Saturday, November 3, 2018

✿[ ዑዝር ቢል-ጀህል የተመለከቱ ነጥቦች ]
• ክፍል አንድ (1)
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

°በአሏህ ስም እጀምራለሁ፡፡ ምሉዕ የሆነ ምስጋና ለአለማቱ ጌታ ለአሏህ ይገባው፡፡ ሶላትና ሠላም በሙዕሚኖች ላይ አዛኝ ፥ በከሃዲያን ላይ ጨካኝ ተደርገው ፥ ከሰዐቲቷም በፊት በሠይፍ ላይ በተላኩት ውዱ ነብይ ﷺ ላይ ዘውትር ይውርድ፡፡

° አሏህ ሱብሃነሁ ወተዐላ ነብያችንን ﷺ በትክክለኛ ኃይማኖት ላይ ሲሆን በጠቃሚ ዕውቀትና በመልካም ስራ ላይ ልኳቸዋል፡፡በአሏህ ፍቃድ ዳዕዋቸውም በኪታብ ተጣርተው ፥ በሠይፍ ደግሞ ተረድተዋል፡፡

° አሏህ ወደ-ተውሒድ ወይም እርሱ በብቸኝነት ማምለክ እንዲጣሩ ልክ ከዚህ በፊት እንደላካቸው መልዕክተኞች ሁሉ ሐቅ አስይዞ ልኳቸዋል፡፡ እርሳቸውም አደራው ሙሉ በሙሉ አድርሰዋል፡፡ ሁሉም ነብያቶች የተላኩበትን ማህበረሰብ ወደ-ተውሒድ ተጣርተዋል፡፡ መልዕክተኞችም እንዲህ በሚል ቃል ታዘዋል...

اعبدو الله ما لكم من إلاه غيره ..........
" አሏህንም አምልኩ ፡፡ ከርሱ ውጪ ምን ሌላ አምላክ አላችሁ? "

° በሚል ነብያቶች ፥ ሩሱሎች ህዝባቸውን ወደ ተውሒድ አሏህን ወደማምለክ ፥ ሽርክን ወደመራቅ ፥ ከባለቤቶቹም ስለማጠንቀቅ አስተምረዋል፡፡

° የአሏህ ፍቃድ ከሆነ በዚህ ፅሁፍ ስለ-ዑዝር ቢል ጀህል በተመለከተ ከአንድ ወንድም እየተሰራጨ ያለው ፅሁፍ ትክክል አይደለም ብዬ ስለማምን እየበተነ ያለውን ሹብሃት ለመግለፅ ነው፡፡ ነገር ግን በጥቅሉ በትልቁ ሽርክ ላይ ዑዝር ቢል-ጀህል አለን? የሚለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የተለያዩ ዑለሞችን ንግግር አጣቅሶ ማቅረብ ይቻላል ግን ይህ (አሁኑ) ቦታው አይደለም፡፡

° ይህ የፌስቡክ ባልደረባችን የፃፈውን ነገር ውድቅ መሆኑ ከመናገሬ በፊት በዚህ ነጥብ ዙርያ ልናውቃቸውን ለይተን ልናያቸው የሚገቡ ነጥቦች መጥቀስ እፈልጋለሁ፡፡ የመጀመርያው በዚህ አይነት ርዕሶች ላይ ስንናገር "አል-አስማእ" (ስሞች) እና " አል-አሕካም" (ህግጋት) በተመለከተ ለይተን ማወቅ ይገባል፡፡ ብዙ ጊዜ እነዚህ ነጥቦች በመቀላቀል የሚመጣ በላእ የቁርአን አንቀጾች ጭምር ያለቦታቸው ለመተርጎምና የማይናገሩትን መልዕክት እየተሻሸሹ ሲቀመጡ ይታያል፡፡

፨° "አል-አስማእ"(ስሞች) :- ስንል ምን ማለታችን ነው?? አስማእ " የሚለው የአረብኛ ቃል "ስሞች" ማለት ሲሆን "ኢስም"(ስም) የሚለውን ቃል ብዜቱን ያመለክታል፡፡ ለምሳሌ ይህን ስሞች በአንድ ሰው ሐቅ ላይ ስንናገረው ፥ ሙስሊም ፥ ሙእሚን ፤ ፋሲቅ ፥ ካፊር ፥ ሙሽሪክ ፥ ሙብተዲዕ ፥ ዓሲ ፥ ዟሊም ፥ ሙዐኒድ ፥ ጃሒድ ፥ ሙከዚብ ፥ ሙዕሪድ ፥ ጣጉት ፥ የሁዲይ ፥ ነስሯኒይ የመሳሰሉት እነዚህ ስሞች እንላቸዋለን፡፡

፨ ° አል-አህካም (ህግጋት) ደግሞ ፦ በአንድ ግለሰብ ላይ እስልምናውን የሚሰጠው ብይንና በኩፍር ላይ የሚሰጠው ህግጋትን የሚመለከት ነው፡፡

° አል-አህካም (ህግጋት) ክፍሎች...
1). ዱንያ ላይ ያለው አህካም አንዱ ነው፡፡ ይህም በዋናነት አልወላእ ወልበራህ ፥ ጥላቻ ፥ መርዳት ፥ የመሳሰሉት፡፡ አንድ ሰው ካከፈርነው ጠላት አድርገን እንይዘዋለን፡፡ ካላከፈርነው ደግሞ እንወዳጀዋለን፡፡ የደም ፥ የገንዘብ ሐላልነት ሐራምነት ፥ መግደል ፥ መማረክ ፥ እነዚህ ሁሉ ዱንያዊ አህካሞች ናቸው፡፡

• ለተወዳጀነውም (ለሙስሊም) እንደዚሁ በርካታ ዱንያ ላይ የሚኖረው ሸሪዐዊ አህካሞች አሉት፡፡

2). የአኼራ አህካም(ህግጋት) ፦ ይህ ደግሞ አንድ ሰው ሙስሊም በመሆኑ ጀነት ይገባል፡፡ ካፊር ከሆነ እሳት ይገባል፡፡ የመሳሰሉትን አህካሞች ሰብስቦ የያዘ ነው፡፡

° ሼይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ (ረሂመሁሏህ) እንዲህ ብሏል ፦

" እወቅ! የተክፊርና የተፍሲቅ ነጥቦች የአል-አስማእ እና የአል-አህካም ጉዳይ ነው፡፡ ይህም በአኼራ የወዒድ(የዛቻና) ፥ የወዕድ (የመልካም ዕድል ቀጠሮ) ጉዳይ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በዱንያ ደግሞ ወዳጅነትና ጠላትነት መግደልና ከመገደል መጠበቅ የመሳሰሉትን ነገሮች የያዘ ነው፡፡ " መጅሙዕ አልፈታዋ ፡ 468


° ኢማም ኢብን ተይሚያህ (ረሂመሁሏህ) እንዲህ ብሏል ፦

" ሙስሊም ፥ የሁዲይ ፥ ነስራኒይ የመሳሰሉ ስያሜዎች በዲን የሚገኙ ስሞች ናቸው፡፡ በዲን ስያሜዎች ላይ የተያያዘ ብይን (ሁክም) ኢስላም ፥ ኢማን ፥ ኩፍር ፥ ሪዳህ ፥ የሁዲነት ፥ ነስራኒነት የሚረጋገጠውም ይህንን በሚያስፈርድ ባህሪ ላይ ሲገለፅ ነው፡፡ " 38/226

° ሌላው በዚህ ስምና አህካም ላይ በተመለከተ መታወቅ ያለበት ነጥብ ይህ የስያሜና የአህካም ነገር የሚቆራኘው በአንድ ሰው በአኼራም ይሁን በዱንያ ጉዳዩ ዟሂሩ አይተን እንጂ የውስጡ ፈልቅቀን አይተን የምንናገረው አይደለም፡፡ ዟሂር በማየት የሚሰጡ ብይኖች ናቸው፡፡

° አንድ ሰው የሆነ ብይን ቢሰጥበት ወይም ዑዝርም የሚሰጠው ከሆነ የምንሰጠው ዱንያዊ የሆነ ሁክሙና ዟሂሩ አይተን ብቻ ነው፡፡ የውስጣቸው ነገርና በአኼራ የሚሰጣቸው ፍርድ በተመለከተ ወደአሏህ ዕውቀት የሚመለስ ነገር ነው፡፡ አሏህ ነው የሚያውቀው፡፡

° ሌላው መለየት እና መታወቅ ያለበት ነጥብ ይህ የስያሜና የአህካም ጉዳይ ሑጃ ከመድረሱ በፊትና ሑጃ ከደረሰ በኋላ ያለው ልዩነት አጥርቶ መመልከት ያስፈልጋል፡፡ ሼይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ (አሏህ ይዘንለት) እንዲህ ብሏል...:-

" በርግጥ አሏህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ) በስያሜና በአህካም ላይ ከሪሳላህ በፊት ያለ ነገርና ከሪሳላ በኋላ ያለውን ነገር ለያይቷል፡፡ እንዲሁም በስያሜና በአህካም ላይ ሰብስቧል፡፡ " መጅሙዕ አልፈታዋ ፡ 20/37

° በሌላም ቦታ ሼይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ (አሏህ ይዘንለት) እንዲህ ብሏል ፦

" የሽርክ ስያሜ ሪሳላ ከመድረሱም በፊት ይፀድቃል፡፡ ምክንያቱም እርሱ በጌታው ያጋራል፥ በሱም ያዘነብላል " መጅሙዕ አልፈታዋ 20/38

፨ ይህ ንግግሩ (ረሂመሁሏህ) አንድ ሰው ጃሒል ከሆነ ሙሽሪክ አይባልም ለሚሉ ሰዎች መልስ አለበት፡፡ ከቁርአን ማስረጃ መጥቀስ ይቻላል፡፡ አሏህ እንዲህ ብሏል..

وَإِنْ أَحَدٌۭ مِّنَ ٱلْمُشْرِكِينَ ٱسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَٰمَ ٱللَّهِ ثُمَّ أَبْلِغْهُ مَأْمَنَهُۥ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌۭ لَّا يَعْلَمُونَ

[ ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ አስጠጋው፡፡ ከዚያም ወደ መጠበቂያው ስፍራ አድርሰው፡፡ ይህ እነሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው፡፡]

፨ ኢማም ኢብን ተይሚያህ (ረሂመሁሏህ) ይህን አንቀፅ ማስረጃ በማድረግ አንድ ሰው በአሏህ ትልቁን ሽርክ የሚያጋራ ከሆነ ሪሳላ(ሑጃ) ቢደርሰውም ባይደርሰውም ሙሽሪክ የሚል ስም ይሰጠዋል፡፡ ባረከሏሁ ፊኩም እዚህ ላይ ከላይ እንደተብራራው ፡፡ ስያሜና አህካም የተለያዩ እይታ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ በቁርአኑ እንደተገለፀው አሏህ የአሏህን ቃል ያልሰማና ያልደረሰው ሰው አሏህ መጀመርያም ሙሽሪክ ብሎ ጠርቶታል፡፡ ስለዚህ ስያሜ ሑጃ ቢሰጠውም ባይሰጠውም ሙሽሪክ የሚል ስም ይሰጠዋል፡፡

° በመጅሙዕ አልፈታዋ (20ኛው ቅፅ) ላይ ኢብን ተይሚያህ ሌሎችም ማስረጃዎች ጠቅሷል፡፡ አሏህ እንዲህ ብሏል..

ٱذْهَبْ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ إِنَّهُۥ طَغَىٰ
ወደ ፈርዖን ኺድ፡፡ እርሱ ወሰን አልፏልና፡፡

ስለ ነብዩሏህ ሙሳ (ዐ.ሰ) አሏህ ሲናገር ገና የነብይ መልዕክት ሳይደርሰው በፊት አሏህ "ጠጋ" (ወሰን አልፏል) በሚል ገልፆታል፡፡ ሌሎችም መረጃዎች መጥቀስ ይቻላል፡፡

° እነዚህ ነጥቦች ለያይቶ ካለመመልከት የተነሳ ይህ ወንድም የተለያዩ መረጃዎችን ያለቦታቸው ሲጠቀምባቸው ነበር፡፡ አኼራ ላይ ስለሚሰጡ ቅጣቶች የመጡ አንቀፆችን ፥ ለስያሜ ሲያውላቸውና ሲጠቀምባቸው ይታያል፡፡ አንዳንድ የሚያመጣ አንቀፆች ደግሞ በራሱ ላይ ተገልብጠው መረጃ የሚሆኑ ናቸው፡፡

° ሌላው ሸሪዐዊ ነጥቦች ብይን የሚሰጥባቸው ባላቸው ግልፅ የመሆን እና ድብቅ የመሆን ነገር ይወሰናል፡፡ ዟሂር የሆኑና ሁሉም ሰው ሊያወቃቸው የሚችሉ ነጥቦች (ተውሒድን መያዝና ሽርክ መራቅ) የመሣሠለው ነጥብ ላይ ምንም ዑዝር ቢል ጀህል የለም፡፡

° በቀጣይ ክፍል ልጁ በትልቁ ሽርክ ላይ ዑዝር ቢል ጀህል እንዳለ መረጃ ይሆኑኛል ብሎ የጠቀሳቸው ማስረጃዎች እናያቸዋለን፡፡ በነዚህ ነጥቦች ላይ አስተያየት ስንሰጥ የሽርክ ነጥብና ሌሎች ኩፍር ሊሆኑ የሚችሉ አንዳንድ አጀንዳዎች እኩል እየጨፈለቅን ማየት የለብንም፡፡ እላለሁ ... በቀጣይ ክፍል በአሏህ ፍቃድ እስክንገናኝ.....

[ ወቢላሒ አት-ተውፊቅ ]
© አቡ ሙስሊም ናሙስ
❀ ሶፈር 24/1440 ዓ.ሒ............

No comments:

Post a Comment

የኢብኑ ተይሚያህ አቋም በተሃኩም ላይ...

  ፨ በአሏህ ሥም እጅግ በጣም አዛኝና በጣም ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ፡፡ ፨ በዚህ ፅሁፍ ሼይኹል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህን ከኸዋሪጆች አመለካከት እናጠራለን፡፡ አቡ ኢምራን ብዙዎች እንደምታውቁት ሁለት ገሪብ የኸዋሪጆችን...