✿ ዑዝር ቢል-ጀህልና ማደናገርያዎች መግለጥ❀ (ክፍል-3)
[ በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ በጣም ሩህሩህ በሆነው]
፨ ምሉዕ የሆነ ምስጋና ለአለማቱ ጋታ ለአሏህ ይገባው፡፡ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም ረድኤት ዘወትር በነብያች ሰለሏሁ ዐለይሒ ወሰለም ላይ ይውረድ፡፡
፨ቅርብ ጊዜ በአንድ የፌስቡክ ባልደረባችን የተፃፈ {በኢስላም ዑዝር ቢልጀህል ስለመኖሩ ግራ ለተጋባችሁ!} የሚል ተከታታይ ፅሁፍ አንብበን ነበር፡፡ የዚህ ፅሁፍ ጸሐፊ ባቀረበው ት/ቱ ቁርኣንና ሐዲስ እንዲሁም የሙስሊሞች የጋራ ስምምነት የሚጥስና የሚቃረን ሐሳብ አቅርቧል ብዬ አምናለሁ፡፡
ሆኖም ብዙዎች ይህ ስህተት ተመልከተው ሊያርሙት ስላልሞከሩ ወይም ስላልደረሳቸው ፥ በርካታ ሰዎች ይህን ፅሁፍ እንደማሥረጃ ከቦታ ወደቦታ ሲያስተላልፉ በማየቴ የማወቀውን ያህል የዑለሞች አስተምህሮት በማብራራት ሐቁን ለማስቀመጥ ሙከራ አድርጊያለሁ፡፡ አሏህ ሱብሐነሁ ወተዐላ ለሐቁ እንዲገጥመኝ እለምነዋለሁ፡፡
[ ፀሐፊው እንዲህ ይላል☞ ኢንሻ አላህ በኢስላም ዑዝር ቢልጀህል እዳለ ቁራኣናዊ ሀዲሳዊ እንድሁም የኡለሞችን ንግግር በተከታታይ ፅሁፍ ለማቅረብ እሞክራለሁ! ] የዚህ ፀሐፊ ስህተት ከዚህ ይጀምራል፡፡ ዑዝር ቢልጀህል ከሰዎች ሁኔታ ፥ ከአካባቢ ሁኔታ ፥ ከዘመን ሁኔታ ፥ የመሣሠሉት ጋር ቁርኝት ያለው ነጥብ በመሆኑ በልቁ "ዑዝር ቢልጀህል እንዳለ.." ብሎ መቅረብ አይገባውም ነበር፡፡ ምክንያቱም በቁርኣንም በሐዲስም በልቁ በጀህል ዐቃቤ ምክንያት(ዑዝር ቢልጀህል) አለ ተብሎ አልተነገረንም፡፡
[ ፀሐፊው እንዲህ ይላል ☞ ዑዝር ቢልጀህል እንደሌሎች ኢጅቲሃድን እንደሚያስተናግዱ ርእሶች ነው። እንጅ #ከዐቂዳ ርእስ አይደለም!! ]
ይህ ንግግር የተጠቀሰበት ምክንያት ዑዝር ቢልጀህል መስጠት ፥ አለመስጠት ኺላፍ ያለበት ርዕስ ስለሆነ ከፊል ፥ ከፊሉን ማውገዝ የለበትም የሚል ድፍን ቃዒዳ ለማርቀቅ የተሞከረበት ነው፡፡
• እንጂ ባለማወቅ ሽርክ ላይ የወደቀ ሰው ሙሽሪክ ካፊር በመሆኑ ላይ ምንም ኺላፍ የለም፡፡ ቁርኣን ፥ ሐዲስ ፥ ኢጅማዕ ይህን ይመሠክራሉ፡፡ እሱ ግን ኺላፍ አለ ብሎ ለማስቀመጥ የሞከረው የተወሰኑ የሱን አካሔድ የሚደግፉለት ዐሊሞች ስም ጠቀሰና በሽርክ ዑዝር ቢልጀህል መስጠት ኺላፍ ያለበት ነጥብ አስመስሎ አቅርቦታል፡፡ ይህ ፍፁም ስህተት ነው፡፡ ምንም ኺላፍ የሌለበት አሏህና መልዕክተኛው ያረጋገጡት ሐቅ ነው፡፡ በርግጥ ይህን የሚፃረሩ የቢድዐ አራማጆች ይጠፋሉ ማለት አይደለም፡፡
[ ፀሐፊው እንዲህ አለ ☞ ለዚህም ነው የሱና አሊሞች በዚህ ዙሪያ ብዙዎቹ ዑዝር ቢልጀህል አለ ሲሉ!
#የተወሰኑት የለም በማለት የተለያዩት። ]
ይህ ንግግሩ በሱና ዑለሞች ላይ የቀጠፈው አስቀያሚ ድፍረቱን ያሳየበት አገላለፅ ነው፡፡
•ለራሱ የስህተት መንሐጅ አሳምሮ ለማቅረብና ለመሸወድ አብዛኛው ዑለሞች በሽርክ ዑዝር ቢልጀህል አለ ይላሉ ፥ የለም የሚሉት የተወሰኑ ናቸው ማለቱ ፥ ምናልባት ዐሊም ሲባል የሚያውቀው እነዚያ የጠቀሳቸው ጥቂት ሰዎች ይሆናሉ ብዬ እጠረጥራለሁ፡፡ እንጂ በዚህ ርዕስ ዙሪያ የተፃፉ ኪታቦች ያነበበ ሰው እንዲህ አይነት የድፍረት ንግግር ሊናገር አይችልም ነበር፡፡ ሁሉም በቦታው እናየዋለን፡፡
•ማስረጃ ብሎ የጠቀሳቸው ነጥቦች ላይ ከመናገሬ በፊት ፥ አንድ በዚህ ነጥብ ላይ የሚናገር የሆነ ሰው ለይቶ ሊያውቃቸው የሚገቡ ነጥቦች አስቀምጣለሁ፡፡ እነዚህ ነጥቦች ያልተረዳ ሰው የተወናበደ እይታ ይዞ ሰዎችን ግራ ያጋባልና !! እነዚህ መግቢያዎች በትኩረት ይመልከቱ ፡፡
• እስልምና የሚያርሱና ወደክህደት የሚወስዱ ነጥቦች በሁለት ተከፍለው ሊታዩ ይችላሉ ፦
1ኛው). አንድ ጃሒል የሆነው ቢሰራው ሑጃ ሳይቆምበት የማይከፍርበት ነጥብ ነው፡፡ እነዚህ ነጥቦች ዑለማዎች መሳኢል ኸፊያ (ድብቅ የሆኑ ነጥቦች) ብለው ይጠሩታል፡፡ በዚህ የጠሩበት ምክንያት እነዚሀ ነጥቦች ማስረጃዎቻቸው አብዛኛው ሰው ዘንድ ግልፅ ያልሆኑ ስለሆኑ ሑጃ ሳይቆም በፊት በኩፍር ብይን አይሰጥም፡፡ አንዳንድ ሲፋቶች ይመሥል፥ አሏህ ሐራም ያደረገውን ሐላል ማድረግ ፥ ሃላል ያደረገውን ሐራም ማድረግ የመሳሰሉ ነጥቦች ሊካተቱ ይችላሉ፡፡
2ኛው). አንድ ጃሒል ቢሰራው ፥ ባለማወቁ ዑዝር የማይሰጥበት ነው፡፡ እሱም "ሽርክ" ነው፡፡ በአሏህ ማጋራት ዑዝር ቢልጀህል የሌለበት ከባድ ጥፋት ነው፡፡ (ኢንሻ አሏህ በማሥረጃዎች እናየዋለን፡፡)
• አል-ዑዝር በሶስት ነጥቦች ላይ ይነገራል፡፡
1). በቂያማ ቀን መቀጣት በተመለከተ ያለ ዑዝር ነው፡፡ ይህ የዒልም ፥ የመጠየቅ ዕድል ያልተመቻቸለት ሰው በጅህልናው የቂያማ ቀን አይቀጣም፡፡ ምክንያቱም አሏህ መልዕክተኛ እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም ብሏል፡፡ ማስረጃውም አሏህ እንዲህ ብሏል
وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبْعَثَ رَسُولًا، [الإسراء: 15]
" መልዕክተኛ እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም፡፡ " አልኢስራእ፡15
° ፨ በዚህ አንቀፅ አሏህ የነገረን ሰዎቹ መልዕክተኛ መጥቶ ተጠንቀቁ ብሎ ሑጃ ሳያደርሳቸው አይቀጣቸውም ማለት እንጂ ሰዎች የሚሠሩት ሽርክ እስልምናቸው የማያፈርስ ነገር ሆኖ አይደለም፡፡ ሰዎች ተውሒዳቸው ፈርሷል፡፡ እስልምናቸው ተንዷል፡፡ ነገር ግን ይቀጡ ዘንድ መልዕክተኛ መላኩ መሥፈርት ተደርጓል፡፡
2). በዱንያ ላይ የመጋደልን ዑዝር የተመለከተ ነው፡፡ የሪዳ ሃድ በተመለከተ የሚሰጠው ዑዝር ነው፡፡ ሰዎች ሽርክ ሰራ ፥ ታድያ ቀጥታ ይገደላልን? ሑጃ አይቆምበትም? ማለት ነው፡፡ በዚህ ነጥብም ላይ ሽርክ ላይ የወደቀ ሰው አንጋደለውም ፥ የሪዳ ሃድም አይቆምበትም ሑጃ ከደረሰው በኋላ እንጂ፡፡ ነገርግን ካፊር ተብሎ ይጠራል፡፡ ሙስሊም አይደለም፡፡
3). ሽርክ ላይ የወደቀ ሰው ማክፈር እሱን ካፊር ሙሽሪክ ብሎ መጥራት በተመለከተ የሚነሳ ዑዝር ሲሆን በዚህ ላይ ሽርክ የሰራ ሰው ሑጃ ቢደርሰውም ፥ ባይደርሰውም ሙሽሪክ ተብሎ ይጠራል፡፡ ሙስሊም ነው አይባል፡፡ እንዲሁም የተክፊርን አህካሞች በሱ ላይ ይፈፀማሉ ፡፡ ነካህ አለማድረግ ፥ በሱ ላይ አለመሥገድ ፥ አለመውረስ የመሳሰሉት...
• ለዚህም ዑለማዎች ተክፊርን በሁለት እይታዎች ይገልፁታል፡፡ 1ኛው). ተክፊር ሙዐዘብ ዐለይሒ ሲሆን ..2ኛው). ተክፊር ገይረል ሙዐዘብ አለይሒ በማለት ይከፍሉታል፡፡ ብዙ ጊዜ ዐዝር ቢልጀህል አለ ብለው ማሥረጃ የሚጠቅሱ ሰዎች የቁርኣን ፥ የሃዲስ የዑለሞች ንግግር ባልፈለጉበት ቦታ በማዋል ሰዎችን ያወናብዳሉ፡፡ ይህ ፀሐፊም ይህንኑ ስህተት ደጋግሞታል፡፡ እስቲ ተክፊር ሙዐዘብ እና ገይረል ሙዐዘብ አለይሒ የሚለው ዑለሞች ተጠቅመውታል? አው፡፡ ለምሳል ኢብን ተይሚያህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ብሏል ፦
[ والكفر المعذب عليه لا يكون إلا بعد بلوغ الرسالة ] الفتاوى ٢/٧٨
[ አልኩፍር ሙዐዘብ (የሚያስቀጣ የሆነው ክህደት) ሪሳላ ከደረሰ በኋላ እንጂ የሚሆን አይደለም፡፡ ] አልፈታዋ፡2/78
• በዚህ ንግግሩ ከላይ እንደጠቀስኩት በአኼራም ሆነ በዱንያ ቅጣትን በተመለከተ ሑጃ ከደረሰው በኋላ እንጂ የሚሆን ነገር አይደለም፡፡ ኢብን ተይሚያም ያለው ይህንኑ ነው፡፡ ግን ሰዎች በዑለማዎች ሲቀጥፉ የአኼራን ቅጣት በተመለከተ የተናገሩት ንግግሩ ያለቦታው በማስገባት ፥ ይኸው ሼይኽ እገሌ ሽርክ ዑዝር ይሰጣሉ ተብሎ ይወራል፡፡ ግን ከዑለሞች የማስረጃ አጠቃቀም እንኳን ብናጤነው ሰውዬ በማጋራቱ ሙሽሪክ የሚል ስም ይሰጠዋል ወይስ አይሰጠውም ሳይሆን ፥ ባለማወቅ በሰራው ሽርክ ይቀጣል ወይስ አይቀጣም በሚል ዙሪያ እንደሆነ እንረዳለን፡፡
• ኢብን ተይሚያህ ፦ አንድ ሰው ሽርክ ከሰራ ሑጃ ባይደርሰውም ሙሽሪክ የሚል ስም እንደሚሰጠው ተናግሯል፡፡ እንዲህ ብሏል ፦
إسم الشرك يثبت قبل الرسالة لأنه يشرك بربه ويعدل به ]الفتاوى ٢٠/٣٨
[ የሽርክን ስያሜ ሪሳላ ከመምጣቱም በፊት ይፀድቃል፡፡ ምክንያቱም በጌታው የሚያጋራና የሚዘነበል ስለሆነ] ብሏል፡፡ ሰዎች በሚሠሩት ሽርክ ሑጃ ቢደርሳቸውም ፥ ቢይደርሳቸውም ሙሽሪክ የሚል የሽርክ ስያሜ ይሰጣቸዋል፡፡ ግን ይቀጣሉ ወይ የሚለው ከሆኑ ሑጃ ሳይደርሳቸው አይቀጡም ነው፡፡ አሁን ማስረጃ ብሎ ያቀረባቸው እንመልከት....!!
[ መረጃ ① ብሎ ያቀረበው ]
﴿ وَمَنْ يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِنْ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَى وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّى وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ وَسَاءَتْ مَصِيرًا ﴾.
سورة النساء (115)
#ቅኑ መንገድ ለእርሱ ከተገለፀለት በኋላ! መልእክተኛውን የሚፃረርና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የሆነን የሚከተል ሰው በዞረበት ላይ እንተወዋለን። ጀሀነምንም እናገባዋለን።
#መመለሻይቱም ከፋች።" [ኒሳእ: 115)]
፨ ይህ አንቀፅ ሽርክ የሰራ ሰው ሙሽሪክ አይባልም የሚል ምንም አይነት ማሥረጃ የለውም፡፡ ሐቅ ከገለፀለት በኋላ መልዕክተኛው የተፃረረ ሰው ጀሀነም ይገባል ነው ጭብጡ፡፡ ሽርክ የሰራ ሰው ሙሽሪክ አይደለም ፥ ሙስለሊም ነው የሚል ትርጉም የለውም፡፡ ስለዑዝር ይጠቅሳል ቢባል እንኳን ከላይ እንዳሳለፍነው ስለ አኼራ ቅጣት እንጂ ሰውዬው በዱንያ በሰራው ሽርክ ተውሒዱ ፈርሷል ወይስ አልፈረሰም የሚል ነገር አይሰጠንም፡፡
የኢብኑ ከሲር ንግግር ብሎ የጠቀሰው ጭራሽ ከርዕሱ የማይገናኝ ሆድና ጀርባ ስለሆነ ትቼዋለሁ፡፡
[ መረጃ ② ብሎ የጠቀሰው]
#وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبْعَثَ رَسُولًا، [الإسراء: 15]
#መልእክተኛም እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም!!
[ኢስራእ: 15]
• ከላይ እንዳሳለፍነው ይህ አንቀፅ ሽርክ ውስጥ የወደቀ ሰው ይቀጣል አይቀጣም የሚል ነጥብ ነው እንጂ በዱንያ ሙሽሪክ የሚል ስም እንሚሰጠው አያስተባብልም፡፡ ምክንያቱም አሏህ ሑጃ ያልደረሰው ሰው "ሙሽሪክ" እንደሆነ በቁርኣን አረጋግጧል፡፡ አሏህ እንዲህ አለ...
وإن أحد من المشركين إستجارك فأجره حتى يسمع كلام الله
[ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ አስጠጋው፡፡ ] በዚህ ቁርኣን አንቀፅ አሏህ ገና ሑጃ/ቁርኣን ያልሰማውን ሰው ከመሥማቱ በፊት ሙሽሪክ ብሎ ጠርቶታል፡፡ ስለዚህ ስምና አህካም መለየት ግድ ይለናል፡፡
[ ፀሐፊው እንዲህ ብሏል ☞ይህ የቁራኣን አንቀፅ መልእክተኛው ይዘውት የመጡት መልእክት የደረሰው ሰው እንጂ እንደማይቀጣ ፍንትው አድርጎ ያሳየናል።] እኛም የምንለው ቅጣት ለመቀጣት መልእክተኛ መልኩ አሏህ መሥፈርት አድርጓል፡፡ ነገርግን በዱንያ ያ ሰው ሙስሊም ነው አልተባለም፡፡
• በዚህ አንቀፅ ላይ የጠቀሳቸው ተፍሲሮች ሁሉ ትክክል ነው ግን የፀሐፊው ችግር በዚህ መስዓላ ላይ ዑለሞች { አል-አስማእ ወል-አህካም} ብለው ያብራሩት ነጥብ የተረዳው አይመሥልም፡፡ አልአስማእ የምንለው በሸሪዐ የተሰጡ ስያሜዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ፦ ሙእሚን ፥ ካፊር ፥ ሙሽሪክ ፥ ሙናፊቅ ፥ ፋሲቅ ፥ ሙብተዲዕ የመሳሰሉት "አልስማእ ሸርዒያ" ናቸው፡፡ እነዚህ ስያሜዎች ተክተለው የሚመጡ "አል-አህካም" ደግሞ አሉ፡፡ ለሙእሚን መውደድ ፥ መርዳት ፥ ማገዝ ፥ ጀነት መግባት ፥ ምህረት ማግነት ሲሆን ለካፊር ደግሞ መጥላት ፥ በራዕ ማድረግ ፥ አለመወዳጀት ፥ አለመርዳት ፥ በአኼራ እሳት መግባት የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ ቀላቅሎ መጓዝ አይገባም፡፡ ኢብን ተይሚያ ረሂሐሁሏህ {አልአስማእና አልአህካም} በተመለከተ እንዲህ ብሏል ፦
[ وقد فرق الله بين ما قبل الرسالة وما بعدها في أسماء وأحكام، وجمع بينهما في أسماء وأحكام ] الفتاوى ٢٠/٣٧
" በርግጥም አሏህ ከሪሳላ በፊት ባለውና ከሪሳላ በኋላ ባለው በስምና በአህካም ላይ ለያይቷል፡፡ በነሱ መካከልም በስም ና አህካም ላይም ሰብስቧል፡፡ " አልፈታዋ፡20/37
أعلم أن مسألة التكفير والتفسيق هي من مسائل الأسماء والأحكام التي يتعلق بها الوعد والوعيد في الدار الآخرة وتتعلق بها الموالاة والمعاداة والقتل والعصمة وغير ذلك في الدنيا. /الفتاوى :٤٦٨
[ እወቅ! የተክፊር ና የተፍሲቅ ነጥብ ከስምና አህካም ጋር የሚመደብ ነው፡፡ በሱም በአኼራ ላይ ቀጠሮና ዛቻ የተያያዘበት ነጥብ ነው፡፡ በዚህ ላይ ነው ወዳጅነት ፥ ጠላትነት ፥ መገደል ፥ ደም ሐራም መሆን ሌሎችም ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ] አልፈታዋ
• እና ሁላችንም ይህ ነጥብ በደንብ መረዳት አለብን፡፡ እንዴት አድርገው የዑለሞች ንግግር ያለቦታ እንደሚያስገቡት መረዳት አለብን፡፡ እሱ ክፍል ሁለት ብሎ ያቀረባቸው ፅሁፎች በቀጣይ በክፍል አራት (4) እንመለከታለን፡፡
አሏህ ሐቅ ይግጠመን፡፡ በትክክለኛው የአንቢያዎች ዲን ላይም ይግደለን፡፡ ወሰለሏሁ ወሰለም ዐላ ነቢዪና ሙሐመድ፡፡
© ✍ አቡ ሙስሊም /ናሙስ..... ሸዕባን/1440 ዓ.ሒ
Tuesday, April 23, 2019
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
የኢብኑ ተይሚያህ አቋም በተሃኩም ላይ...
፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን...
-
🔖 በአሏህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩህና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ በዚህ ሁፍ በአሏህ እርዳታ በመታገዝ ወደ ጧጉት መፋረድ ምን እንደሆነ እና ወደ ጧጉትም መፋረድ ያለው ሁክም እንመለከታለን፡፡ በምን አይነት...
-
✔ በአሏህ ስም እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ الحمد لله وصلاة وسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه ومن والاه ..... أما بعد ° በዚህ አጠር ያለ ትምህርት ...
-
📌 [ አል-መድኸሉ ኢላ አልጃሚዕ ፊ ኩትቢ አል ኢማን ወርረድ ዓለል ሙርጂአህ ] -------------- ክፍል _ 2 -------------- بسم الله الحمد لله والصلاة والسلام على رسول ...
No comments:
Post a Comment