Saturday, December 15, 2018

፨ [ ሺዓ _ ምን ማለት ነው ? ]

..........................................................

- በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ምስጋና ሁሉ ኃይማኖቱን ሙሉ አድርጎ ፥ ፀጋውን በኛ ላይ ለዋለልን አሏህ ይገባው፡፡ ከእርሱ በቀር በሐቅ የሚመለክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፡፡ ለአለማት እዝነት ፥ ለጨለማው ብርሐን ተደርገው በተላኩት የአሏህ ነብይ "ሙሐመድ" ላይ የዘወትር የአሏህ በረከትና ረድኤት ይስፈን፡፡ በመቀጠል ፦

..........  ........... ........ ......  .....

በዚህ ፅሁፍና ተከታትለው በአሏህ ፍቃድ የሚቀርቡ ሌሎች አምዶች "ሺዓ" ተብለው የሚጠሩትንና ራሳቸውን ወደ ኢስላም የሚያስጠጉ ቡድኖች በተመለከት መጠነኛ ዳሰሳ ለማቅረብ ለመሞከር ነው፡፡ የዚህ አደገኛና ጠማማ ቡድን ምንነት በጥልቀት ለመፈተሽና ለማጥናት ጊዜንና አቅምን የሚጠይቅ እንደሆነ ግልፅ የሆነ ነገር ነው፡፡ ሆኖም በመሠረታዊነት ሊናውቃቸው የሚገቡና ሊታለፉ የማይገባቸው አንዳንድ ነጥቦች እንተዋወሳለን፡፡

..........  ...........   ..........   ..........   .........

-መገጠምና እርዳታ ከአሏህ ብቻ እንከጅላለን፡፡ ለአንባቢያን ግልፅ እንዲሆን ዋቢ አድርጌ ከምጠቀምባቸው መፅሐፍት ቅርፅን ሙሉ በሙሉ ወስጄ ፥ የመልዕክት ይዘት ለማሳጠርና ዋና ዋና አንኳር ነጥቦች ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡
........  ........  ........ ........    ..........  .....

- ስለ ቡድኑ(ሺዓ) ምንነት ከመግለፄ በፊት ፊርቃው የሚጠራበት ስያሜ የያዘው መልዕክት ማወቁ የሚበጅ ነው፡፡ አንዳንዴ በቁርአን ፥ በሐዲስ "ሺዓ" የሚለው ቃል ሊመጣ የሚችልበት አጋጣሚ ስላለ ለማወናበድ ውዥንብር ለመፍጠር በር ሊከፍት ይችላል፡፡ ስለዚህ ይህ ነጥብ መጀመርያ መቅረቡ ጥሩ ይሆናል፡፡ በዋናነት ለማጣቀሻነት ስለሺዓዎች ምንነት የሚያትተውን የዶ/ር ናስር አልቀፋሪይ መፅሐፍ በዋናነት ተጠቅሚያለሁ፡፡ መልካም ንባብ !!!

===========================

1). " ሺዓ በቋንቋ ያለው ትርጉም "
........ ........... .........  .........  .........
ኢብን ደሪይድ (321 ዓ.ሒ የሞተ ) እንዲህ ብሏል ፦
- فلان من شيعة فلان. أي ممن يرى رأيه.
(ፉላን ሚን "ሺዓቲ" ፉላን) ይባላል ፥ ይህ ማለት " የሱን አመለካከት የሚከተል ወይም በእገሌ ቡድን አመለካከት የሚሄድ ብሎ ለመግለፅ ነው፡፡

[ ጀምኸረቱ አልሉግጋ ፡ 3/63]

" እገል ከእገሌ ሺዓ(ጎራ) ነው ፡፡ " ያልነው፡፡ ስለዚህ በቀላሉ ይህ ቃል አንድ ጎራን ፣ቡድንን ለመግለፅ እንደሚፈለግበት ነው፡፡

° አል-አዝኸሪይ (አሏህ ይዘንለት) በ370 ዓ.ሒ የሞተ እንዲህ ብሏል ፦

- وشيعة أنصار الرجل وأتباعه ، وكل قوم اجتمعوا على أمرهم شيعة.
" ሺዓ የሚባለው ነገር ፦ የአንድ ሰው ረዳቶቹና ተከታዮቹ ማለት ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰዎች በአንድ ያሰባሰባቸው ነገር "ሺዓ" እንለዋለን፡፡

[ ተህዚብ አልሉግጋ ፡ 3/61]

_ እንዲሁም ሺዓ የሚለው ቃል "ረዳት" እንዲሁም "በአመለካከት አንድ የሆነ ቡድን ፥ እንዲሁም በተመሳሳይ አመለካከት መሰባሰብ " የሚሉ ፍቺዎች ሊኖሩት እንደሚችል የቋንቋ ምሁራን ያስቀምጣሉ፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች ይህን ቃል በቀጥታ " ታላቁ ሶሃቢይ ዓሊይ(ረ.ዐ) ና ቤተሰቦቹን ወዳጅ አድርገው የያዙ " በሚልም አንድምታ የተቀመጠበት ሁኔታ አለ፡፡ ነገሩ በአተኩሮት ለተመለከተው ሰው ግን በተለምዶ "ሺዓ" ተብለው የሚጠሩ ድንበር አላፊ ቡድኖች ለዓሊይም(ረ.ዓ) ሆነ ለቤተሰባቸው ረዳትና ተከታይ ሆነው አናገኛቸውም ፡፡ እንደውም ዓሊይ(ረ.ዓ) ና ቤተሰቦቹን የነበሩበት ቀጥተኛ ኃይማኖት ሲጥሱን በቢድዓና በሽርክ ድንበር ሲያልፉ ነው የምናገኛቸው፡፡
............  ..............  ..............  ........ .......

ሼይኹል-ኢስላም ኢብን ተይሚያህ (ረሒመሁሏህ)  እንደሚናገረው ፦ ከዓሊይ (ረ.ዓ) የተዘገቡ በስምነት (8) አይነት ገላፃ የተናገራቸው ንግግሮች ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ በኩፋ ሚንበር ላይ ሆኖ " የዚህ ዑሜ ብልጫ ያለው ሰው ከነብዩ በኋላ አቡበክርና ዑመር (ረ.ዐ) ናቸው፡፡ አል-ቡኻሪይ የዘገበው፡፡
[ ሚንሐጅ አስሱናህ ፡ 4/137] እንዲሁም ከአንዳንዶች በተዘገበው ዓሊይ(ረ.ዓ) የማይከተል በእውነቱ (ሐቂቂይ) "ሺዒይ" እንደማይባሉ ጠቁመዋል፡፡ ምክንያቱም ከላይ እንዳሳለፍነው ፥ ሺዓ ሲባል በቋንቋውም የሚፈለግበት "ተከታይ" እንዲሁም "ረዳት"  " በተመሳሳይ አቋም ላይ የሚገኝ" ለማለት ስለሆነ እነዚያ ደግሞ ለዚህ ነገር የገጠሙ ወይም የተገቡ አይደሉም፡፡

-------------  -------------  --------------  ------ ---  ------
" ሺዓ" የሚለው ቃል በቁርአን ውስጥ ያለው ትርጉም
.................   ............  .........       ...........
ሺዓ ፦ የሚለው ቃል በቁርአን ውስጥ አስራ ሁለት ቦታ ላይ ተጠቅሶ ይገኛል፡፡ ኢብን አል-ጀውዚይ ፦ የተፍሲር ሊቃውንቶች " ሺዓ" የሚለው ቃል በአራት ቅርፅ እንዳስቀምጡት ይገልፃል፡፡ ( ይህ ማወቃቻን እነዚያ የጥመት ቡድኖች ስለኛ ነው አንቀፁ የሚያወራው ብለው እንዳያምታቱ ያግዘናል)፡፡

1). የመጀመርያው " ቡድን" በሚል ተጠቅሷል፡፡
إِنَّ ٱلَّذِينَ فَرَّقُوا۟ دِينَهُمْ وَكَانُوا۟ شِيَعًۭا

[ እነዚያ ሃይማኖታቸውን የለያዩ አሕዛብም የኾኑ በምንም ከእነሱ
 አይደለህም፡፡ ]

[ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ فِى شِيَعِ ٱلْأَوَّلِينَ]
( ከአንተም በፊት በነበሩት በመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ውስጥ (መልክተኞችን) በእርግጥ ልከናል፡፡ )

☞ በነዚህ አንቀፆች ሺዓ የሚለው ቃል "ቡድን" ወይም የሰዎች ስብስብ በሚያመለክት ሁኔታ ተቀምጧል፡፡

2). በሁለተኛ ፦ " ቤተሰብና የራስ ወገን (ዘርን) ለመግለፅ መጥቷል፡፡

وَدَخَلَ ٱلْمَدِينَةَ عَلَىٰ حِينِ غَفْلَةٍۢ مِّنْ أَهْلِهَا فَوَجَدَ فِيهَا رَجُلَيْنِ يَقْتَتِلَانِ هَٰذَا مِن شِيعَتِهِۦ وَهَٰذَا مِنْ عَدُوِّهِۦ ۖ فَٱسْتَغَٰثَهُ ٱلَّذِى مِن شِيعَتِهِۦ عَلَى ٱلَّذِى مِنْ عَدُوِّهِۦ
[ ከተማይቱንም ሰዎቿ በዝንጋቴ ጊዜ ላይ ሆነው ሳሉ ገባ፡፡ በእርሷም ውስጥ የሚጋደሉን ሁለት ሰዎችን አገኘ፡፡ ይህ ከወገኑ ነው፤ ይህም ከጠላቱ ነው፡፡ ]

☞ በዚህ አንቀፅ ሺዓ የሚለው ቃል "ወገን" ወይም "የራስ ዘር" የሚል አገባብ ነው የተፈለገበት፡፡ የበኒ እስራኤል ሰዎችን ነው የተፈለገበት፡፡

3). የመንገድ (የመዝሃብ) ባለቤቶችን ለመጥቀስ ቀርቧል፡፡

ثُمَّ لَنَنزِعَنَّ مِن كُلِّ شِيعَةٍ أَيُّهُمْ أَشَدُّ عَلَى ٱلرَّحْمَٰنِ عِتِيًّۭا
[ ከዚያም ከየጭፍሮቹ ሁሉ ከእነርሱ ያንን (እርሱ) በአልረሕማን ላይ በድፍረት በጣም ብርቱ የኾነውን እናወጣለን፡፡]

4). አራተኛ ፦ የተለያዩ ስሜት ባለቤቶችን ለመጠቆም ተጠቅሷል፡፡ አሏህ እንዲህ ብሏል ፦

قُلْ هُوَ ٱلْقَادِرُ عَلَىٰٓ أَن يَبْعَثَ عَلَيْكُمْ عَذ

َابًۭا مِّن فَوْقِكُمْ أَوْ مِن تَحْتِ أَرْجُلِكُمْ أَوْ يَلْبِسَكُمْ شِيَعًۭا وَيُذِيقَ بَعْضَكُم بَأْسَ بَعْضٍ ۗ ٱنظُرْ كَيْفَ نُصَرِّفُ ٱلْـَٔايَٰتِ لَعَلَّهُمْ يَفْقَهُونَ
«እርሱ (አላህ) ከበላያችሁ ወይም ከእግሮቻችሁ በታች ቅጣትን በእናንተ ላይ ሊልክ ወይም የተለያዩ ሕዝቦች ስትኾኑ ሊያደባልቃችሁና ከፊላችሁን የከፊሉን ጭካኔ ሊያቀምስ ቻይ ነው» በላቸው

.............   ..............    ............  .......   ......

- ኢብንል ቀይም (አሏህ ይዘንለት)
ስለዚህ ነጥብ ሲያመለክት እንዲህ ይላል ፦

" ምናልባት በዚህ ሁኔታ እንጂ በቁርአን አልመጣም ይሆናል፡፡ (ኢብን አልቀይም) ሲናገር ለዚህ ነገር ምክንያት ሲያስቀምጥ ይህ ነገር ያውቃል ፦ ሺዓ በሚለው ቃል አሽሺያዕ ስላለበት ነው፡፡ አል ኢሻዓህ የሚለው "መተሳሰር" "መሰባሰብ" የሚለውን ቃል የሚቃረን ነው፡፡ ለዚህም "ሺዓ" የሚለው ቃል በጠመመ ቡድን ላይ እንጂ አይነገርም፡፡ ስለተለያዩና ስለተበታተኑ፡፡

[ በዳኢዕ አልፈዋኢድ ፡ 1/155]

- ይህ "ሺዓ" የሚለው ቃል በአሏህ ኪታብ ውስጥያለው ትርጉም ይህ የምናውቀው ፊርቃ የሚመለከት እንዳልሆነ በነዚህ መረጃዎች ግልፅ ይሀሆናል፡፡

......   .......  .............  .............. ... .......  ......
ነገርግን እነዚህ የጥመት በድኖች የተለያየ የትርጉም ማንሻፈፍ በማድረግና አላዋቂዎች በማደናገር በቁርአን የተጠቀሰው "ሺዓ" የሚለው ቃል የነሱ መጤ አመለካከት ለመግለፅ የመጣ እንደሆነ አድርገው ማቅረብ ዳክረዋል፡፡ ቁርአን ከተገቢው የፍቺና የመልዕክት ይዘት አንጋደው ሠለፎች ሶሓቦች ዘንድ የማይታወቅን ተዕዊል በማስቀመጥ እያጣመሙ ይገልፁታል፡፡በነዚህ ሰዎች ኪታብ ውስጥ እንደተቀመጠው እንዲህ ብለዋ፦
۞ وَإِنَّ مِن شِيعَتِهِۦ لَإِبْرَٰهِيمَ
[ ኢብራሂምም በእርግጥ ከተከታዮቹ ነው፡፡ ]

- ሺዓዎችም በተፍሲራቸው እንዲህ ተርጉመውታል፡፡ '' ኢብራሂም ከዓሊይ 'ሺዓ' ነው፡፡ ማለት ነው አሉ፡፡ " ይህ ደግሞ የቁርአንን አገባብ የሚቃረን ነው፡፡ የኢስላም መሰረት የሚቃረን ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ድንበር አላፊ ሺዓዎች እነዚያ አኢማዎቻቸውን ከነብያት የሚያስበልጡ የሆኑ ፥ የነሱ የተበላሸ ግንዛቤ ነው፡፡ ከአህለ ሱናህ በትክክል የተፈሰረው በዚህ አንቀፅ ከሠለፎችም የተገኘው ኢብራሒም (ዓ.ሰ) ከኑህ (ዓ.ሰ) ሺዓ ጋር ነበር ነው፡፡ በመንሐጁም በአካሔዱም ለማለት ነው፡፡ [ ተፍሲር አጥጦበሪይ ]
ከአንቀፁ ጋር የቃላት አገባብም ሆነ ትርጉም የሚገጥመው ይህ ነው፡፡ ምክንያቱም ቀድሞም በአንቀፁ ስለ ኑህ ዓ.ሰ ተጠቅሷልና፡፡

===========================

ይህ ርዕስ በዚህ ጀምረን ቀጣይ በሚቀርቡ ክፍሎች የበለጠ ስለጉዳዩ ግንዛቤ እንዲኖረን ለማድረግ በአሏህ ፍቃድ ጥረት ይደረጋል፡፡ አሏህ ለኸይር ሁሉ ይግጠመን፡፡

............. መልዕክቱን ለሌሎች በማስተላለፍ የራሳችን ድርሻ እንወጣ፡፡ ...................

© አቡ ሙስሊም ናሙስ

No comments:

Post a Comment

የኢብኑ ተይሚያህ አቋም በተሃኩም ላይ...

  ፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን...