□《የሺዓ ሐይማኖት 》□
■ ክፍል_2
ለአሏህ ሱብሐነሁ ወተዓላ ምስጋና ይገባው፡፡ በነብያችን ላይ የአሏህ ሶላትና ሰላም ይውረድ፡፡ በመቀጠል...
በመጀመርያው ክፍል ፦ ሺዓ የሚለው ቃል የሚሰጠው ትርጉምና ምንነቱ በተወሰነ መልኩ አይተን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ከእምነቶቻቸው መካከል ጥቂቱን ለማስታወስ ያህል እናያለን፡፡
ሺዓ የቁርአን ሑጃነት (ማስረጃነት) በተመለከተ ምን ይላሉ ?? ይህ ክፍል በሶስት አይነት ከፍለን እናየዋለን፡፡
የመጀመርያው (1) ቁርአን በቀይም (ከአኢማዎቻቸው አንዱ) ካልሆነ በቀር ሑጃ (ማስረጃ) አይሆንም ማለታቸው፡፡
ሁለተኛ (2) የቁርአንን ዕውቀት መረዳት በአኢማዎቻቸው መገደባቸው፡፡
ሶስተኛው(3) የኢማማቸው ንግግር የቀርአን ጥቅል መልዕክትን #ይገድባል ፥ ልቅ የሆነውን ደግሞ በራሱ ገደብ ያስቀምጥለታል ማለታቸውን እናያለን፡፡
1▪የመጀመርያው ነጥብ ፦ ቁርሐን ሐጃ አይደለም ማለታቸው ነው፡፡ ይህ ነጥብ በበርካታ ሺዓዎች በሚመረኮዙባቸው መፅሐፎቻቸው የሚገልፁት እውነት እንደሆነ የተረጋገጠ ነው፡፡
አንድም ሰው " ቁርአን ሑጃ አይደለም" የሚል ቡድን ይኖራል ብሎ ጭራሽ አስቦ ላያውቅ ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የአሏህ መልዕክተኛ ሰለለሏሁ አለይሒ ወሰለም እውነተኝነታቸው የሚገልፅ አንቀፅ የፈለገ አሏህ እንዲህ ብሏል ፦
أَوَلَمْ يَكْفِهِمْ أَنَّآ أَنزَلْنَا عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ ۚ
[ እኛ መጽሐፉን በእነሱ ላይ የሚነበብ ኾኖ ባንተ ላይ ማውረዳችን አይበቃቸውምን? ] አንከቡት ፡51
ታላቁ መፅሐፍ ቁርአን መስካሪ ነው፡፡ ጠቋሚ መረጃ ነው፡፡ እንዲሁም ሑጃ አስረጅ ነው፡፡ ነገር ግን የሺዓ ሐይማኖት አስተማሪዎች ይህ #ሲቀቱል ኢስላም ብለው የሚጠሩት ( አል-ኩለይኒይ ) ኡሱል አልካፊ በተባለ ኪታቡ እነሱ ዘንድ ልክ አህለ ሱና ዘንድ አል-ቡኻሪይ እንደምንለው ነው የሚቆጥሩት፡፡ በዚህ ኪታቡ እንዲህ ዘግቧል ...
أن القرآن لا يكون حجة إلا بقيم ...وأن عليا كان قيم القرآن وكانت طاعته مفترضة ، وكان الحجة على الناس بعد الرسول. (أصول الكافي ١/١٨٨)
[ ቁርአን አስረጅ የሆነ ሑጃ አይሆንም በቀይም ቢሆን እንጂ፡፡ ዓሊይ ደግሞ የቁርአን ቀይም ነበር፡፡ እሱን መታዘዝም ግዴታ ነበር፡፡ በረሱል (ሰለሏሁ አለይሒ ወሰለም) በኋላ በሰዎች ላይ ሑጃ ነበር፡፡ ]
እንደዚህ አይነት ንግግሮቻቸው እነሱ ዘንድ በሚመረኮዙባቸው ኪታቦቻቸው ሰፍሮ ይገኛል፡፡ እንደ ሪጃል አልከሽፊይ ፥ ዒለል አልመሽራኢዕ ፥ አልመሐሲን ፥ ወሳኢል አሽሺዓ የመሳሰሉት ውስጥ ይገኛል፡፡
ይህ ንግግራቸው ይህ ዓቂዳቸው ምን ማለት ፈለሸገው ነው? ማለት የፈለጉት የቁርአን ጥቅሶችና መረጃዎች አሸንደ አስረጂነት ሊቀርቡ አይችሉም ወደ አኢማዎች ንግግር በመመለስ እንጂ ማለታቸው ነው??
ይህ ማለት ሑጃ ያለው በኢማም ንግግር እንጂ በአርራህማን ንግግር አይደለም ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት የኢማም ንግግር አሏህ በቁርአኑ ካብራራው የበለጠ ገርና ምርጥ አገላለፅ ነው እንደማለት ነው፡፡ ከዚህ ግልፅ ሆና የምናየው እነዚህ ሰዎች ሑጃ ያለው በኢማም ንግግር እንጂ በአሏህ አይደለም ብለው እንደሚያምኑ ነው፡፡ ለዚህ ነው ዝምተኛው ቁርአን ብለው የሰየሙት ፡ ኢማማቸውን ደግሞ ተናጋሪው ቁርአን፡፡ እንዲህም ይላሉ ፦
ዓሊይ እንዲህ ብሏል ፦
" ይህ የአሏህ መፅሐፍ ዝምተኛው ነው፡፡ እኔ ደግሞ ተናጋሪው የአሏህ መፅሐፍ ነው፡፡ "
📚 አልሐር አልዓሚሊይ ፡230
እንዲህ ብሏል ይላሉ ፦
" ያ ቁርአን አናግሩት ለናንተ አይናገርም፡፡ ስለሱ (እኔ) እነግራቹሐለሁ፡፡ "
📚ኡሱል አልካፊ ፡ 1/61
በሌላ ዘገባቸው ....
" ዓሊይ የአሏህ ኪታብ ተፍሲር ነው፡፡ " ይላሉ፡፡
📚 አልቢሐር ፡ 37/209
በተደጋጋሚም አኢማዎቻቸው ቁርአን ራሱ ናቸው ሲሉም ይሞግታሉ፡፡ ለዚህ እንዲህ የሚለው የአሏህ ቃል
واتبعوا النور الذي أنزل معه ....
-በዚህ አንቀፅ " ኑር " የተባለው ዓሊይና አኢማዎች ናቸው ብለው ይናገራሉ፡፡ ስለዚህ ከዚህ ተነስተን ምን ሊባል ነው አኢማዎች ከሰማይ ነው የተወረዱት ሊባል ነው፡፡
📚አልካፊ 1/194
- እንደገናም ቁርአን ለአንድ ሰው እሱም ለዓሊይ እንጂ ለማንም አልተፈሰረም ብለው ይሞግታሉ፡፡
[ ኡሱል አለሸካፊ ፡ 1/250 ]
ዓሊይ ራሱ ተፍሲር ቁርአን ነው ተብሎ ለምን ቀይሙል ቁርአን እንደሚሆን አናውቅም፡፡ ዓሊይ እሱ ራሱ ቁርአን ከሆነ ወይም በቁርአን ላይ ቀይም ከሆነ ለምንድነው ለሱ የሚፈሰርለት ወይም እንዴት እሱ ራሱ ተፍሲር ነው ተብሎ እንደገና ለሱ ይፈሰርለታል ? ይህ እርስ በራሱ የተማታ ንግግር ነው፡፡ ይህ አንዲ ኢስላምን ለማበላሸት ዚንዲቅ የቀጣጠፈው ኹራፋት እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ እንዴት እንዲህ ይባላል አሏህ ቁርአን ያወረደው የሰው ልጆች ሁሉ ሊመሩበት ነው፡፡ አሏህ እንዲህ ብሏል ፦
إِنَّ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانَ يَهْدِى لِلَّتِى هِىَ أَقْوَمُ ً
[ ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው መንገድ ይመራል፡፡ ] ኢስራእ 9
ታላቁ ቅኑ መንገድ የተመራው ኸሊፋው ዓሊይ (ረዲየሏሁ አንሁ) እንዲህ ብሏል ፦
" የአሏህ ኪታብ በውስጡ ከናንተ በፊት (ስለነበሩ ጉዳዮች) ዜና አለው፡፡ ከናንተ በሗላም ስለሚመጣው ዜና አለበት፡፡ በመካከላቹ ያለ ፍርድ ነው፡፡ እውነት ከውሸት የሚለይ እንጂ እንዲሁ ቀልድ አይደለም፡፡ የተወውም አሏህ ይቆርጠዋል፡፡ ከቁርአን ውጪ መመራት የፈለገ አሏህ ያጠመዋል፡፡ እሱ የአሏህ ጠንካራ ገመድ ነው፡፡ ጥበበኛ የሆነ አስታዋሽ ነው፡፡ ]
[ ፈዳኢል አልቁርአን ፡15 ; ቲርሚዚይ 290
ዐብድሏህ ቢን አባስ (ረዲየሏሁ አንሁ) እንዲህ ብሏል ፦
" ቁርአን ቀርቶና እንዲሁም ለሰራበት ሰው አሏህ በዱንያ ላያጠመው ፥ በአኼራ ከእድለቢሶች ላያደርገው ሐላፍትና ወስዶለታል፡፡ " ከዚያም ይህን አንቀፅ ቀራ....
فَمَنِ ٱتَّبَعَ هُدَاىَ فَلَا يَضِلُّ وَلَا يَشْقَىٰ
[ ከእኔም የኾነ መሪ ቢመጣላችሁ መሪየን የተከተለ አይሳሳትም አይቸገርምም፡፡ ]
የአሏህ ኪታብ ሑጃ ና መሪ በመሆኑ ላይ ብዙ አጨቃጫቂ ነገረሸ አይደለም፡፡ አብዛኛው ሙስሊም ያውቀዋል፡፡
ኢንሻ አሏህ በቀጣይ የቁርአን ሑጃነትና የሺዓዎች እረስ በራሳቸው የተጋጩ ንግግሮች እናያለን፡፡ ወሰላሙ አለይኩም፡፡
በቴሌግራም ለመከታተል....!!
↘↘↘↘↘↘↘↘↘↘↘
┏━ 🍃 ━━━━ 🍂 ━┓
✒️ @Aqida_muwehid🖋
┗━ 🍂 ━━━━ 🍃 ━┛
Saturday, December 15, 2018
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
የኢብኑ ተይሚያህ አቋም በተሃኩም ላይ...
፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን...
-
🔖 በአሏህ ሥም እጅግ በጣም ሩህሩህና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ በዚህ ሁፍ በአሏህ እርዳታ በመታገዝ ወደ ጧጉት መፋረድ ምን እንደሆነ እና ወደ ጧጉትም መፋረድ ያለው ሁክም እንመለከታለን፡፡ በምን አይነት...
-
✔ በአሏህ ስም እጅግ በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ الحمد لله وصلاة وسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه ومن والاه ..... أما بعد ° በዚህ አጠር ያለ ትምህርት ...
-
📌 [ አል-መድኸሉ ኢላ አልጃሚዕ ፊ ኩትቢ አል ኢማን ወርረድ ዓለል ሙርጂአህ ] -------------- ክፍል _ 2 -------------- بسم الله الحمد لله والصلاة والسلام على رسول ...
No comments:
Post a Comment