Thursday, May 16, 2019

📌 [  አል-መድኸሉ ኢላ አልጃሚዕ ፊ ኩትቢ አል ኢማን ወርረድ ዓለል ሙርጂአህ ]

--------------  ክፍል _ 1 --------------

بسم الله الحمد لله والصلاة والسلام على رسول الله صلى الله عليه وسلم : أما بعد _

- የአሏህ ፍቃድ ከሆነ በተከታታይ ፅሁፎች በ አሽ-ሼይኽ አቡ ዐብድሏህ ዓዲል አል ሓምዳን (አሏህ ለኸይር ይግጠመው) የተዘጋጀውን ኪታብ መግቢያ ከጠቀሳቸው አንገብጋቢ "በኢማን" ዙርያ የሚያጠነጥኑ ጉዳዮች ወደ አማርኛ ቋንቋ ብመልሰው ብዙ ሰው ትጠቅማለች ብዬ ስላሰብኩ ተርጉሜዋለሁ፡፡ አሏህ ኢኽላስ ይወፍቀን፡፡
............................................    ..............

- አል ኢማን በሸሪዓችን ፦ ሶስት ማዕዘናትን አጠቃሉ የያዘ ነው፡፡ እነዚህ ሶስት ማዕዘናት እስኪሰበሰቡ ድረስ የአንድ ሰው ኢማን አይስተካከልም፡፡ ከቀደምት ደጋግ ሠለፎች ጀምሮ አህሉ ሱናዎች ፥ ከነሱ ኋላ የመጡትም (አህሉ ሱናዎች) ኢማን ሶስት ማዕዘናት እንዳሉት ተስማምተዋል፡፡ (እነዚህን) በቀልብ እውነት ማለት ፥ በምላስ መናገር ፥ በሰውነት መተግበር (ኢማን) በእነዚህ ማዕዘናት የአንድ ባርያ ኢማን አይስተካከልም ሁሉም እስካልተሰባሰቡ ድረስ፡፡ በዚህ ላይ ዑለሞች ንግግራቸው በተለያየ ሁኔታ አስቀምጠዋል፡፡

፩). ከእነሱ መካከል ፦ ኢማን ንግግርና ተግባር ነው፡፡ የሚሉ አሉ ፡፡
፪). ከእነሱ መካከል ፦ ኢማን ንግግር ፥ ተግባር ፥ ኒያ ነው ይላሉ፡፡
፫). ከእነሱ መካከል ፦ ኢማን ንግግር ፥ ተግባር ፥ ኒያ ፥ ሱናን መከተል የሚል አለ፡፡
°
°
°_ እነዚህ ሁሉ ትክክል የሆነ ገለፃዎች ናቸው፡፡ አጠቃሎ የያዘውም መልዕክት "ተግባርን " ከኢማን ያስወጡትን ሙርጂአዎች ላይ ረድ ለማድረግ ነው፡፡ ( ሙርጂአዎች ) የአንድ ባርያ ኢማን ችሎታ ኖሮት ስራን ባይሰራ (ኢማኑ) የተስተካከለ ነው አሉ፡፡

°
🍃 ሼይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ (አሏህ ይዘንለት)

وفي " مجموع الفتاوى " ٧/١٧٠ ... ومن هذا الباب أقوال السلف وأئمة السنة في تفسير الإيمان : تارة ، يقولون ( هو قول وعمل ) وتارة ، يقولون ، ( هو قول ، وعمل ، ونية ) وتارة يقولون ، ( قول ،وعمل، ونية، وإتباع السنة) وتارة يقولون ( قول باللسان ، واعتقاد بالفلب ، وعمل الجوارح) وكل هذا صحيح....
_[ በዚህ ርዕስ የሠለፎች ንግግር ፥ የሱና ሊቃውንት በኢማን  ተፍሲር ላይ ፦ አንዳንዴ "እሱ (ኢማን) ንግግር ና ተግባር ነው፡፡ " ይላሉ፡፡ አንዳንዴ " እሱማ ንግግር ፣ ተግባር ፣ ኒያ ነው ይላሉ፡" አንዳንዴ "በምላስ መናገር ፣ በቀልብ ማመን ፣ በሰውነት መተግበር ነው ይላሉ፡፡ አንዳንዴ "ንግግር ፣ ተግባር ፣ ኒያ ፣ ሱና መከተል ነው ይላሉ፡፡  ] ይህ ሁሉ ትክክል የሆነ ነው፡፡
..................................................
የተፈለገውም ( እዚህ ቦታ ) ከሠለፎች ኢማን ንግግርና ተግባር ሲሉ የቀልብና የምላስ ንግግር ነው፡፡ ተግባር ሲሉ የቀልብና የሰውነት ተግባር ነው፡፡

° " ኢዕቲቃድ (ማመን) የፈለገበት ሰው ደግሞ የንግግሩ ቃል ከሱ መረዳት አይቻልም፡፡ ግልፅ የሆነው ንግግር እንጂ ብሎ ነው፡፡ ወይም ያንን ፈርቶ ነው፡፡ ኢዕቲቃድ በቀልብ የሚለውን ጨመሩ፡፡

- (ኢማን) " ንግግር ፥ ተግባር ፥ ኒያ ነው ያሉት ደግሞ ንግግር (ልብ) እምነትና የምላስ መናገር ያካተተ ነው፡፡ ነገር ግን ተግባር ከሱ "ኒያ" የሚልን ነገር አንረዳም፡፡ ከዚያም ይህ ጨመሩ፡፡

..................................................
" ሱናን መከተል " የሚለውን የጨመሩት ደግሞ ምክንያቱም ይህ ነገር ሁሉ ለአሏህ የተወደደ አይሆንም ሱናን በመከተል እንጂ፡፡ እነዚያ ሁሉንም ንግግርና ተግባር የሚፈልጉ አይደሉም፡፡ ነገር ግን የፈለጉት በሸሪዓ የተደነገገውን ንግግርና ተግባር ነው፡፡

° ነገር ግን የነሱ ሃሳብ በእነዚያ (ኢማን) ንግግር ብቻ ባደረጉት ሙርጂአዎች ላይ ረድ ማድረግ ነው፡፡

" ኢማን ንግግርና ተግባር ነው፡፡ " አሏቸው፡፡ እነዚያ 4 ቦታ የከፋፈሉት የሚፈልጉበት ነገር ፈስረዋል፡፡ ልክ ሰሕል ቢን ዐብድሏህ አትስተሪይ ስለ ኢማን እንደተጠየቀው ነው ፦

سئل سهل بن عبد الله التسترى عن الإيمان ما هو ؟ فقال : قول وعمل ونية وسنة ، لأن الإيمان إذا كان قولا بلا عمل ، فهو كفر.  وإذا كان قولا وعملا بلا نية ، فهو نفاق ، وإذا كان قولا وعملا ونية بلا سنة ، فهو بدعة. اهـ
[ ሰህል ቢን ዐብድሏህ አተስተሪይ ፦ ስለ ኢማን ተጠየቀ እንዲህም አለ ፦ ንግግር ፥ ተግባር ፥ ኒያ ፥ ሱና ነው፡፡ ምክንያቱም ኢማን ያለ ተግባር ንግግር ብቻ ከሆነ ይህ ኩፍር ነው፡፡ ንግግር ና ተግባር ሆኖ ያለ ኒያ ከሆነ ይህ ኒፋቅ ነው፡፡ ንግግር ፥ ተግባር ፥ ኒያ ሆና ሱና መከተል ከሌለው ይህ ቢድዓ ነው፡፡

(የኢብን ተይሚያህ ንግግር አለቀ፡፡ )
................................................ ..
.፨ ኢማም ኢብን አልቀይም (አሏህ ይዘንለት) [ዒደቱ ሷቢሪን ፡ 206]

• ኢማን ንግግር ና ተግባር ነው፡፡ ንግግር የተባለው የቀልብ ተግባር ና የሰውነት ተግባር ነው፡፡ የዚህ ነገር ማብራርያው ፡፡ አሏህ በቀልቡ ያወቀ ሰው ፡፡ በአንደበቱ ያላረጋገጠ ከሆነ #ሙእሚን አይሆንም፡፡ ልክ ስለ ፊርአውን ህዝቦች እንዳለው ፦

وَجَحَدُوا۟ بِهَا وَٱسْتَيْقَنَتْهَآ أَنفُسُهُمْ ظُلْمًۭا وَعُلُوًّۭا ۚ
[ ነፍሶቻቸውም ያረጋገጧት ሲኾኑ ለበደልና ለኩራት በእርሷ ካዱ፡፡ ]

- ስለ ዓድና ሷሊህ ህዝቦች አሏህ እንዳለው ፦
وَعَادًۭا وَثَمُودَا۟ وَقَد تَّبَيَّنَ لَكُم مِّن مَّسَٰكِنِهِمْ ۖ وَزَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيْطَٰنُ أَعْمَٰلَهُمْ فَصَدَّهُمْ عَنِ ٱلسَّبِيلِ وَكَانُوا۟ مُسْتَبْصِرِينَ
[ ዓድንና ሰሙድንም (አጠፋን)፡፡ ከመኖሪያዎቻቸውም (ፍርስራሾች በኩል መጥፋታቸው) ለእናንተ በእውነት ተገለጠላችሁ፡፡ ሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ ሸለመላቸው፡፡ ከመንገድም አገዳቸው፡፡ የማስተዋልም ባለቤቶች ነበሩ፤ (ግን አላስተዋሉም)፡፡ ]

° እነዚያ የቀልብ ንግግር ተገኘላቸው፡፡ እሱም ማረጋገጥና ማወቅ ነው፡፡ በዚህም ሙእሚን አልሆኑም፡፡

° እንደዚሁ በቀልቡ የሌለውን በምላሱ የተናገ በዚህ ነገር ሙእሚን አይሆንም፡፡ እንደውም ከሙናፊቆች ይሆናል፡፡

° እንደዚሁ በቀልቡ ያረጋገጠ ፥ በምላሱ ያፀደቀ በዚህ ነገር ብቻ ሙእሚን አይሆንም ፡፡ ቀልቡ ውዴታና ጥላቻ እስከሚሰራ ድረስ፡፡ ወዳጅነት ፡ ጠላትነት አሏህና መልዕክተኛውን ይወዳል፡፡ የአሏህ ወልዮች ይወዳል ፡ የአሏህ ጠላቶች ይጠላል፡፡ በቀልቡ ለአሏህ ብቻ እጅ ይሰጣል፡፡ ለመልዕክተኛው ትዕዛዝ ሆነ በመከተል ይጎተታል፡፡ ሸሪዓችንም በውስጥም በውጭም በመያዝ ነው፡፡

° ይህ ነገር የተገበረ ጊዜ ኢማን ለመሙላቱ የሚበቃ ነገር አይደለም፡፡ የታዘዘውን ነገር እስከሚሰራ ደረስ ነው፡፡

(የኢብኑል ቀይም ንግግር አለቀ

__________________________
ሼይኽ ዓዲል ፦ ኢማኑን ለመሙላት የተባለው ፦ ያ ግዴታ የሆነውና የአንድ ባርያ ኢማን የማይስተካከልበት የሆነው መሙላት ነው፡፡

°°°°°°°°°°°°° ይህ የመጀመርያ ክፍል ነው፡፡ በቀጣይ ክፍል ኢማን በ3 አርካኖች እንጂ እንደማይረጋጥ የዑለሞች ኢጅማዕ እናያለን፡፡

[ ወቢላሒ አትተውፊቅ ]

© አቡ ሙስሊም ናሙስ



No comments:

Post a Comment

የኢብኑ ተይሚያህ አቋም በተሃኩም ላይ...

  ፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን...