Monday, April 8, 2019

¤በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩሕሩህ እና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ፡፡

《ኸዋሪጅ አይደለሁም ስል በምክንያት ነው》

በመጀመርያ ምሉዕ ምስጋና ሁሉ ለአሏህ ነው፡፡ ከኃይማኖት ሁሉ መርጦ ወደኢስላም ስለመራን በድጋሚ እናመሠግነዋለን፡፡ በታላቁ ነብይ ሙሐመድ ቢን ዐብዲላህ ላይ ዘወትር የአሏህ ሰላምና ሶለት ይውረድ፡፡

¤ በኢስላም ብቅ ካሉ ትክክለኛው መንገድ ትተው በስሜትና በጥመት ወደጥፋት ከሔዱ ቡድኖች መካከል ኸዋሪጆች አንዱ ናቸው፡፡ ዘመን ዘመን እየተካ በሔደ ቁጥር ሐቅ በሰዎች ላይ በተለያየ መልኩ በባጢል እየተቀየጠ ብዙዎች ለግራ መጋባትና ዲናቸውን በትክክል ላለመረዳት ዳርጓቸዋል፡፡

¤በዚህ ፅሁፍ ላመላክት የወደድኩት ባለማወቅ ወይም ከስሜት በመነዳት የሐቅ ሰዎችን በ"ኸዋሪጅነት" የምትፈርጁ ሰዎች ቆም ብላቹ እንድታስቡና እኛም ከዚህ በባጢል ከለጠፋቹብን መጥፎ ስም የጠራን መሆናችን ታውቁ ዘንድ ነው፡፡

¤በመጀመርያ "ኸዋሪጆች" እነማን ናቸው? አጭር ገለጻ:- የዚህ ጠማማ ቡድን መጀመርያ መቼ ነበር? የዚህን መልስ በተመለከተ አልኢማም አቡበክር ሙሐመድ ቢን አልሑሰይን አል-ኣጁሪይ (360 ዓ.ሒ) ረሒመሁሏህ "አሽ-ሸሪዓህ" በተባለ ኪታባቸው ኸዋሪጆችን በተመለከተ ሲጠቅሱ እንዲህ ብለዋል ፦
فأول قرن طلع منهم على عهد رسول الله صلى الله عليه وسلم : هو رجل طعن على رسول الله صلى الله عليه وسلم ، وهو يقسم الغنائم بالجعرانة. فقال "اعدل يا محمد ، فما أراك تعدل" فقال صلى الله عليه وسلم : 《 ويلك ،فمن يعدل إذا لم أكن أعدل》
የመጀመርያ ብቅ ያሉበት ዘመን ፥ በረሱል   ዘመን ነበር፡፡

¤ እሱም አንድ ሰው ነበር ነብዩ ﷺ በጀዕራን ምርኮ እያከፋፈሉ በነበረበት ወቅት ላይ አነወራቸው (ክብራቸው ነካ)፡፡  እንዲህም አለ ፦ " አንተ ሙሐመድ ሆይ! ፍትሓዊ ሁን፡፡ ፍትሐዊ ነህ ብዬ አላይም(አላምንም)፡፡ " አላቸው፡፡ እሳቸውም እንዲህ አሉት "ወዮልህ! እኔ ፍትሐዊ ካልሆንኩ ማንነው ፍትሐዊ የሚሆነው?" አሉ፡፡

¤ ይህ አነሳሳቸው ነው፡፡ በዚህም ሐዲስ ላይ ለዚህ ክብራቸው ለነካ ሰው ባልደረቦች እንዳሉትና አንደኛቹህ ሶላቱን አሳንሶ ያያል ፥ ከዚህ ሰው አሰጋገድ ፥ ፆሙንም ከዚህ ሰው ጾም ፥ ከዲንም ተስፈንጥረው ይወጣሉ ብለዋል፡፡ ኢማም አልኣጁሪይ (360 ዓ.ሒ) እንዳሉትም እነዚህ ኸዋሪጆች ከዚያ በኋላ በተለያዩ ሐገራት ብቅ ብለዋል ይላሉ፡፡ ራሳቸውን በመልካም እንደሚያዙና ከመጥፎ እንደሚከለክሉ መሥለው ብቅ አሉ፡፡ ከዚያም መዲና መጡ፡፡ ዑስማን ቢን ዐፋን ረዲየሏሁ ዐንሁ ገደሉ፡፡ በመዲና የነበሩ የረሱል ﷺ ባልደረቦች ዑስማን ቢን ዐፋን እንዳይገደል ብዙ ጥረዋል፡፡ ግን አልቻሉም፡፡ ከዚያም በዓሊ ቢን አቡ ጧሊብ ረዲየሏሁ ዐንሁ ላይ አምፀው ወጡ፡፡ በፈረደው ፍርድ ወደው አልተቀበሉም፡፡

¤ ከዚያም "ፍርድ ሁሉ ለአሏህ ነው በማለት ፊትናቸውን አጧጧፉ፡፡ ይህ ንግግራቸው ዓሊ ቢን አቡ ጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) " ሐቅ የሆንች ንግግር ፥ ለባጢል የተፈለገባት" ብለዋታል፡፡ እነዚህ ኸዋሪጆች ዓሊ ቢን አቡ ጧሊብ ላይ"ፍርድ ሁሉ ለአሏህ ነው" ብለው ሲያምፁ ዓሊ ቢን አቡ ጧሊብ ዛሬ እንደምናያቸው መሪዎች በሠው ሰራሽ ህግ ፈርዶ አልነበረም ፥ ወይም በዲሞቅራጢ ፈርዶ አልነበረም፡፡ እርሱ (ረዲየሏሁ ዐንሁ ) በሸሪዐ ነው የፈረደው ግን ኸዋሪጆች ስህተት በሆነ ግንዛቤ ወድቀው ነው፡፡

¤ ለመሆኑ ኸዋሪጅ አይደለሁም የምለው ?

1ኛ). ኸዋሪጆች ፦ " በሙስሊም መሪዎች ላይ አምፆ መውጣት ግዴታ ነው ይላሉ፡፡" ይህ ዐቂዳ የኸዋሪጆች ዐቂዳ ነው፡፡ እኔም ይህን እቃወማለሁ፡፡ ምክንያቱም የአሏህ መልዕክተኛﷺ እንዲህ ብለዋል ፦ ዑባዳህ ቢን ሷሚት እንዲህ ይላል ፦

دعانا رسول الله ﷺ فبايعناه فكان فيما أخذ علينا أن بايعنا على السمع والطاعة في منشطنا ومكرهنا وعسرنا ويسرنا وأثرة علينا وأن لا ننازع الأمر أهله,  قال 《الا أن تروا كفرا بواحا عندكم من الله فيه برهان》

የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ ጠሩን፡፡ ቃልኪዳንም ተጋባናቸው፡፡ ከኛ ከያዙት ቃል መካከል በመሥማትና በመታዘዝ ላይ ነው፡፡ ደስ ባለን ጊዜም ፥ በጠላንም ጊዜ፡፡ ነገሮች በከበዱንም ጊዜ ይሁን ፥ ገር በሆነ ጊዜ፥ ችግር ቢደርስብንም የጉዳዩ ባለቤት ኃላፊነቱን እንዳንነጥቅ (ቃል ገብተናል፡፡) "የአሏህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ 《እናንተ ዘንድ ከአሏህ የሆነ  ማሥረጃ ያለው ግልፅ ኩፍር እስክታዩ ድረስ (ስሙ ታዘዙ፡፡》

📚ሙስሊም ፡ 1709 ዘግበውታል፡፡

¤ በዚህ መሠረት አህሉሱና ዘንድ አንድ ሙስሊም በሸሪዐ የሚያስተዳድር መሪ ግልፅ የሆነ ክህደት ካልታየበት "እሱን መጋደል አይገባም፡፡" ኸዋሪጆችም የተወቀሱት አንድ መሪ ከኢስላም የማያስወጣ ወንጀል በሠራ ጊዜ ያከፍሩታል፡፡ ሠይፍ ይዘውም ይጋደሉታል፡፡ ይህ ስህተት ነው ፡፡ ነገር ግን አንድ መሪ በሸሪዓ ማስተዳደር ትቶ በጣጉት የሚያስተዳር ከሆነ ፥ በአሏህ የሚያጋራ ከሆነ ፥ ኩፋሮችን ተወዳጅቶ ሙስሊሞች የሚጋደል ከሆነ ፥ ሌሎችም ከኢስላም የሚያስወጡ ክህደቶች የሚተገብር ከሆነ እሱን መጋደልና የሸሪዐ አስተዳደር ማምጣት የኸዋሪጆች ዐቂዳ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ መጋደል የሌለብን ኩፍር ያልሰሩ እንደሆነ ነው በማለት ለጉዳዩ ገደብ አስቀምጠዋል፡፡

¤  ኸዋሪጆች ደግሞ አምፀው የሚወጡትና የሚጋደሉት ኩፍር ያልሆኑ ወንጀሎች የሠራ ሰው ነው፡፡ ኩፍር የሰራ መሪ የሚጋደልማ "ኸዋሪጅ" በፍጹም አይባልም፡፡

¤  እዚህ ጋር መነሳት ያለበት ነጥብ ከአሏህ ውጪ ባለ ሠውሠራሽ ህግ መፍረድ ኩፍር አይደለም የሚሉ ሰዎች ሁሌም መደገፊያ የሚያደርጉት የሱረቱል ማኢዳ አንቀፅን በመጥቀስ ነው፡፡ ነገር ግን በቁርኣን ይህን ሑክም የሚያብራሩ ሌሎችም አንቀጾች አሉ በተለይ ሱረቱል ኒሳእ ፡60 ይጠቀሳል፡፡ አሏህ በዚህ አንቀፅ ከአሏህ ህግ ውጪ ያሉ ህግጋት "ጣጉት" መሆናቸው ይነግረናል፡፡

《الم ترى الى الذين يزعمون أنهم ءامنوا بمآ أنزل إليك ومآ أنزل من قبلك يريدون أن يتحاكموا إلى الطاغوت وقد أمروا أن يكفروا به》

《ወደ እነዚያ እነርሱ በአንተ ላይ በተወረደውና ከአንተ በፊትም በተወረደው አምነናል ወደሚሉት፤ አላየህምን በእርሱ እንዲክዱ በእርግጥ የታዘዙ ሲኾኑ ወደ ጣዖት መፋረድን ይፈልጋሉ፡፡ 》

¤ ይህ አንቀፅ በተመለከተ ሼይኽ ዐብድርራህማን ቢን ናሲር አስ-ሰዕዲይ እንዲህ ተርጉመውታል ፦
"يريدون أن يتحاكموا إلى الطاغوت" وهو كل من حكم بغير شرع الله فهو طاغوت.
(የሚለው) " እሱም ከአሏህ ሸሪዓ ውጪ ባለ የፈረደ ነው፡፡ እሱም ጧጉት ይባላል ይላሉ፡፡ እንደገና በእነዚህ ጧጉቶች የተፋረደን በተመለከተ እንዲህ ይላሉ ...
فكيف يجتمع هذا والإيمان ؟ فإن الإيمان يقتضي الإنقياد لشرع الله وتحكيمه في كل أمر من الأمور ، فمن زعم أنه مؤمن واختار حكم الطاغوت على حكم الله فهو كاذب في ذلك ، وهذا من إضلال الشيطان  إياهم.
《እንዴት (ወደ ጣጉት መፋረድና) ኢማን አንድ ላይ ይሰበሰባሉ? ኢማን ደግሞ ለአሏህ ሸሪዐ መታዘዝ(መጎተትን) አመላካች ነገርና በሁሉም ጉዳያችን መፋረጃ ማድረግ ነው፡፡  በአሏህ ህግ ላይ የጧጉትን ህግ መርጦ እኔ ሙእሚን ነኝ ብሎ የሞገተ እሱ በዚህ ውሸታም ነው፡፡ ይህ ከሸይጧን የሆነ ማጥመም ነው》ይላሉ፡፡

፨ ስለዚህ ወደጧጉት መፋረድና ኢማን ተፃራሪ ነገሮች ናቸው፡፡ እነዚህ በጧጉት የሚፈርዱና የተለያዩ ኩፍር ተግባራት የሚሠሩ መሪዎች መጋደል የኸዋሪጆች ዐቂዳ አይደለም፡፡ ነው የሚል ሰው ማስረጃ ማምጣት አለበት፡፡

2ኛ). ኸዋሪጆች ፦ ከባኢር(ትልልቅ ወንጀል) በተባሉ ወንጀሎች ያከፍራሉ፡፡ እኛም በፍፁም በትልልቅ ወንጀሎች አናከፍርም፡፡ እነዚህ ትልልቅ የተባሉሰ ወንጀሎች ሽርክና ከፍር ደረጃ የማያደርሱ  የሆኑ ናቸው፡፡ መስረቅ ፥ አልኮል መጠጣት ፥ ሐሜት ፥ ስዕል መሣል ፥ የመሣሰሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን በትልቁ ሽርክና በትልቁ ኩፍር ማክፈር የኸዋሪጆች ዐቂዳ አይደለም፡፡ ምክንያቱም አሏህና መልዕክተኛው ﷺ አክፍረዋልና፡፡ ዛሬ ግን በተቃራኒው ቀብር አምላኪዎች ስታከፍር ሙስሊም አክፍረሐል ተብሎ በዚህ ወቅት "ኸዋሪጅ" የሚል ስም ይሰጡሐል ይህ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ አንድ ቀን ኸዋሪጆች በአሏህ የሚያጋራ ሰው በማክፈራቸው ተወቅሰው አይታወቅም፡፡

3ኛው). ኸዋሪጆች በአንድ ሰው ላይ ምንዳና ቅጣት አይሰበሰብም ይላሉ፡፡ ይህ የአህሉ ሱና መንሐጅ አይደለም፡፡ በዚህም አናምንም፡፡ ኸዋሪጆች ግን አንድ ሰው ላይ ቅጣትና ጥሩ ምንዳ አይሰበሰብም ይላሉ፡፡ ይህ ስሕተት ነው፡፡

4ኛው). ኸዋዋሪጆች ዘንድ ኢማን አይበላለጥም ይላሉ፡፡ አህሉ ሱና ወል ጀመዐ ዘንድ ኢማን ይበላለጣል፡፡ ኢማን  በቀልብ የሚቋጠር ፥ በምላስ የሚነገር ፥ በአካል የሚተገበር ፥ መልካም ስራ በመሥራት ይጨምራል፡፡ አሏህን በማመፅ ይቀንሳል፡፡ ይህን የአህሉ ሱና መዝሐብ፡፡  ኸዋሪጆች ግን ይህ ጥሰው ኢማን ወጥ ነገር አድርገዋል፡፡ ስለዚህ ኸዋሪጅ አይደለንም፡፡
الإيمان قول باللسان واعتقاد بالقلب وعمل بالجوارح يزيد بطاعة وينقص بالمعصية.
5ኛው). ኸዋሪጆች ፦ ከፊል ሶሓቦችን ያከፍራሉ፡፡ ዓሊይ ፥ ጦልሓ ፥ ዓኢሻ ፥ ኢብን ዓባስ (አሏህ ስራቸው ይውደድላቸው)  ያከፍራሉ፡፡ እኛ አህሉሱና ወልጀመዐህ ከዚህ ባጢል የጠራን ነን፡፡ ዐቂዳችን ልክ ሼይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ እንደገለጸው ነው፡፡
ويقبلون ما جاء به الكتاب والسنة والإجماع من فضائلهم ومراتبهم ويفضلون من أنفق من قبل الفتح -وهو صلح الحديبية -  وقاتل، على من أنفق من بعد، وقاتل ويفضلون المهاجرون على الأنصار... (كتابه الواسطية)
《አህሉሱናዎች ፦ በቁርኣን ፥ በሐዲስ ፥ በኢጅማዕ የመጣውን ትልቅነታቸው ፥ ደረጃቸው እንቀበላለ፡፡ ከፈትሕ በፊት ከገንዘቡ የሰጠና የተጋደለ ያስበልጣሉ፡፡ ከአንሷሮች ሙሐጂሮችን ያስበልጣሉ፡፡ 》በዚህ መሠረት ሶሓቦች ላይ ባለን አቋም ከኸዋሪጆች የተለየን ነን፡፡ ሶሐቦች ሁሉንም እንወዳለን፡፡ በመካከላቸው የተፈጠረ ነገርንም አንስተን እከሌ እንዲህ ነው ፥ እከሌ እንዲህ ነው አንልም፡፡

6ኛው). ኸዋሪጆች ፦ ትልልቆ ወንጀል ለሰሩ ሙስሊሞች ሸፈዐ የለም ይላሉ፡፡ አህሉሱና ወልጀመዐ ግን ከነብያችን አስተምህሮት በመያዝ ለትልልቅ ወንጀል ባለቤቶች ሸፈዐ አለ ይላሉ፡፡ ማሥረጃቸውም የአሏህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል ፦
عن النبي ﷺ قال 《شفاعتي لأهل الكبائر من أمتي》أخرجه الترمذي
《ሸፈዐዬ ከዑመቴ ትልልቅ ወንጀል ለሰሩት ነው》ብለዋል፡፡ ስለዚህ ከኸዋሪጆች አይደለንም፡፡ እነሱ  ከባኢር የሰራ ሰው ስለሚያከፍሩ ሸፈዐ የለም ይላሉ፡፡

7ኛው). ኸዋሪጆች ፦ የአሏህ ስሞችና ባሕርያት በተመለከተ የጀሕሚዮች አቋም ያላቸው አሉ፡፡ እኛ አህሉ ሱናዎች ደግሞ ከዚህ የቢድዐ መንገድ የጠራን ነን፡፡

ومن الإيمان بالله : الإيمان بما وصف به نفسه في كتابه وبما وصف به رسوله محمد ﷺ من غير تحريف ولا تعطيل ومن غير تكييف ولا تمثيل....

" በአሏህ ከማመን መካከል :- አሏህ ራሱን በኪታቡ በገለፀበት ና መልዕክተኛ ﷺ አሏህ የገለፁበት ማመን ነው፡፡ ያለ ትርጉም ማዛባት ፥ ውድቅ ሳናደርግ ፥ ሁኔታው ሳንገልፅ ፥ ሳናመሣስል ማመን ነው፡፡" ይህ ነው የአህሉሱና ዐቂዳ ፡፡ ኸዋሪጆች ግን ይኽ ተቃርነዋል፡፡

8ኛው). ኸዋሪጆች:- ከሁለት ቅን መሪ ኹለፋዎች ራሳቸውን ያጠራሉ፡፡ ከዑስማንና ከዓሊ (ረዲየሏሁ አንሁም)
 التبروء من الخليفتين الراشدين عثمان وعلي رضي الله عنهما.
°እኛ የአህሉ ሱና ወልጀመዐ ዐቂዳ ተከታዮች ግን እንደኸዋሪጆች ዑስማንና ዓሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) አንጠላም ፡፡ እንወዳቸዋለን፡፡ በጀነት የተመሠከረላቸው እንደሆኑ እናምናለን፡፡ እናልቃቸዋለን፡፡ ኸዋሪጆች ግን እነዚህን ታላላቅ ኸሊፋዎች ይጠላሉ፡፡ እኛ በፍፁም አንጠላቸውም፡፡

9ኛው). ኸዋሪጆች ፦ ዚና የሰራ ሠው በድንጋይ ተቀጥቅጦ የሚገደልበትን የሸሪዐ ሐድ ውድቅ ያደርጋሉ፡፡
إسقاط حد الرجم عن الزاني،

°እኛ ግን ይህ በፍፁም አንልም፡፡ በረጅም እናምናለን፡፡ እንሰራበታለን፡፡

10ኛው). ኸዋሪጆች ሐይድ ያየች ሴት ሶላቷ ቀዷ ማውጣት ግዴታ ነው ይላሉ፡፡ በዚህም አጠቃላይ የሙስሊሞች ኢጅማዕ ጥሰዋል፡፡ እኛ በዚህ አናምን፡፡ ከዚህ ቆሻሻ ንግግርም የጠራን ነን፡፡
القول بوجوب قضاء الصلاة على الحائض، فخالفوا النص والإجماع .
°ጾም ነው ሸሪዐችን ቀዷ አውጡ ያለው፡፡

11ኛው). ወዘተ የተበላሸ ዐቂዳቸው ይጠቀሳል፡፡ እኛ አህሉ ሱናዎች ከዚህ ሁሉ የጠራን ነን፡፡

¤  በመጨረሻም በዚህ በሌለንበት የጥመት መንገድ በዙልም የሚፈርጀን ሁሉ  አሏህ ፊት እንጠይቀዋለን፡፡ በህይወት ኖረንም ፥ ሞተንም ከኸዋሪጅ ዐቂዳ ወደአሏህ እንጠራለን፡፡ አሏህ ሆይ! መሥክር እኛ ከኸዋሪጆች መንገድ አይደለንም፡፡

[ ወሰለሏሁ ዐለይሒ ወሰለም ወዐላ ዓሊሒ ወሰለም፡፡ ]

No comments:

Post a Comment

የኢብኑ ተይሚያህ አቋም በተሃኩም ላይ...

  ፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን...