Friday, November 29, 2019

☑️ * ዑዝር ቢል-ጀህልና የሙሂቡዲን ግልፅ ማደናገሪያዎች *

🔘ክፍል አንድ(3)

፨ በአሏህ ስም እጀምራለሁ፡፡ በረሱል ሰለሏሁ ወለይሒ ወሰለም ላይ ዘወትር የአሏህ እዝነት ይውረድ፡፡

-በዚህ ፅሁፍ በቀጥታ የአህሉ ሱናዎች አቋም እናረጋግጣለን፡፡ ሙኻሊፎች (ትክክለኛውን መንገድ) የሚቃረኑ ሰዎች ንግግር ደግሞ በስተመጨረሻ እንመለከተዋለን፡፡

[ ይህ (ሙስሊም ነኝ የሚለው)  ግለሰብ ኩፍር ወይም ሽርክ ላይ ከወደቀ ቀጥታ ከማክፈራችን በፊት የነገሩን ኩፍርነት እና ሽርክነት ሊብራራለት ይገባል።ከዚያ በኋላ ሽርኩ ላይ ከፀና ይከፍራል።] ይላል ሹብሃው፡፡

ይህ ባጢል አባባል ከቁርኣን የተለያዩ አስረጅ የሆነ አንቀጾች እያመጣን ውድቅ እናደርገዋለን፡፡

•ማሥረጃ(4) አሏህ እንዲህ ብሏል:

5፡103 " ከበሒራ ከሳኢባም ከወሲላም ከሓምም አላህ ምንንም (ሕግ) አላደረገም፡፡ ግን እነዚያ የካዱት በአላህ ላይ ውሸትን ይቀጣጥፋሉ፡፡ አብዛኞቻቸውም አያውቁም፡፡" ሱራ አልማኢዳ፡103
مَا جَعَلَ اللَّهُ مِنْ بَحِيرَةٍ وَلَا سَائِبَةٍ وَلَا وَصِيلَةٍ وَلَا حَامٍ وَلَكِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا يَفْتَرُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَأَكْثَرُهُمْ لَا يَعْقِلُونَ (103)

• ከዚህ አንቀፅ የምንረዳው አሏህ (ሱብሐነሁ ወተዐላ) እዚህ ሃራም ነገሮች ሰዎች ዲን አድርገው እንዲይዙ እንዳልደነገገ እየነገረን ነው፡፡ ነገር ግን እነዚያ #ካፊሮች ይህ ውሸት ወደ አሏህ በማሥጋት ይቀጥፋሉ፡፡ በዚህ የምንረዳው እነዚህ የዐረብ ሙሽሪኮች በሚሠሩት ኩፍርና ሽርክ መልዕክተኛ መጥቶ ሳያስጠነቅቃቸው ፥ ወይም ሽርክ ላይ እንደሆኑ ሳይብራራላቸው #ሙሽሪክ_ካፊር ተብለዋል፡፡

ሙሽሪክ ያስባላቸው በጅህልናቸው ምክንያት ሽርክ በመሥራታቸው እንጂ *ተዉ ሽርክ አትስሩ ሲባሉ እንቢ ሽርክ ይሻለናል* ብለው አይደለም፡፡ ምክንያቱም ረሱል (ሰለሏሁ ዐለይሒ ወሰለም) ከመላካቸውም በፊት ሙሽሪክ ተብለዋል፡፡

ምናልባት እነዚህ ሙስሊም ነኝ የሚሉት እኮ * ሸሃደተይን ይመሠክራሉ* ትለኝ ይሆናል፡፡ ግን እነዚያም ሙሽሪኮች *ሐጅ ያደርጉ ነበር* *በካዕባ ጠዋፍ ያደርጉ ነበር* *በጭንቅ ሰዐት አሏህ ብቻ ይጠሩ ነበር* ሆኖም እነዚህ መልካም ስራቸው ውድቅ የሆነ በስራቸው ላይ ሽርክ ስለቀላቀሉ ነው፡፡

•ዒባዳን ከአሏህ ውጪ ላሉ ግዑዝ ነገሮች ስላቀረቡ ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ *ሸሐደተይን* የመሠከሩ ሰዎች ከሽርክ ሙሉ በሙሉ ካልጠሩ ይህ ቃል መመሥከራቸው ሙስሊም አያደርጋቸውም፡፡ ምናልባት * ጃሒል እኮ ናቸው * ካልክም እነዚያ በኢስላም ተፈጥረው ፥ አያቶቻቸውን በጭፍን ተከትለው ሽርክ የሰሩ ቁረይሾችም *ጃሒል* ነበሩ፡፡ ግን አሏህ *በጅህልናቸው* ነው ሽርክ የሰሩት ብሎ ሙስሊም ናቸው አላለም፡፡

•ማሥረጃ(5) አሏህ እንዲህ ብሏል:



2:89 « ከነሱም ጋር ያለውን (መጽሐፍ) አረጋጋጭ የኾነ መጽሐፍ ከአላህ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ (ከመምጣቱ) በፊት በነዚያ በካዱት ላይ ይረዱበት የነበሩ ሲኾኑ ያወቁት ነገር በመጣላቸው ጊዜ በርሱ ካዱ፡፡ የአላህም ርግማን በከሓዲዎች ላይ ይኹን፡፡»
وَلَمَّا جَاءَهُمْ كِتَابٌ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ مُصَدِّقٌ لِمَا مَعَهُمْ وَكَانُوا مِنْ قَبْلُ يَسْتَفْتِحُونَ عَلَى الَّذِينَ كَفَرُوا فَلَمَّا جَاءَهُمْ مَا عَرَفُوا كَفَرُوا بِهِ فَلَعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الْكَافِرِينَ (89)

፨ ይህ አንቀጽ የሚያስረዳን በአሏህ የሚያጋራ ሰው በየትኛውም ዘመንም ሆነ ፥ ቦታ ሙሽሪክ መሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱም እነዚያ *ይረዱት የነበሩት* ( يَسْتَفْتِحُونَ) አይሁዶች ናቸው፡፡ በማን ከተባለ *በእነዚያ በካዱቱ* ( عَلَى الَّذِينَ كَفَرُوا) እነሱም የ "የስሪብ" ሰዎች ናቸው፡፡ አሏህ ግን ገና ረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ሳይላኩ በፊት የነበሩ ፥ ሑጃ ያልደረሳሠቸው የ "የስሪብ" ሰዎች ካፊር መሆናቸው አረጋገጡ፡፡ እነዛ ሰዎች *አንድ ሰው ኩፍር ላይ መሆኑ ሳይነገረው ፥ ሽርኩ ሳይብራራለት አይከፍርም ይላሉ* ይኸው አሏህ ሽርክ ላይ መሆናቸው ያልተብራራቸው ሰዎች #ካፊር ብሎ ጠራቸው፡፡ *ላ ኢላሃ ኢለሏህ* የሚለው ቃል የሚጠቅመው ከሽርክ ለፀዳ ሰው ነው፡፡

እነዚህ ሰዎች የሚያስጠነቀቅ መልዕክተኛ ሳይመጣላቸው፥ በጅህልናቸው ሽርክ ላይ በመሆናቸው *ሙሽሪክ* ከተባሉ ፥ መልዕክተኛ ተልኮላቸው ፥ ቁርኣን ደርሷቸው ፥ በአሏህ የሚያጋሩ ሰዎች እንዴት *ሙስሊም* ይባላሉ? ፡፡

ኢንሻ አሏህ ሌሎችም ማሥረጃዎች ቀጥለው ይቀርባሉ፡፡

🔘ወቢላሒ አት-ተውፊቅ🔘

✍🏼አቡ ሙስሊም
☑️ @aqida_muwehid

No comments:

Post a Comment

የኢብኑ ተይሚያህ አቋም በተሃኩም ላይ...

  ፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን...