Saturday, December 15, 2018

🍃" የሺዓ ሐይማኖት "  🍃
   ______    ክፍል ሶስት (3) ______

ምስጋና ሁሉ ለብቸኛ ተመላኪው አሏህ ይድረስ፡፡ ሶላትና ሠላም በነብያችን ላይ ይውረድ፡፡

ይህ ካለፈው ትምህርት የቀጠለ አጠር ያለ ሺዓ ተብለው የሚጠሩና ራሳቸውን ወደ ኢስላም የሚያስጠጉ ቡድኖች ማንነት የምናይበት ነው፡፡

ሺዓዎች ከነብያችን በኋላ ሸሪዓ የሚደነግግ ፥ መዕሱም የሆኑ ( ከስህተት ጥቡቅ የሆኑ) ፥ ወንጀል የማይሰሩ ፥ ከአሏህ ወህይ የሚደርሳቸው ፥ ቁርአን የሚሽሩ ፥ ልቅ የሆነውን የሚገድቡ ፥ ጥቅል የሆነውን ለውስን የሚያደርጉ (የሚወሰሸኑ) የሆኑ 12 (አስራ ሁለት ) አኢማዎች አሉን ይላሉ፡፡

በነዚህ አኢማ ብለው በሚጠሯቸው ግለሰቦች የተነሳ ከፍተኛ ድንበር ማለፍ ላይ ወድቀው ሙሉ በሙሉ ጥመት ላይ ተዘፍቀው ይገኛል፡፡

፩). ሺዓዎች ለምንድነው የኢማማቸው ንግግር ቁርአን ይሽራል፡፡ ልቅ የሆነው ይገድባል ብለው የሚያምኑት ?

እነዚህ ቡድኖች " ኢማም " የሚሉትን ሰው የቁርአን ብቸው የግንዛቤ ባለቤት አድርገው እንደውም ኢማም ማለት " ተናጋሪ ቁርአን " ነው በማለት ይገልፃሉ፡፡ ኢማሞች የአሏህ ዒልም (እውቀት) ማከማቻና የወህይ ሚስጥር የሚጠብቀ ተደርገው ይታመናል፡፡

በነብያችን (ሰለሏሁ አለይሒ ወሰለም ) መሞት የአሏህ ዲን ኢስላም (ሸሪዓ መደንገግ) ሙሉ አልሆነም ብለውም ያምናሉ፡፡

እንደውም ያ የቀረው ያልተሟላው ሸሪዓ ለዓሊይ (ረዲየሏሁ አንሁ) ትተውለት ሔደዋል ብለውም ያምናሉ፡፡ ከዚያም ዓሊይ (ረ.ዐ) ከዚያች ከተሰጠው ነገር እያወጣ ዘመኑን የሚፈልገው አይነት ሸሪዓ ደነገገ ማለት ነው፡፡ አዑዙቢላህ ፡፡ ከዚያ የቀረው ሸሪዓ የማርቀቅ መብት ከሱ በኋላ ላሉት ተወላቸው፡፡

ሺዓዎች የአኢማዎቻቸውን ንግግር እንደ አሏህ ንግግር ነው የሚቆጥሩት፡፡ እንዲህ ይላሉ ፦

أن حديث كل واحد من الأئمة الطاهرين قول الله عز وجل ، ولا اختلاف في أقوالهم كما لا اختلاف في قوله تعالى.

📚 شرح جامع (على الكافي) : ٢/٢٧٢

" የጠሩ የሆኑ አአማዎቻችን እያንዳንዳቸው ንግግራቸው የአሏህ (ዐዘ ወጀል) ንግግር ነው፡፡ በንግግሮቻቸውም ምንም መጋጨት የለም፡፡ ልክ በአሏህ ንግግር ላይ መጋጨት የሚባል ነገር እንደሌለው ሁሉ፡፡ "

📚 ሸርህ አልጃሚዕ (በ አልካፊ) ፡ 2/272

እንደውም የአኢማዎች ንግግርም " ቃለ አሏህ " ( አሏህ እንዲህ ብሏል) ተብሎ ቢዘገብ ችግር የለውም ይላሉ፡፡ ለምሳሌ .....

ከአቡ ዐብድሏህ ( ጃዕፈር ኢብን ሙሐመድ አስሷዲቅ ማለታቸው ነው) ከሱ የተወራ ሐዲስ ከአባቱ ወይም ከአያቶቹ የሚዘግበው የሆነ የሰማ ሰው " አሏህ እንዲህ ብሏል " ብሎ ማውራት ይፈቀድለታል ይላሉ፡፡

📙 📚 ሸርህ አልጃሚዕ (በ አልካፊ) ፡ 2/272

በነሱ እምነት መሠረት ኢማማቸው ቁርአን በማንኛው ርዕስ ላይ የመወሰን የመገደብ ስልጣን አለው ብለው ያምናሉ፡፡ ወይም ቁርአን በቁርአን የመሻር  መብት አለው ይላሉ፡፡

በዚህ ዘመን እንድ ትልቅ መሪያቸው የሚቆጥሩት ሰው እንዲህ ብሏል

" (ሸሪዓ መደንገግ) ቀስ በቀስ የሆነበት ጥበቡ ተጠናቋል፡፡  ሸሪዓዊ አህካሞችን ከፊሉ በማብራራት ሌላው ደግሞ በመደበቅ፡፡ ነገር ግን አሊይ (ረ.ዐ) በወስያዎቹ ላይ አስቀምጦታል፡፡ ሁሉ የተናዘዙለት ደግሞ ለሌላኛው ያስተላልፋል፡፡ ለጉዳዩ በሚገጥም ጊዜ ሊያሰራጨው፡፡ ...."

[ ሙሐመድ ሁሰይን አል ካሺፍ አልጊጣ አስሉ ሺዓ ፡ 77]

አኢማዎቻቸው ልክ እንደነብያቶች እንደመላኢኮች አድርገው ይቆጥሯቸዋል ፡፡ ከሰማይ የወረዱ አጠቃላይ የአሏህ ኪታቦች አኢማዎች ዘንድ አለ በማለት የሚቀጥፉ ናቸው፡፡

( ይህ በሚቀጥሉ ክፍሎች በመረጃ እናየዋለን፡፡ )

በቁርአን የተጠቀሱ አንዳንድ ለብዙ ነገር የሚያጠቃልሉ ቃላት በአኢማዎቻቸው አማክኝነት ያልተገደበውን ሲገድቡ ይስተዋላሉ፡፡ ለምሳል

ኩፍር ፥  ኩፋር ወይም ደግሞ ሽርክ ፥ ሙሽሪኮች ተብለው በአሏህ ኪታብ የተጠቀሱ ቃላት ኩፍር የሚለው ሁሉንም የክህደት አይነቶች የሚያጠቃል ሆኖ ሳለ ፥ ሽርክ ወይም ሙሽሪክ የሚለው ሁሉንም በአሏህ ማጋራትና በአሏህ ያጋራ ሰው የሚያጠቃልል ሆኖ ሳለ እነሱ ግን ለአላማቸው በሚያመች መልኩ ብቻ ይገድቡታል፡፡

በብዙ ዘገባዎቻቸው እንደተገኘው  ኩፍር (ክህደት) የሚሉ ቃላት በ ዓሊይ (ረ.ዐ) ዊላያነት የካደ በሚል ይፈስሩታል፡፡ ሽርክ የሚለው ደግሞ ከአማማቸው ጋር ሌላ ኢማም መያዝ አድርገው ገድበውታል፡፡

- በአሏህ ኪታብ በጥቅሉ የተነገረ ነገር እነሱ ያለ መረጃ ይገድቡታል ፡፡ የኢማምያ ነጥብ ከኩፍርና  ከሽርክ የበለጠ ነጥብ አድርገው ያምናሉ፡፡ ይህ የዓቅልም የነቅል የሚደግፈው ነገር አይደለም፡፡ በዚህ ከሙስሊሞች የጋራ ስምምነት ወጡ ፡፡

አሏህ እንዲህ ብሏል ፦

إِنَّآ أَنزَلْنَٰهُ قُرْءَٰنًا عَرَبِيًّۭا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

( እኛ (ፍቹን) ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው፡፡ )

በቀጣይ ከዚህ ጥመታቸው ከፊሎቹን ለማስታወስ ያህል እንጠቅሳለን፡፡

☞ ወቢላሒ አት-ተውፊቅ

               📮   © አቡ ሙስሊም ናሙስ
               📮ረጀብ 26 / 1439 ዓ.ሒ

አልኢንቲሳር ሊ'ሒዝቢላህ አልሙወሒዲን

telegram.me/aqida_muwehif

No comments:

Post a Comment

የኢብኑ ተይሚያህ አቋም በተሃኩም ላይ...

  ፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን...