከማክፈራችን በፊት የነገሩን ኩፍርነት እና ሽርክነት ሊብራራለት ይገባል።ከዚያ በኋላ ሽርኩ ላይ ከፀና ይከፍራል።] ይላል ሹብሃው፡፡
ይህ ባጢል አባባል ከቁርኣን የተለያዩ አስረጅ የሆነ አንቀጾች እያመጣን ውድቅ እናደርገዋለን፡፡
•ማሥረጃ(1) አሏህ እንዲህ ብሏል:
12:103 «አብዛኛዎቹም ሰዎች (ለማመናቸው) ብትጓጓም የሚያምኑ አይደሉም፡፡»
12:104 «በእርሱም (በቁርአን) ላይ ምንም ዋጋ አትጠይቃቸውም፡፡ እርሱ ለዓለማት ግሳጼ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡»
12:105 «በሰማያትና በምድርም ካለችው ምልክት ብዙይቱ እነሱ ከርሷ ዘንጊዎች ኾነው በርሷ ላይ ያልፋሉ፡፡»
12:106 «አብዛኞቻቸውም፤ እነሱ አጋሪዎች (ሙሽሪኮች) ኾነው እንጂ በአላህ አያምኑም፡፡»
وَمَا أَكْثَرُ النَّاسِ وَلَوْ حَرَصْتَ بِمُؤْمِنِينَ (103) وَمَا تَسْأَلُهُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ إِنْ هُوَ إِلَّا ذِكْرٌ لِلْعَالَمِينَ (104) وَكَأَيِّنْ مِنْ آَيَةٍ فِي السَّمَوَاتِ وَالْأَرْضِ يَمُرُّونَ عَلَيْهَا وَهُمْ عَنْهَا مُعْرِضُونَ (105) وَمَا يُؤْمِنُ بِاللَّهِ إِلَّا وَهُمْ مُشْرِكُونَ.
•ይህ አንቀፅ የሚያስተላልፈው መልዕክት ምንድነው? ከዑዝር ቢል-ጀህል ጋር ምን አገናኘው?፡፡ ይህን የቁርኣን አንቀጽ የወረደበት ምክንያት አንዱ "ሙሽሪኮች" በካዕባ ላይ ጠዋፍ ያደርጉ ነበር፡፡ እዛም ተልቢያ ይሉ ነበር፡፡ ተልቢያውም * ለበይክ ላ ሸሪከ ለክ፡፡ ኢላ ሸሪከን ሁወ ተምሊኩሁ ወማ መለክ፡፡* ይሉ ነበር፡፡ (ሙስሊም እንደዘገበው)፡፡ ታድያ እነዚህ ሙሽሪኮች ከነበራቸው እምነት መካከል "ሰማይ ማን ነው የፈጠረው?" "ምድር ማን ፈጠረው?" ተብለው ሲጠየቁ *አሏህ ነው* ብለው ይመልሱ ነበር ከዚህ ጋር ግን ሙሽሪኮች ናቸው፡፡ በአሏህ ሩቡቢያ ቢያረጋግጡም ፥ ከርሱ ውጪ ያለ ነገር በማምለካቸው "ሙሽሪክ ሆኑ"፡፡ ይህን አንቀጽ የወረደው በመካ ነው፡፡
ረሱል ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በመካ እያሉ የተውሂድ ዳዕዋ ሁሉም ቦታ አልተዳረሰም ነበር፡፡ ሆኖም ግን አሏህ በአብዛኞቹ ላይ ሙሽሪክ መሆናቸው ገለጸ፡፡ ይህ እንኳን እንደኛ ዘመን ያሉ ቁርኣንና ሀዲስ የደረሳቸው ሰዎች ይቅርና ሪሳላ ያልደረሳቸውም ሰዎች ቢሆኑ በአሏህ እስካጋሩ ድረስ ሙሽሪክ ይባላሉ፡፡
እንደሚባለው ከሆነ እነዚህ ሰዎች የሚሠሩት ስራ ሽርክና ኩፍር መሆኑ ሳይነገራቸው "ሙሽሪክ" አይባሉም ከተባለ ታድያ ለምን አሏህ ሙሽሪክ አላቸው? ረሱል (ሰዐወ) የረሱልነት ማዕረግ ሳይሰጣቸው በፊት ፥ ዳዕዋ ሳይጀምሩ በመካ ዙሪያ ጣዖታት የሚያመልኩ ሰዎች "ሙስሊም" ነበሩ? ሑጃ ስላልደረሳቸው፡፡ ይህ መጅኑን የሆነ ሰው እንጂ አይናገረውም፡፡
ምናልባት እነሱ እኮ መጀመርያ ወደ ኢስላም አልገቡም ትለኝ ይሆናል፡፡ እኔ የምልህ ደግሞ እነዚህ ሙሽሪኮች መጀመርያም ሙስሊም ነበሩ፡፡ የተፈጥሮ ሃይማኖታቸው እስልምና ነው፡፡ ግን የአባቶቻቸው መንገድ በጅህልና ተከትለው ነው ሙሽሪክ የሆኑት፡፡ ልክ እንደዛሬዎቹ፡፡ ስለዚህ ያለበት ስራ ሽርክ መሆኑ ተነግሮት የሚለው ሸርጥ ባጢል ነው፡፡
•ማሥረጃ(2)..አሏህ እንዲህ ብሏል
6:137 " እንደዚሁም ከ(ሙሽሪኮች) አጋሪዎቹ ለብዙዎቹ፤ ተጋሪዎቻቸው ሊያጠፉዋቸው ሃይማኖታቸውንም በእነሱ ላይ ሊያቀላቅሉባቸው (ሊያመሳስሉባቸው) ልጆቻቸውን መግደልን አሳመሩላቸው፡፡ አላህም በሻ ኖሮ ባልሠሩት ነበር፡፡ ከቅጥፈታቸውም ጋር ተዋቸው፡፡" አንዐም፡137
وَكَذَلِكَ زَيَّنَ لِكَثِيرٍ مِنَ الْمُشْرِكِينَ قَتْلَ أَوْلَادِهِمْ شُرَكَاؤُهُمْ لِيُرْدُوهُمْ وَلِيَلْبِسُوا عَلَيْهِمْ دِينَهُمْ وَلَوْ شَاءَ اللَّهُ مَا فَعَلُوهُ فَذَرْهُمْ وَمَا يَفْتَرُونَ.
•አሏህ በዚህ አንቀፅ እየነገረ ያለው እነዚያ ሙሽሪኮች ድህነትን ፈርተው ፥ ወይሌ " ልጆቻቸውን መግደል" "ሴት ልጆችን ከነ-ህይወታቸው መቅበር " የመሳሰለው አስቀያሚ ለብዙ ሙሽሪኮች መልካም ሆኖ ታያቸው ይላል፡፡ ይህን አስነዋሪ ስራ ይሰሩ የነበሩ ሰዎች በብዙ የተለያየ የአረቦች አካባቢ የነበሩ ናቸው፡፡ እንደ ማንኛውም ሰው በእስልምና ላይ ነው የተወለዱት ፥ ሆኖ ትክክለኛ የኢብራሒም ዲን ባለማወቃቸውና በአሏህ በማጋራታቸው "ሙሽሪክ" ሆኑ፡፡ አሏህም ቁርኣን ሳይመጣ በፊት ሙሽሪክ እንደነበሩ እየነገረን ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው በጅህልና ሽርክ ሰርቶ "ይህ ሽርክ መተው አለብህ" ተብሎ ባይነገረውም እንኳን ሙሽሪክ ይሆናል፡፡
፨ እነዚህ እኮ *ላ ኢላሃ ኢለሏህ* ይላሉ ትለኝ ይሆናል፡፡ ይህ *ላ ኢላሃ ኢለሏህ* የሚጠቅማቸው ከሽርክ ቢርቁ ነበር፡፡ ካልሆነማ በሽርክ ተጨማልቆ ላ ኢላሃ ኢሏህ ማለቱ ዋጋ የለውም፡፡
•ማሥረጃ(3)...አሏህ እንዲህ ብሏል፦
16:35 «እነዚያም (ጣዖታትን) ያጋሩት «አላህ በሻ ኖሮ ከእርሱ ሌላ እኛም አባቶቻችንም ምንንም ባልተገዛን ነበር፤ ያለእርሱም (ትእዛዝ) ምንንም እርም ባላደረግን ነበር አሉ፡፡» እነዚያም ከነሱ በፊት የነበሩት እነደዚሁ ሠሩ፡፡ በመልክተኞቹም ላይ ግልፅ ማድረስ ብቻ እንጂ ሌላ የለባቸውም፡፡»
وَقَالَ الَّذِينَ أَشْرَكُوا لَوْ شَاءَ اللَّهُ مَا عَبَدْنَا مِنْ دُونِهِ مِنْ شَيْءٍ نَحْنُ وَلَا آَبَاؤُنَا وَلَا حَرَّمْنَا مِنْ دُونِهِ مِنْ شَيْءٍ كَذَلِكَ فَعَلَ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ فَهَلْ عَلَى الرُّسُلِ إِلَّا الْبَلَاغُ الْمُبِينُ (35)
• እነዚህ ሰዎች ከዚህ ሽርክ ተከልከሉ ተብለው እምቢ ብለው አይደለም * ሙሽሪክ * የተባሉት፡፡ ነገርግን በጅህልናቸው ምክንያት አያቶቻቸውን ተከትለው ሽርክ በመሥራታቸው ነበር፡፡ ለጃሒልማ ዑዝር ቢኖረው ኖሮ እነዚህ *ሙስሊም* ይባሉ ነበር፡፡ ምክንያቱም ጃሂሎች ናቸው ተውሂድ አያውቁም፡፡ ግን ሑጃ ደርሷቸው እንቢ ባይሉም አሏህ "ሙሽሪክ አላቸው፡፡
• ዛሬ እነዚህ ሙስሊም ነን እያሉ በአሏህ የሚያጋሩት እኮ መልዕክተኛ ተላከላቸው ፥ ቁርኣን ደረሳቸው ፥ ሆኖም በአሏህ ያጋራሉ፡፡
፨ ስለዚህ [ ከማክፈራችን በፊት ስለ ሚሠራው ሽርክ ፥ ስለ ሚሠራው ኩፍር እናስረዳዋለን፡፡ አልመለስም ካለ እናከፍረዋለን፡፡ ] የተባለው አባባል ከነዚህ የቁርአን አንቀፆች ጋር የሚጣረስ ነው፡፡
ምክንያቱም እነዚህ አረቦች ምንም መልዕክተኛ ሳይላክላቸው ፥ የሚያስረዳቸው ዓሊም ሳይገኝ በሰሩት ሽርክ ሙሽሪክ ተብለዋልና፡፡ ኢንሻ አሏህ ይቀጥላል፡፡
🔘ወቢላሒ አት-ተውፊቅ🔘
✍🏼አቡ ሙስሊም
☑️ @aqida_muwehid
Thursday, November 28, 2019
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
የኢብኑ ተይሚያህ አቋም በተሃኩም ላይ...
፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን...
-
🔖 በአሏህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩህና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ በዚህ ሁፍ በአሏህ እርዳታ በመታገዝ ወደ ጧጉት መፋረድ ምን እንደሆነ እና ወደ ጧጉትም መፋረድ ያለው ሁክም እንመለከታለን፡፡ በምን አይነት...
-
✔ በአሏህ ስም እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ الحمد لله وصلاة وسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه ومن والاه ..... أما بعد ° በዚህ አጠር ያለ ትምህርት ...
-
📌 [ አል-መድኸሉ ኢላ አልጃሚዕ ፊ ኩትቢ አል ኢማን ወርረድ ዓለል ሙርጂአህ ] -------------- ክፍል _ 2 -------------- بسم الله الحمد لله والصلاة والسلام على رسول ...
No comments:
Post a Comment