፨ < ኢማን > አህለሱናዎች ዘንድ ??
#الايمان_عند_اهل_السنة.
- ኢማን "ንግግር" "ተግባር" እና "ኒያ " ነው፡፡ ትዕዛዛት በመፈፀም ይጨምራል፡፡ ወንጀል በመስራት ይቀንሳል፡፡
الإيمان قول وعمل ونية ، يزيد بالطاعة وينقص بالمعصية *
1). አሏህ እንዲህ ብሏል ፦
1- قال الله تبارك وتعالى : * ﴿ فَزَادَهُمْ إِيمَانً ﴾ * {آل عمران : 173} .
[ እምነትንም ጨመረላቸው፡፡ ] አለ-ኢምራን፡ 173
2). አሏህ እንዲህ ብሏል ፦
2- وقال الله عز وجل : * ﴿ وَإِذَا تُلِيَتْ عَلَيْهِمْ آيَاتُهُ زَادَتْهُمْ إِيمَانًا ﴾ * {الأنفال : 2} .
[ አንቀፆቹም በነሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ ፥ ኢማንን ጨመረላቸው፡፡ ] አልፈትህ፡ 4
3). አሏህ እንዲህ ብሏል ፦
3- وقال ربنا عز وجل : * ﴿ لِيَزْدَادُوا إِيمَانًا مَعَ إِيمَانِهِمْ ﴾ * { الفتح : 4} .
[ ከኢማናቸው ጋር ኢማንን ሊጨምሩ] አልፈትህ፡ 4
4). አሏህ እንዲህ ብሏል ፦
4- عن أبي هريرة ، أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال :
* [ الْإِيمَانُ بِضْعٌ وَسَبْعُونَ بَابًا، أَفْضَلُهَا لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ ، وَأَدْنَاهَا إِمَاطَةُ الْعَظْمِ عَنِ الطَّرِيقِ ، وَالْحَيَاءُ شُعْبَةٌ مِنَ الْإِيمَانِ ] متفق عليه
አቡ ሑሠይራህ (ረዐ) ባስተላለፈው ሃዲስ የአሏህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ፦
" ኢማን ሰባ ምናምን በሮች አሉት፡፡ ትልቁ ላ ኢላሃ ኢለሏህ ነው፡፡ ትንሹ ከመንገድ እንቅፋት ነገር ማስወገድ ነው፡፡ ሓያእም ከኢማን ቅርንጫፍ ነው፡፡ " ቡኻሪና ሙስሊም
5). ኢማም ሓርብ ቢን ኢስማኢል አል-ኸንዘሊይ [ አስሱና በተባለ ኪታቡ ፡ 142]
ኢብን መስዑድ (ረዐ) በዱዓው እንዲህ ብሏል ፦ "አሏህ ሆይ! ኢማን ፥ እረርግጠኝነት ፥ ና እውቀትን (ግንዛቤን) ጨምርልን፡፡ "
5- قال الإمام حرب بن اسماعيل الحنظلي الكَرماني في كتابه السنة (142) :
حدثنا أحمد ، قال : ثنا وكيع ، عن شَريك ، عن هلال بن حُميد ، عن عبد الله بن عُكيم ، قال : سمعت ابن مسعود رضي الله عنه يقول في دعائه :
* [ اللَّهُمَّ زِدْنَا إِيمَانًا وَيَقِينًا وَفِقْهًا ] * .
ይህ ከዐብድሏህ ቢን መስዑድ የተገኘ ማረጋገጫ ነው፡፡ እሱ ከታላላቅ የሶሃባ ፉቀሃዎችና ዑለሞቻቸው ነበር፡፡ ኢማን ይጨምራል፡፡
وهذا تصريح من عبدالله بن مسعود - وهو من أجل فقهاء الصحابة وعلمائهم - بأن الإيمان يزداد ، وإلا لما كان لدعائه معنى .
6). ኢብን አቢ ሼይባህ "ኢማን፡ 10 "ላይ የዘገበው ኺሻም ከአባቱ ይዞ እንዳወራው ፦ እንዲህ ብሏል ፦
" በጭራሽ የአንድ ባርያ አማና አትጓደልም ፥ ኢማን የጎደለ ቢሆን እንጂ፡፡
6- قال ابن أبي شيبة في الإيمان (10) :
حدثنا وكيع ، عن سفيان ، قال : قال هشام ، عن أبيه ، قال :
* [ مَا نَقَصَتْ أَمَانَةُ عَبْدٍ قَطُّ إِلَّا نَقَصَ إِيمَانُهُ ] * .
የኺሻም ወላጅ ፦ ታላቁ ታብዕይ ዑርዋህ ቢን ዙበይር ከ7ቱ የመዲና ፉቀሃዎች ነው፡፡ አባቱም አንዱ በጀነት ከተበሰሩት መካከል ነው፡፡ ወንድሙ ታላቅ ሶሃባ ነው፡፡ እናቱ ደግሞ አስማእ ቢንት አቡበክር
ووالد هشام هو : التابعي الجليل عروة بن الزبير بن العوام أحد فقهاء المدينة السبعة ، والده أحد العشرة المبشرين بالحنة ، وأخوه صحابي جليل ، وأمه أسماء بنت أبي بكر ، وخالته عائشة أم المؤمنين فقد حاز الفضل والعلم من كل جهة .
وهذا تصريح منه رحمه الله بأن الإيمان ينقص .
7). ዐብድሏህ (ኪታብ አስሱናህ፡ 611 ) በተባለ ኪታቡ እንዲህ ብሏል
7- قال عبدالله في كتاب السنة (611) :
حدثني أبي ، نا عفان بن مسلم ، نا حماد بن سلمة ، عن أبي جعفر الخطمي ، عن أبيه ، عن جده عمير بن حبيب بن خماشة أنه قال :
ሒማሻህ እንዲህ ብሏል ፦ ኢማን ይጨምራል ፥ ይቀንሳል፡፡ ለሱ እንዲህ ተባለ መጨመሩና መቀነሱ ምንድነው ? አሏህ ያስታወስን ጊዜና የፈራነው ጊዜ ያኔ መጨመሩ ነው ፥ ከተዘናጋንና ከረሳን ፥ ካጠፋነው ይህ ነው ጉድለቱ፡፡
* [ الْإِيمَانُ يَزِيدُ وَيَنْقُصُ ، فَقِيلَ لَهُ : وَمَا زِيَادَتُهُ وَنُقْصَانُهُ ؟
قَالَ : إِذَا ذَكَرْنَا اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ وَخَشَيْنَاهُ فَذَلِكَ زِيَادَتُهُ وَإِذَا غَفَلْنَا وَنَسِينَا وَضَيَّعْنَا فَذَلِكَ نُقْصَانُهُ ] * .
وعمير بن حبيب من الصحابة رضي الله عنهم .
- ዐብድሏህ ቢን ኢማም አህመድ እንዲህ ብሏል ፦
[ መዕመር ፥ ኢብን ጁረይጅ ፥ አስሰውሪይ ፥ ማሊክ ፥ ኢብን ኡየይናህ "ኢማን ንግግርና ተግባር ነው ይጨምራል ይቀንሳል" ሲሉ ነበር፡፡
قال الإمام عبدالله بن الإمام أحمد في كتابه " السنة " :
حدثني أبو عبدالرحمن سلمة بن شبيب - قبل سنة ثلاثين ومائتين - ، ثنا عبدالرزاق ، قال :
* [ كان معمر ، وابن جريج ، والثوري ، ومالك ، وابن عيينة يقولون : الْإِيمَانُ قَوْلٌ وَعَمَلٌ يَزِيدُ وَيَنْقُصُ * .
قَالَ عَبْدُ الرَّزَّاقِ :
وَأَنَا أَقُولُ ذَلِكَ :
* الْإِيمَانُ قَوْلٌ وَعَمَلٌ وَالْإِيمَانُ يَزِيدُ وَيَنْقُصُ فَإِنْ خَالَفْتُهُمْ فَقَدْ ضَلَلْتُ إِذًا وَمَا أَنَا مِنَ الْمُهْتَدِينَ ] * .
፨ ዐብድርረዛቅ እንዲህ ብሏል ፦ እኔም ይህ እላለሁ ፡፡ ኢማን ንግግር ና ተግባር ነው፡፡ ይጨምራል፡፡ ይቀንሳል፡፡ ይህን ከተፃረርኳቸው ያኔ እኔ ጠመምኩ ከተመሩት አይደለሁም ማለት ነው፡፡
قال الإمام الشافعي :
* [ وكان الإجماع من الصحابة والتابعين من بعدهم ممن أدركناهم يقولون : إن الإيمان قول وعمل ونية ، لا يجزئ واحد من الثلاثة إلا بالآخر ...] * .
نقله عنه شيخ الاسلام في كتاب الإيمان ص (197) .
፨ ኢማም አሽሻፊዒይ ፦ የሶሃቦች ፥ የታብዕዮች ና ከነሱም በኋላ የመጡ የጋራ ስምምነታቸው ፥ ኢማን ንግግር ፥ ተግባር ኒያ ነው፡፡ ከሶስቱ አንዱ ያለ ሌላኛው አያብቃቃም፡፡
@ Abu Muslim namus
Thursday, May 16, 2019
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
የኢብኑ ተይሚያህ አቋም በተሃኩም ላይ...
፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን...
-
🔖 በአሏህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩህና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ በዚህ ሁፍ በአሏህ እርዳታ በመታገዝ ወደ ጧጉት መፋረድ ምን እንደሆነ እና ወደ ጧጉትም መፋረድ ያለው ሁክም እንመለከታለን፡፡ በምን አይነት...
-
✔ በአሏህ ስም እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ الحمد لله وصلاة وسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه ومن والاه ..... أما بعد ° በዚህ አጠር ያለ ትምህርት ...
-
📌 [ አል-መድኸሉ ኢላ አልጃሚዕ ፊ ኩትቢ አል ኢማን ወርረድ ዓለል ሙርጂአህ ] -------------- ክፍል _ 2 -------------- بسم الله الحمد لله والصلاة والسلام على رسول ...
No comments:
Post a Comment